Australia has thousands of kilometres of spectacular coastline, and a trip to the beach for a swim is a much-celebrated part of the lifestyle – whether to cool off, keep fit, or to socialise. Being aware of beach safety is vital to minimise the risk of getting into trouble in the water. This includes understanding the threat that sharks pose to minimise the chance of encountering a shark and being aware of shark behaviour, so you know how to react to stay safe. - በጣሙን ተወዳጅና የኑሮ ዘዬ አካል ለሆነው ዋና ወደ ባሕር ዳርቻ ተጉዞ ለመዋኘት፣ ቀዝቀዝ ለማለት ይሁን፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ወይም የማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፎ ለማካሔድ አውስትራሊያ በሺህ ኪሎ ሜትሮች የሚቆጠር ማራኪ የባሕር መስመር አላት። ውኃ ውስጥ ለችግር የመዳረግ ተጋላጭነትን መቀነሻ የባሕር ዳርቻ ጥንቃቄን መገንዘብ ወሳኝ ነው። ይህም ሻርክ የሚደቅነውን አደጋ በመገንዘብ ከሻርክ ጋር የመጋፈጥ አጋጣሚን ለመቀነስና የሻርክን ባሕሪይ መረዳትን ያካትታል፤ እናም ደህንንነትዎን ጠብቀው ለመቆየት ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ።