Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀር... more
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.
August 03, 2026ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉልከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ ያለመ መሆኑ አላከራከረም። የህወሐት ዋና ፀሐፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ለትግራይ ወጣቶች «አሁን ብቻችን አይደለንም» ማለታቸዉ ግን ከቃል አቀባያቸዉ አባባል ጋር የሚጣረስ በተገላቢጦሹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይን ወቀሳ የሚያረጋግጥ ነዉ...more14minPlay
July 27, 2026ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮችየዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ የአፍሪቃ፣ የእስያና የአዉሮጳ የባሕር መስመር ሕልቅት ነዉ። በባሕር ከሚተላለፉ የዓለም ሸቀጦች ከ12 ከመቶ በላይ ይመላለስበታል።ከዓለም የኢንተርኔት መስመር 17 ከመቶዉ ተዘርግቶበታል።...more14minPlay
July 20, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያየአሜሪካ ዉሳኔ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔዎች ጋር መቃረኑ ዋሽግተኖች ለዉሳኔዉ የሰጡትን ምክንያት አጠያያቂ አድርጎታል።አጠያየቀም-አላጠያየቀ የአሜሪካ ዉሳኔ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎች እንደሚሉት 20 ዓመት ግድም ላስቆጠረዉ ለአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት ተልዕኮ የመጨረሻዉ መጀመሪያ ሊሆን ይችላል...more15minPlay
July 13, 2026የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል?የአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ ድርድር ለመግፋት ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አስፈልጓል።...more12minPlay
July 06, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን አያክልም።ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ሊግ ኦቭ ኔሽንስን አፍርሳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በሚጠቅማትና ዓላማዋን በሚያራምድ መልክ አደራጅታለች።...more16minPlay
June 29, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉዝግብ፣ የአረቦች ሥልትና የቀይ ባሕር መዘዝየዋሽግተንና የቴሕራን ቁርቁስ፣ በቴል አቪቭ-ቤይሩቶች ደባ ላይ ታክሎ እንጭጩን ሥምምነት እንድም ሆርሙዝ ሰርጥ አለያም ሜድትራኒያን ባሕር ዉስጥ እንዳያሰምጠዉ ሲፈራ-ሰሞኑን፣ ቀይ ባሕር መስመር የአዲስ ሽኩቻ-ሽሚያና ግጭት መድረክ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።አል ቁዱስ የተባለዉ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር (IRGC) ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጌድየር ጄኔራል እስማኢል ቃኒ ሐገራቸዉና ተባባሪዎችዋ አዲስ የፀጥታ መቀነት መዘርጋታቸዉን ሲናገሩ የሰማ እንጂ ያመናቸዉ ጥቂት ነበር።...more14minPlay
June 22, 2026ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።...more14minPlay
June 22, 2026ማሕደረ ዜና፣ የ7ኛዉ አጠቃላይ ምርጫ ዉጤት፣ እድምታዉና የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታከ5 ዓመት በፊት እንደሆነዉ ሁሉ በዘንድሮዉም ምርጫ ያሸነፈዉ ብልፅግና ፓርቲ ከትግራይ ክልል እስከ አዲስ አበባ ጠረፎች የሕዝብን ሕይወት፣ ኑሮና እንቅስቃሴ ለአደጋ ያጋለጠዉን የፀጥታ መታወክ፣ የፖለቲካ ዉዝግብ፣ ሕዝብ ያማረረዉን የኑሮ ዉድነት፣ የባለሥልጣናቱን ሙስናና የአስተዳደር እዉቀት ጉድለትን ካላሻሻለ የትናንቷ ኢትዮጵያ ዛሬ እንደሌሎች ሁሉ ዛሬ ያለችዉ ኢትዮጵያ ነገ መኖርዋ በርግጥ ያጠራጥራል።...more14minPlay
June 15, 2026ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ሥምምነት-የሠላም ጭላንጭል ብርቀትከዶናልድ ትራምፕ ጋር ሆነዉ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈቱት ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንኔታንያሁ በድርድሩ ሒደ,ት አልተሳተፉም ወይም ተገልለዋል።የእስራኤል የባር ኢላን ዩኒቨርስቲ የፖለካ ሳይቲስት ዮናታን ራይንሆልድ እንደሚሉት ሥምነቱ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ፖለቲካዊ ሕይወት መጥፎ ነዉ።ኔታንያሁ አሁን የሚመኙት ተንታኙ እንዳሉት ጦርነቱ እንዲቀጥል ነዉ።...more13minPlay
June 08, 2026ማሕደረ ዜና፣ የድርድር መሐል ጦርነት፣ የጦርነት መሐል ድርድር---ዜሮ ዉጤትበአሜሪካ አማላጅነት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ ሶስቴ ተኩስ እንዲቆም ከእስራኤል ጋር ተስማምቶ ነበር።ደቡባዊ ሊባኖስን የሚያወድመዉ የእስራኤል ጦር ድብደባ ወይም ጦርነት-ይባል ግጭት የመጫሩ ምክንያት በኢራን ላይ ጦርነት በመከፈቱ ከሆነ የኢራኑ ጦርነት ሲቆም የሊባኖሱ ያልቆመበት ምክንያት ከተጠየቀ-ትክለኛዉ መልስ «በጡንቻዉ የታበየን ማንጠይቆት» የሚል ነዉ-የሚሆነዉ።እንዲያዉ ለማለቱ ያክል ሒዝቦላሕና እስራኤል እየተዋጉ፣ የሒዝቦላሕ ጠላት እስራኤልና የሒዝቦላሕ ተቃዋሚ የቤይሩት መንግሥት፣ በሒዝቦላሕ ጠላት፣ በእስራኤል ጥብቅ ወዳጅ ዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት «ግጭትን ለማቆም» ተብዬዉን ስምምነት መዋዋላቸዉ---...more13minPlay
FAQs about ማሕደረ ዜና:How many episodes does ማሕደረ ዜና have?The podcast currently has 339 episodes available.