ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በሚዋሰኑበት የቱርካና አካባቢ በከተሰተ ግጭት 25 ሰዎች ተገደሉ።
ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በሱዳን ሰሜን ዳርፉር ግዛት በተባባሰው ውጊያ ምክንያት የሚሰጠውን የህክምና እርዳታ ለማቆም መገደዱን ዛሬ አስታወቀ።
ትናንት በጀርመን በተካሄደው ወቅቱን ያልጠበቀ ምርጫ አብላጫ የሕዝብ ድምፅ ያገኘው ክርስቲያን ዴሞክራት ፓርቲ የጥምር መንግሥት ለመመስረት ጥረት እያደረገ ነው።
ሩሲያ ዩክሬን ላይ ጦርነት የከፈተችበት ሦስተኛ ዓመት በዛሬው ዕለት ኪየቭ ላይ ታሰበ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ካልተፈለጉ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ዝግጁነኝ ብለዋል።