የየካቲት 19 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው ጋር ነገ መቅዲሾ ይሄዳሉ ሲል የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምንጮች መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አንድ የሱዳን አንቶኖቭ ወታደራዊ የማጓጓዣ አውሮፕላን ትናንት ለሊት ተከስክሶ 46 ወታደሮችና ሰላማዊ ሰዎች ሞቱ። በዚሁ አደጋ 10 ሰዎችም ቆስለዋል።
የሩስያና የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶች ከሶስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ እንደሚነጋገሩ ሩስያ አስታወቀች።