በመራዊ የተፈጸመው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ላይ “ገለልተኛ ምርመራ ተደርጎ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ” አሜሪካ ጥሪ አቀረበች። በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ ሊጓዙ ነው። የሱዳን ጦርነት 700,000 ሕጻናትን ለብርቱ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ሊያጋልጥ እንደሚችል የተመ አስጠነቀቀ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ጋዛ ከምትገኘው ራፋ ሰላማዊ ሰዎች ለማሸሽ እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ ሰጡ። አሜሪካ እና ብሪታኒያ በየመን በፈጸሙት ድብደባ የተገደሉ 17 የሑቲ ታጣቂዎች አባላት ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