Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 080_ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ!

    "ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ" በሚል ርዕስ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር መልዕክት::

    የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል: /ሉቃ. 1:26-35/

    26 min
  • 079_ጨምሩ ክፍል 2

    ጨምሩ በሚል ርዕስ በ2 ጴጥ. 1 ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ቀጣይ ክፍል::

    32 min
  • 078_ጨምሩ ክፍል 1

    078_ጨምሩ ክፍል 1 በወንድም ያቬሎ ናታዬ

    በመንፈሳዊ ህይወት ለመጨመር መለኮታዊ ባህርይን መላበስ 2 ጴጥ 1:1-11 ላይ የተመሰረተ

    0.መግቢያ መጽሃፉና መልእክቱ

    1.እ/ርና የሰው መለኮታዊ ማንነት

    2.የተሰጠን የመለኮት ሃይልና ተስፋ ምንድናቸው::

    3.የመለኮቱ ሃይል እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነው ተስፋ ለምን ተሰጠን::

    4.የመለኮታዊ ባህርይና የመንፈሳዊ ህይወት መሰረቶች (1ኛ.የሰው ድርሻ እና 2ኛ. የእ/ር ድርሻ)

    53 min
  • 077_ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን?

    077_ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን

    ወንድም ዶ/ር ተከለ ማርቆስ  በእለቱ የቀረበ የእግዚአብሄር ቃል መልእክት:  ሁልጊዜ ጸልዩ የሚለውን ቃል ላይ በመመስረት "ለምንድነው ዘወትር መጸለይ የሚያስፈልገን?" ለሚለው ምላሽ ይሆን ዘንድ በአስር ዋና ዋና ነጥቦች ከፋፍሎ  የሚያስረዳ በትምህርት መልክ የቀረበ መልእክት:: ጥቅሶች በጥቂቱ . ከእ/ር ጋር ህብረት ለማድረግ መዝ 42:1,ጥበብን ለማግኘት ያእ1:5, ከክፋት ለመጠበቅ መዝ20:1,ከፍርሃት እና ከጭንቀት ለመወጣት ፊሊ 4:4, እና... መዝ 32:1,ሉቃ 22:40 ,ሮሜ10:14,ኤፌ 1:15 ሌሎችም

    52 min
  • 076_ጸሎት

    "ጸሎት የአምልኮ ዋና ክፍል" በሚል አሳብ ላይ ተመሥርቶ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    መልዕክቱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረውን ጸሎት መሠረት አድርጎ እኛም እንደ ክርስቶስ ተከታዮች ጸሎታችን ምላሽ ያለው እንዲሆን እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ያስረዳል::

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 21:22፣ 6:9-13/ሉቃ. 11:1-5/ዮሐ. 15:7/ያዕ. 4:3/ምሳ. 3:5

    1 hr 5 min
  • 075_የወንድሙ ጠባቂ ማን ነው?

    "የወንድሙ ጠባቂ ማን ነው? ቁምና ልብህን ፈትሽ ቅጥርህንም ጠብቅ!" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሐሳብ ልክ እንደ ቃየን የወንድሞቻችንን ክፋት (ሞት) የምንጠብቅ ሳንሆን ልክ እንደ ሙሴ እህት ወንድሞቻችንን ከክፋት (ከሞት) የምንጠብቅ እንድንሆንና በክርስቶስ የተሰጠንን አንድነትና ኅብረት አስበን በዓለም ውስጥ እንዳሉት የጥፋት መሣሪያ ላለመሆን ልባችንን እንድንጠብቅ ማሳሰብ ነው::

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ዘፍ. 4:1-10/1ቆሮ 1:9-10/ዘጸ. 2:1-10/ምሳ. 18:19-21

    46 min
  • 074_[ለታላቁ ተልዕኮ] ንቁ!

    "ንቁ" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምደ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሀሳብ ሰዎችን ከዘላለም ጥፋት ለማዳን ወንጌልን መመስከር የእያንዳንዱ አማኝ ደቀ መዝሙር ኃላፊነት መሆኑንና ለወንጌላዊያን ብቻ የሚተው ሥራ አለመሆኑን አጽንዖት ሰጥቶ መግለጽ ነው::

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ማቴ. 28:18-20/ሐዋ. 1:8/ማቴ. 13:24-30

    1 hr 19 min
  • 073_በውስጥህ/ሽ ወንዝ አለ!

    ማክሰኞ ምሽት (22.10.2019) "በውስጥህ/ሽ ወንዝ አለ!" በሚል ርዕስ በፓስተር ሰሎሞን አምዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    የመልዕክቱ ዋና ትኩረት ለኢየሱስ ክርስቶስ ህይወቱን የሰጠና መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ማንኛውም ሰው የሌሎችን ህይወት መለወጥ የሚችል እምቅ መንፈሳዊ አቅም (ወንዝ) በውስጡ እንዳለ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መተንተንና ማስገንዘብ ነው::

    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሕዝ. 47:1-12/ራዕ. 22:1-2/ዮሐ. 7:38

    1 hr 5 min
  • 072_ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል!

    "ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ "ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት ማውቅ ለምን  ያስፈልጋል?"  የሚል ሲሆን 1) ተዘጋጅቶ ለመኖር  2) ከጌታ የተሰጠንን አደራ በትጋት ለመፈጸም እንዲረዳን  እና 3) በህይወት ጎዳና መጽናኛችን ስለመሆኑ በመልዕክቱ በስፋት ተብራርቷል:: 

    የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ሐዋ 1:9-11/ ራዕይ 1:5-7፣ ራዕይ 22:12/ማቴ. 24:37-44, 45-51/ሉቃ. 12:35-40, 41-48/1 ተሰ. 4:13-18 

    42 min
  • 071_አምልኮ

    "አምልኮ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    54 min