
Sign up to save your podcasts
Or


የዓለም ኢኮኖሚ እየተለወጠ ነው። የኢኮኖሚ እና የንግድ ኃይል ከባህላዊ ማዕከላት በመውጣት ወደ እስያና ወደ ተለያዩ የዓለም ክልሎች እየተስፋፋ ነው። ሩሲያ የሩቅ ምሥራቅ ክልሏን ከእስያ-ፓሲፊክ ጋር ለማገናኘት እየሰራች ሲሆን፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ እና ሌሎች የእስያ ኢኮኖሚዎችም በአዲሱ የዓለም ኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ የበለጠ ሚና እየወሰዱ ነው። ይህም እ.ኤ.አ ከመስከረም 1 እስከ 4 2026 በሩሲያ ቭላዲቮስቶክ - የምስራቃዊ ኢኮኖሚ ፎረም በሰፊው እየተነሳ ነው፡፡
“በብዙ ማዕከላዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን፣ አገራት ራሳቸውን ወደ ዓለም ኢኮኖሚ ማዕከል ማምጣት አለባቸው፤ ይህም በመከፋፈል ሳይሆን በትብብር፣ በመቀናጀት እና በኢኮኖሚ ውህደት ሊሳካ ይችላል።” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ተመራማሪዉ ዱጋሳ ሙለጌታ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ከቭላዲቮስቶክ እስከ አዲስ አበባ የሚዘልቀውን የዓለም ኢኮኖሚ ለውጥ፣ የሩሲያ ሩቅ ምሥራቅ ከእስያ ጋር እየገነባ ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር እና የበርካታ የኢኮኖሚ ማዕከላት መፈጠር ለአፍሪካና ለኢትዮጵያ የሚያመጣውን ዕድል እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ።
ሙሉውን መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡
«አሜሪካ በኢራን ላይ በርካታ ሙከራዎችን አድርጋለች፣ ነገር ግን የኢራንን ኃይል መቆጣጠር አልቻለችም... ጦርነቱ እየሰፋ ከሄደ እና ኢኮኖሚው ጥያቄ ውስጥ ከገባ፣ አሜሪካ አሁን እውነተኛ ተፅዕኖ ላላቸው ብሪክስን ጨምሮ ለተቀናጁ ሀገራት እጇን ለመስጠት ልትገደድ ትችላለች።» ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር መሐመድ ኢሳ ሹራላ (ዶ/ር) ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በሆርሙዝ ሰርጥ ያለው የጂኦፖለቲካ ውጥረት በአፍሪካ የኢነርጂ ደህንነትና ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የሚፈጥረውን ዕድል ወደ ተጨባጭ ንግድ ለመቀየር የሚያስፈልጉትን የሎጂስቲክስና የንግድ ትስስሮች ከመሳይ አየለ(ዶ/ር) ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሎጂስቲክስና የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ረዳት ፕሮፌሰር ጋር እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ።
"የዝግጅቶች የጉባኤ ወይም MICE ቱሪዝም በመባል የሚታወቀው ዘርፍ በ180 ሀገራት ውስጥ በተደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች ወደ 1.6 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን አዘዋውሯል፤ 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ገቢም አስገኝቷል። ስለዚህ በቢሊዮኖች ሳይሆን በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ይህም በቀጥታ ሽያጭ ብቻ የሚገኝ ነው። ከእሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ኢንዱስትሪዎች ሲጨምር ወደ 3.1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ይደርሳል። ይህም በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ሲሰላ 1.8 ትሪሊዮን ዶላር አካባቢ ነው። በእርግጥ ይህ ኢንዱስትሪ ራሱ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል። ስለዚህ ከአንድ ሀገር ኢኮኖሚ አንፃር ስንየው፣ በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ ኢኮኖሚዎች 16ኛ ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው እገምታለሁ።" ሲሉ ዮአዳን ጥላሁን፣ የ«ፍሎውለስ ኢቨንትስ» መስራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ዝግጅቶችና ኤግዚቢሽን አዘጋጆች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ የዝግጅቶችና ስብሰባዎች ኢንዱስትሪ ለዓለምና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ያለውን ግዙፍ ፋይዳ፣ እንዲሁም ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ያለውን ስትራቴጂያዊ ሚና እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ከኢኮኖሚ ትስስርና ከአህጉራዊ ትብብር አንፃር የአፍሪካ ወደብ አልባ ሀገራት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችና ዕድሎች ከፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)ጋር እንዳስሳለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበዉን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
