Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
November 23ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሙሉ ጦርነት ቢገቡ ምን ይገጥማቸዋል?ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሙሉ ጦርነት ቢገቡ ምን ይገጥማቸዋል?14 minPlay
November 16ማሕደረ ዜና፣ የሁቲዎች ድል፣ ያልተጠበቀዉ መራር ዕዉነትየዓለምን ሠላም ያስከብራል የተባለዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ከተፋላሚዎች አንዱን ምናልባትም የዓለም ገዢዎችን አገዛዝ የሚቃረነዉን ግን በኢራን የሚደገፈዉን አንሳር አላሕን ከመወንጀል-መቅጣት ባለፍ ጦርነት-ግጭቱን ለማስቆም እስካሁን የተከረዉ የለም14 minPlay
November 09ማሕደረ ዜና፣ የዲሞክራቶች ድል የትራምፕን መርሕ ይቀይር ይሆንትራምና ኔታንያሁ የጫሩት እሳትና አፀፋዉ ኢራንን፣ሊባኖስን፣የመንን፣እስራኤልን፣ ከኢራቅ እስከ ኩዌት የሚደርሱ የፋርስ ባሕረ ሠላጤ ሐገራትን ክፉኛ ጎድቷል።ኢራኖችን ግን ዛሬም አልተሸነፉም።ጥቅምት 29 ቀን 2026 እስራኤል፣ በአራተኛ ቀኑ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ በተደረገዉ ምርጫ ግን የኔታንያሁና የትራምፕ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሸንፈዋል።14 minPlay
November 02ማሕደረ ዜና፥ ኢትዮጵያ፣ ሸቀጥ የተወደደ፣ ሞት የረከሰባት ሐገርኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰዎች በጣሙን ለየዋሆች ሕይወት የሚጨነቅ አይደለም የሚያሳብ ፖለቲከኛ መገኘቱ እያጠራጠረ ነዉ።ወይም አስከሬን መቅበር፣ ተፈናቃይ መቁጠር፣ ለየጦርነት ግጭቱ «ጠላት» የሚባሉ ወገኖችን ማሳጣት፣ ሰበብ ምክንያት መደርደሩ ተለመደና አስጨናቂዉ ጥፋት የወትሮ ምግባር የሆነ ያክል ቀጠለ።14 minPlay
October 26የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት ውጥረት ውስጥ የገቡትን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ማገናኘት ይፈልጋልኃይለኛ ፍጥጫ ውስጥ ለገቡት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት በዚህ ሣምንት በሚካሔደው የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ የመገናኛ መድረክ መፍጠር ይፈልጋል። ግብጽ በቀይ ባሕር በኩል ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ግፊት እና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር ግንኙነት እንደማይኖራቸው አስታውቃለች።12 minPlay
October 19ማሕደረ ዜና፣ ቀይ ባሕር፤ በደም ቀልቶ ደም የሚገበርለት ባሕርኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ሐገር በነበሩበት ዘመን ይዋጉ ነበር።30 ዓመት። ሁለት ሐገርም ሆነዉ ይዋጋሉ።የአሥመራና የአዲስ አበባ መሪዎች ያልተዋጉበት ጊዜ ከነበረ-አንድም-በ1990ዎቹ እንዳየነዉ «የጋራ ጠላት» የሚሏቸዉን መንግሥትን ወይም በ2013 እንደሆነዉ የመቀሌ ገዢዎችን ለመዉጋት የተወዳጁበት-ሁለትም አንዱ የሌላዉን ጠላት የሚያደራጁበት ነበር።15 minPlay
October 12ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ?የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ ግልፅ ነዉ።15 minPlay
October 05ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏልከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም15 minPlay
September 28ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያ የጦርነት ማግሥት አዲስ ጦርነት መፍለቂያ ምድርጦርነት ሲጀመር «ተፋላሚዎች መጀመሪያ የሚገድሉት ዕዉነትን ነዉ» እንዲሉ ሆኖ የጦርነቱ ጀማሪ ማንነትን መለየት፣ እስካሁን የተገደለና የሞተዉን ሰዉ ቁጥር በዝርዝር ማወቅ አይቻልም።ተፋላሚ ኃይላት፣ ደጋፊዎቻዉ፣ መገናኛ ዘዴዎቻቸዉና በየፊናቸዉ ያደራጁት የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የፕሮፓጋንዳ ሠራዊ የሚነዙት የሐሰት መረጃ፣ስድብና ነቀፋም ቀጥሏል።16 minPlay
September 21ሑቲዎች እና ሳዑዲ አረቢያ የገጠሙት ጦርነት በደሐዋ የመን ሲቪሎችን ወደ ሰቆቃ እየገፋ ነውየአንሳር አላሕ ንቅናቄ ከጅቡቲ 20 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀውን ማዩን ወይም ፔሪም ደሴት እና ኤርትራ ከየመን የተዋጋችባቸው የሐኒሽ ደሴቶችን ጨምሮ ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ምዕራባዊ የመን ለመቆጣጠር የፈጀበት ሣምንት ገደማ ብቻ ነው። በውጊያው ቱርክ እና ፓኪስታን ሳዑዲ አረቢያን ለመደገፍ ፈቃደኛ ቢሆኑም አሜሪካ ለጊዜው ቸልተኛ ሆናለች።13 minPlay