Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
''Continental Drift' is a program tracking the tectonic changes reshaping Africa and redefining the Global South's role in the world. The show explores how policies, markets, and innovation intersect ... more
FAQs about Continental Drift:How many episodes does Continental Drift have?The podcast currently has 13 episodes available.
November 14, 2025ፍትህ በችሎት ላይ : የአፍሪካ ድምፆች ከአለምዓቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ባሻገርፍትህ የውጭ ተጽዕኖን ሲከናነብ ፣ ማን ይዳኛል ? ማንስ ደግሞ በነጻ ይለቀቃል? '' የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ምስረታን ስንመለከት፣ አብዛኞቹ ለክስ የሚቀርቡ ጉዳዮች የአፍሪካ ጉዳዮች ሆነው እናገኛቸዋለን። በአህጉር አቀፍ ደረጃ ለጦርነቶች አስተዋጽኦ የሚያደርጉት አብዛኞቹ ሀገራት ግን የአፍሪካ ሀገራት አይደሉም። ስለዚህ እንደ አፍሪካውያን የዉስጥ ጉዳዮቻችንን የምናይበት የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የምናቋቁምበት ጊዜ አሁን እንደሆነ አምናለሁ። ራሳቸውን ከአይሲሲ ቻርተር ያገለሉትን የአፍሪካ ሀገራትንም ማድነቅ ወይም ማመስገን እወዳለሁ '' ስትል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች።በዚሁ የኮንቲነንታል ድሪፍት መሰናዶ ሁለት የተለያዩ ግን ወሳኝ ጉዳዮችን እናያለን ፣ አፍሪካዊያን ለምዕራባዊያ ባደሩ የ'ፍትህ ተቋማት ስለሚፈጸምባቸው በደልና እና የአፍሪካ ሀገራት አማራጮች ምንድን ናቸው ስንል የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች የቀድሞ ተመራቂዎች ኮሚሽን ፌዴሬሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር አልፍሬድ ኤሊ ፣ የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን ዓለም አቀፍ ዋና ጸሐፊ ግሎሪያ ሲሲያ ምማሲን እና የአፍሪካ የህግ ተማሪዎች ፌዴሬሽን የሰሜን አፍሪካ ክልላዊ ዳይሬክተር ራታኒያ ዳዊን ጠይቀናል፡፡ በሌላኛው ጉዳያችን ደግሞ የአፍሪካ የግብርናና ገጠር ልማት ጦችን ለማስመዝገብ አፍሪካ ምን ማድረግ አለባት ስንል የኢንተር አፍሪካ ፊቶሳኒተሪ ካውንስል አስተባባሪ ዶ/ር ሳሊዩ ኒያሲ፣ የአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቫላካቲ እና ሌሎችንም አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡...more1h 0minPlay
November 14, 2025የባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የዉዝዋዜዎች ኃይል - ማንነትን ለመግለጥና ለምጣኔ ኃብታዊ እድገትኢትዮጵያ የብዝሃ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ተፈጥሮ ካደላት መገለጫዎቿ እኩሌታ ብዙኃ ቋንቋና ባህል ያላት መሆኑ የልዩ መልካነቷ ማሳያ ነው፡፡ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎቿም ትናንቷን የሚዘክሩ ፣ የነገን መልክ ዛሬ ላይ ለመቅረጽ በብዙ የሚጥሩ ናቸው፡፡ እንዴት ? “ አንደኛ የስራ እድል ምንጭ ይሆናል። የሚጫወቱ ሰዎች ቢበዙ የስራ እድል ነው ብዙ ሙዚቀኛ በዚህ ሙያ ላይ ያሉ ሙዚቀኞች እንደመኖሪያቸው ይሆናል። ሁለተኛ ደግሞ የሀገር ሀብት ነው። እንደ ሀገርም መሸጥ ይቻላል ሙዚቃን መሸጥ ይቻላል ፣ በነገራችን ላይ ያው [ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር] በተለያየ መንገድ ገቢ ማግኘት አለብን ብዬ አስባለሁ። እና አንደኛው ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃ በትልቁ ገቢ ማምጣት ይችላል ብዬ አስባለሁ ፤ ከሌላው አለም። ሙዚቃችንን ብንሸጠው እንደ ሀገር እንጠቀማለን። ዋናው ደግሞ የኢትዮጵያን ጥሩ ገጽታ ታስተዋውቂበታለሽ። ” ሲል የሙዚቃ አጥኚው እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያዊያንን ማንነት ለመላዉ ዓለም ስለሚያንጸባርቁ ባህላዊ ዉዝዋዜዎች እና በኢትዮጵያዊያን መገለጫ ስለሆነው ዋሽንት አንስተን ስለባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ሁሉንአቀፍ አቅማቸው በሰፊው እንነጋገራለን ፤ ለዚህም የፈንዲቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ጋብዘናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡...more1h 0minPlay
October 28, 2025መጭውን ጊዜ መቅረጽ፡ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ፈጠራ ኢኮኖሚኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ170 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውጪ ለምታስገባው የእንጨት ዉጤቶች ወጪን ታወጣለች ። [...]መንግሥት የእንጨት ሥራ ውጤቶች ከውጭ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ቢያንስ ለመቀነስ ዉሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በውስጡ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ምክንያት ይህ ውሳኔ ተሰርዟል፣ የእንጨት ውጤቶች እንደገና ለማስገባት ተፈቅዷል። ነገር ግን ክልከላው በተጣለበት አስር ወራት ጊዜ ውስጥ እንኳን በሀገር ውስጥ ገበያው ፍላጎት ምክንያት ብዙ ሀገር በቀል የእንጨት ሥራ ውጤት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየአቅጣጫው መጥተው አይተናቸዋል።” ሲሉ የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለሀገሪቱ የፈጠራ ኢኮኖሚ ያላቸውን ሚና ፣ ፈተናና እድሎች በሰፊው እንመለከታለን፡፡ ለዚህም የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ እና የፓራዳይዝ ፋሽን ባለቤትና ዲዛይነት ገነት ከበደን ጋብዘናቸዋል፡፡ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡...more1h 0minPlay
FAQs about Continental Drift:How many episodes does Continental Drift have?The podcast currently has 13 episodes available.