"በአፍሪካ ያለው የኢንሹራንስ ዘርፍ አሁን ካለበት የካሳ ክፍያ ብቻ ላይ የሚያተኩር አቀራረብ ወደ የጽናትና የመቋቋም አቅም ኢንቨስትመንት የሚያተኩር ሥርዓት መሸጋገር ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የአስተሳሰብ ለውጥ በጣም ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ተቋማት ይህንን የጥበቃ ክፍተት ለመሙላት አዳዲስ የንግድ ሞዴሎችን እየተገበሩ ነው። ለምሳሌ፣ በአፍሪካ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ አደጋዎች የሚደርሱ ኪሳራዎች ውስጥ በኢንሹራንስ የሚሸፈነው 0.5 በመቶ ብቻ ነው። በአደጉ ሀገራት ግን ይህ ቁጥር 50 በመቶ ይደርሳል። ስለዚህ ከአየር ንብረት ነክ አደጋዎች አንፃር በአፍሪካ እጅግ ሰፊ የኢንሹራንስ ጥበቃ ክፍተት እንዳለ ይህ በግልጽ ያሳያል።" ፍቅሩ ጸጋዬ በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የስትራቴጂና የቢዝነስ ልማት ዋና ኃላፊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የ«ኮንቲነንታል ድሪፍት» ዝግጅታችን፣ ኢንሹራንስ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ጽናት እንዴት ስትራቴጂያዊ ምሰሶ ሊሆን እንደሚችል እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ 'ኢኤስጂ' (አካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና አመራራዊ) ዘላቂ የመልካም ስራ መመዘኛዎች ከተለመደው የማህበራዊ ኃላፊነት ባለፈ የኢንቨስትመንት ፍሰትን፣ የብድር አቅርቦትንና የንግድ ተወዳዳሪነትን የሚወስኑ ወሳኝ መስፈርቶች እየሆኑ መጥተዋል። አፍሪካ የአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠናን እውን ለማድረግና የኢንዱስትሪ ልማቷን ለማፋጠን በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህ መስፈርቶች ተጨማሪ የፋይናንስና የአቅም ጫና የሚፈጥሩ እንዳይሆኑ ስጋት አለ።
"አፍሪካውያን የአካባቢ የበካይ ጋዝ ልቀት ምንጮች ባንሆንም፣ የ'ኢኤስጂ' መመዘኛዎችን ከእኛ አህጉራዊ እና ማህበራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር አጣጥመን መጠቀም ይኖርብናል። ለአውሮፓ የአካባቢ ልቀትን መቀነስ ዋነኛ አጀንዳ ቢሆንም፣ ለአፍሪካ ግን ዋናው ትኩረት እንደ ሴቶችን ማካተት፣ የፋይናንስ ተጠቃሚነትን ማስፋፋትና የማህበራዊ ክፍተቶችን መሙላት ያሉ ጉዳዮች ላይ መሆን አለበት። እነዚህን መመዘኛዎች ከራሳችን የልማት ቅድመ-አብዮቶች አንፃር ካቀናጀናቸው ሰፊ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና የካርቦን ገበያን ጨምሮ አዳዲስ የፋይናንስ ምንጮችን ለመክፈት ትልቅ ዕድል ይፈጥርልናል።" ሲሉ ጆሴፍ አዎላቢ — የቀድሞ የዓለም አቀፉ የቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንቶች ማህበር (ACCA) ፕሬዝዳንት እና የካርቦን ገበያና አረንጓዴ ፋይናንስ ዓለም አቀፍ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ እነዚህ ዘላቂ የመልካም ስራ መስፈርቶች ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ዕድገት ማፋጠኛ ሊሆኑ የሚችሉበትንና የአህጉሪቱን የልማት ፍላጎቶች እንዴት ሊደግፉ እንደሚችሉ በሰፊው እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
አፍሪካ ለዓለም ገበያ በርካታ ጥሬ ዕቃዎችን የምታቀርብ ቢሆንም፣ ከውጭ ለሚገቡ ምርቶችም ጥገኛ ናት። አሁን ላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሲመሠረት፣ ትኩረቱ ወደ ቀጠናዊ የዋጋ ሰንሰለቶች ግንባታ እና የሎጂስቲክስ አውታሮችን በማጠናከር ሀብቱ በአህጉሪቱ እንዲቆይ ማድረግ ላይ እየተሸጋገረ ይገኛል።
