
Sign up to save your podcasts
Or


"አሮጌ እርሾና አዲስ ሊጥ" - የ2024 ዘመን መለወጫ ዋዜማ መርሃ ግብር ላይ በፓስተር ዳንኤል ሳቡሬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ 1 ቆሮ. 5፡7
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ዘጸ. 12፡15፣ ዘጸ. 13፡7፣ ማቴ. 16፡6፣ ማር. 8፡15፣ ገላ. 5፡1-15
የእግዚአብሔር ሥጦታ - የኢየሱስ ክርስቶስን ጽንሰትና ውልደት በተመለከተ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ማቴ. 1፡18-25፣ ሉቃ. 1፡26-35፣ ሉቃ. 2፡8-12፣ 21-32፣ 2፡15-20፣ 41-51
"ፍለጋውን መከተል" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
በዚህ ክፍል የተነሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡- መዝ. 25፡4-7፣ ሩት 1፡1-18፣ ማቴ. 25፡1-13፣ ሆሴ. 6፡3፣ ዮሐ. 14፡1-6፣6-7
"ኢየሱስን መውደድ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን ጥያቄ እየጠየቀ ያገለግላቸው ነበር።
ቁ. 15 "ከእነዚህ አብልጠህ ትወደኛለህን?"
ቁ. 16 "በእውነት ትወደኛለህን?"
ቁ. 17 "ትወደኛለህን?"
ኢየሱስን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው?
ጴጥሮስ ለጌታ ጥያቄዎች መልስ ከሰጠ በኋላ በህይወቱ የታዩ ለውጦች፡-
በ 2 ሳሙኤል 9 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ሮሜ 9፡1-4፣ 10፡1-2
ሀ) በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱ ሊያዝን እንደሚችል ተጽፏል፡ -
1) እግዚአብሔር ያዝናል - ዮናስ 4፡11
2) ጌታ ኢየሱስ ያዝናል - ሉቃ.19፡41፣ ዮሐ. 11፡33-34፣ ማር.6፡34
3) መንፈስ ቅዱስ ያዝናል - ኤፌ. 4
ለ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነ ሐዘን
1) በእግዚአብሔር ምህረት ላይ የሚያስቆጣ ነው - ዮናስ 4፡1-3
2) ወደ ኀጢአት የሚወስድ ነው - 2 ሳሙ. 13፡1- 19
3) ተስፋ እንዳይታየን የሚያደርግ ነው - 1 ተሰሎ. 4፡15-18
ሐ) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን
1) ሰዎችን ወደ ንስሐ የሚገፋ ነው - ሐዋ. 2፡37-38
2) እግዚአብሔር ሲገስጸን የሚሰማን ሐዘን ነው - 2 ቆሮ. 7፡8-11
3) ሌሎች ችግር ውስጥ ሲሆኑ የሚሰማን ሐዘን ነው - ሮሜ 9፡1-5፣ 10፡1
4) ወደ ጾምና ጸሎት የሚመራ ሐዘን ነው - ነህ. 1፡1-4
በአባቶች ቀን "የሁላችን አባት - አብርሃም" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መነሻ ጥቅስ፡ ሮሜ 4፡16-17
አብርሃም በእምነት ያደረጋቸው 5 ነገሮች፡ -
1) አብርሃም #በእምነት የታዘዘ ሆነ - ዕብ. 11፡8፣ ዘፍ. 12፡1
2) አብርሃም #በእምነት ተቀመጠ - ዕብ. 11፡9-10፣ ዕብ. 12፡22፣ 1 ጴጥ. 2፡11፣ ፊል. 3፡20
3) አብርሃም #በእምነት ተስፋ አደረገ - ሮሜ 4፡18፣ ዕብ. 11፡11፣ ዘፍ. 15
4) አብርሃም #በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ - ሮሜ 4፡19
5) አብርሃም #በእምነቱ በረታ/ጸና እንጂ አተጠራጠረም - ሮሜ 4፡20
> እምነቱም ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት - 4፡22-23
"ጌታ ሊያድ'ሰን ይፈልጋል!" በሚል ርዕስ በወንድም አብርሃም ፈንተ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
1) እግዚአብሔር እንዲያድሰን፣ ትሑት መሆን ከእኛ ይጠበቃል። ኢሳ. 66፡2፣ መዝ. 51፡12፣
2) እግዚአብሔር እኛን የሚያድስበት ዓላማ / ለእውነተኛው አምላክ ምስክሮች እንድንሆን ነው።
3) የእግዚአብሔር ተልዕኮ ለእኛ
ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ 1 ሳሙኤል 30፡1-> ፣ ዕብ. 3፡13፣ 1 ጴጥ. 5፡6፣ ዘሌ. 18፡15፣ ፊል. 2፡5-11፣ ሮሜ 1፡16፣ 1 ዮሐ. 1፡1፣
"እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!" በሚል ርዕስ በፓስተር አለማየሁ ሙልጌታ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
ርዕስ: እግዚአብሔር ለማዳን ሥራው ይፈልጋችኋል!
1) እግዚአብሔር ቀዳሚው አጀንዳው ሰዎችን ማዳን ነው/ መሳ. 3፣ 10፣ ኢሳ. 9፡6-7፣ ማቴ. 1፡20-21፣ ቲቶ 2፡10-11፣ ሮሜ 1፡16-17
2) ሰዎች ነፍሳቸው እንድትድንና ከክፋት እንዲጠበቁ እግዚአብሔር ይፈልጋል / ዮሐ. 17፡15
3) እግዚአብሔር በእኛ በኩል ሰዎችን ማዳን ይፈጋል
1) የዮሴፍ ታሪክ
2) የሶሪያዊው ንዕማን አገልጋይ ታሪክ
3) የአስቴር ታሪክ
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days