አርዕስተ ዜናዎች
ከ250 ሚሊየን በላይ አዋቂ እና አዳጊ ሴቶች ግርዛት እንደተፈጸመባቸው ዛሬ ይፋ የተደረገ ጥናት አመለከተ።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የቀበሌ አመራሮችና ሚሊሻዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን መፈናቀላቸው ተሰማ። «የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት» ኦነሰ በወረዳው የሚገኙ አብዛኞቹን ቀበሌያት መቆጣጠሩን ተፈናቃዮቹ ገልጸዋል።
በሀረሪ ክልል አሚር ኑር ወረዳ የክልሉ መስተዳድር ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን ይዞታዎች ለማፍረስ በወሰደው እርምጃ ግጭት ተከስቶ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።