7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ"አስቻይ" የፀጥታ "ሁኔታዎች" ባሉባቸው ባላቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቋል።
ሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ከፌደራል መንግስት ከማህበራት ተወካዮች ከታዋቂ ሰዎችና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለሶስት ቀናት ያካሄደውን የምክክርና የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃ ግብር አብቅቷል። በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ውስጥ በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት 6 የኃይል ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በመውደቃቸው ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ ወደ ሱዳን የሚተላለፈውን ጨምሮ በዞኑ አብዛኛዎቹ ከተሞች ኤሌክትሪክ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።