" አብዛኛዎቹ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከአፍሪካ አይደሉም፤ ከ90 እስከ 95 በመቶ የሚሆነው የገቢና የወጪ ንግድ ጭነት የሚከናወነው በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ ኩባንያዎች ነው። ይህ በወጪያችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በቁጥር ላሳያችሁ፤ ከቻይና ሻንጋይ እስከ ኢትዮጵያ ለአንድ የዕቃ መጫኛ ኮንቴነር የምንከፍለውን ክፍያ እንመልከት..." ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሎጅስቲክስ እና ዕሴት ሰንሰለት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መሳይ አየለ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የንግድና የሎጂስቲክስ አውታሮቿን በማቀናጀት ከጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት ወጥታ የራሷን የዋጋ ሰንሰለት እንዴት መዘርጋት እንዳለባት እንቃኛለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
አፍሪካ ትልቅ ወጣት ህዝብን ይዛለች፤ ነገር ግን ይህ የዴሞግራፊ ዕድል ወደ እውነተኛ የኢኮኖሚ ውጤት እንዲቀየር የፋይናንስ ተደራሽነት እና ተቋማዊ ማሻሻያዎች ወሳኝ ናቸው።
"የውስጥ ሀብታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ያለንን ጥገኝነት ለመቀነስ ይረዳናል። ማናቸውም ሀገር ያለ ዓለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ብቻውን ኢኮኖሚውን ማሳደግ ይችላል ማለቴ አይደለም፤ ድጋፋቸው ያስፈልገናል። ነገር ግን ማድረግ ያለብን ጥገኝነታችንን መቀነስ ነው። የውጭ ተቋማትን አስተዋጽኦ ለመቀነስ ማዕድናችንን ማቀነባበር አለብን። ለምሳሌ በማሊ ከወርቅ ብቻ ብዙ ወጣቶችን ስራ ማስያዝ እና ዓላማዎቻችንን ማሳካት እንችላለን።" — ሲሉ ዣን ፑዲዩጎ፣ የቪዥን ፈንድ ማሊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የመንግስት የወጣቶች ልማት እና ድህነት ቅነሳ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ በሳህል ቀጣና በተለይም የማሊ ወጣቶች የኢኮኖሚ ማካተት እና በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ መስፋፋት ዙሪያ የሚደረጉ ወሳኝ ውይይቶችን እንቃኛለን። ለዚህም የቪዥን ፈንድ ማሊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የመንግስት አማካሪ ዣን ፑዲዩጎ እንዲሁም ዮናስ ፍቅሩ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡
አፍሪካ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆነው የአህጉሪቱ ህዝብ ከ25 ዓመት በታች ነው። ይህ ግዙፍ የሰው ኃይል ወደ ኢኮኖሚያዊ ውጤት እንዲቀየር፣ ትምህርት እና ሥልጠና ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር መጣጣም አለባቸው።
"ኢትዮጵያ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። ከ70 በመቶ በላይ የሆነው ህዝባችን ከ30 ዓመት በታች ነው። መንግስት ለስራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ ኢላማ በማስቀመጥ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል። ይህንን ለማሳካትም በ2020 መጀመሪያ ላይ የተቋቋመውና በአሁኑ ወቅት ወጣት ከሚባሉ ተቋማት አንዱ የሆነው 'የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር' ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው።" ሲሉ በኢትዮጵያ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ብሔራዊ አስተባባሪ እና የ ‘አሶሴሽን ኦፍ ቻርተርድ ሰርቲፋይድ አካውንታንትስ’ (ACCA) ባልደረባ ቃልኪዳን ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ አፍሪካ የራሷን የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ለማፍራት የምታደርገውን ጥረት እና ስለ "ክህሎት ሉዓላዊነት" እንወያያለን።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
"ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል። አሁን ደግሞ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ይህን ሂደት እንደሚጀምሩ ቃል እየገቡ ነው፤ ምንም የተለየ አዲስ ነገር ይዘው እንደሚመጡ አልጠብቅም።" ሲሉ ፈቃአህመድ ነጋሽ፣ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የህዳሴ ግድብን ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ ውስብስብነት እንዲሁም የኢትዮጵያን አዳዲስ የኦዲት ማሻሻያዎች በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ፈቃአህመድ ነጋሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የገንዘብ ዘርፍ ሀላፊ ተመስገን ጌታዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