የየካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
የተመድ ፣የሱዳንን ጦር የሚወጋውን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይልን እርዳታ በማገድ ከሰሰ የድርጅቱ የሱዳን እርዳታ አስተባባሪ እንደተናገሩት ፣ በተለይ በሱዳንዋ ግዛት ዳርፉር የሚገኙ ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑ እርዳታዎችን ለሚያስፈልጓቸው ሰዎች ማቅረብ አልቻሉም።
በጋዛ የተኩስ አቁም ቀጣይ ደረጃ ላይ ለመነጋገር ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ዶሀ ኳታር ሄዶ የነበረው የእስራኤል የልዑካን ቡድን ወደ ሀገሩ መመለሱን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አስታወቀ።
ትራምፕ ወደ አሜሪካን በሚገቡ ብረታ ብረቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እጥላለሁ አሉ።