የዓለም ዜና

የየካቲት 23 ቀን 2016 የዓለም ዜና


Listen Later

ኢትዮጵያውያን ቅኝ ሊገዛቸው የሞከረውን የጣሊያን ጦር ተባበረው ቢያሸንፉም እርስ በርስ ባደረጉት ጦርነት ብርቱ ሰብአዊ ቀውስ መድረሱን ርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓድዋ ድል 128ኛ ዓመት ሲከበር ተናገሩ። በሱዳን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለተቸገሩ ርዳታ እንዳያቀርቡ መተላለፊያ መከልከል በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ፎልከር ቱርክ አስጠነቀቁ። የቻድ ወታደራዊ መሪ ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በሀገራቸው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። በጋዛ ርዳታ ከጫነ የከባድ ተሽከርካሪዎች ቅፍለት አቅራቢያ በተከፈተው ተኩስ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን የተመ ታዛቢዎች ቡድን አስታወቀ
...more
View all episodesView all episodes
Download on the App Store

የዓለም ዜናBy DW