በዜና መጽሔት አምስት ዘገባዎች በትንታኔ ይቀርባሉ ። ለጸጥታ ቅድሚያ ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪቃ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ፤ ሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ ለአፍሪቃ ህብረት የላከው ደብዳቤ እና አንድምታው ፤ በደብረታቦር ከተማ የተከሰተው የጸጥታ አለመረጋጋት እና የነዋሪው አስተያየት ፤ የኢትዮጵያውያን ሕብረትና የሽግግር ቅድመ ሁኔታ ላይ የተደረገ ምክክር እና አንድምታው፤ የአውሮጳ መሪዎች ከኤኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ የያዙት መንገድ የተመለከቱ ዘገባዎች ይደመጣሉ ።