Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

By DW.COM | Deutsche WelleEducation
Download on the App Store

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle episodes

  • Mission Berlin 24 – ሰዐቱ ይሮጣል
    አና በ 1961 ዓ ም የደበቀችውን የብረት ሳጥን መልሳ ታገኘዋለች። ስለዛገ ግን መክፈት ያቅታታል። ሲሳካላት ደግሞ ያረጀ ቁልፍ ታገኛለች። የሚስጥር ቁልፍ ይሆን?
    ሰዐቱ ይሮጣል። አና የብረት ሳጥኑን መክፈት አለባት። ተጫዋቹ ግን ሌላ ሰው ባለበት ማህሌቱን እንዳትከፍት ያስጠነቅቃታል። ሳጥኑ ውስጥ አሮጌና የዛገ ቁልፍ ታገኛለች። ቀይ ለባሿን ሴት ለማሸነፍ አሁን ቶሎ ብላ ወደ 2006 ዓ ም መመለስ አለባት። ለዚህ ግን በቂ ጊዜ ይቀራት ይሆን?
    5 min
  • Mission Berlin 25 – በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
    ሰዐቱ እየጠበበ ነው። አና ፓውልን መሰናበት አለባት ወደ ህዳር 9 2006 ዓ ም ለመመለስ። ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ይበቋት ይሆን?
    ተጫዋቹ አና ያለውን ግርግር ተጠቅማ እንድትጠፋ ይመክራታል። አና ግን ፓውልን ሳትሰናበት መጓዝ አትፈልግም። የጨዋታውን ውጤት ስትመዘግብ የዛገው ቁልፍ እንቆቅልሹን ለመፍታት የሚያስፈልጋት አንደኛው ቁልፍ እንደሆነ ትደርስበታለች። ሌላኛው ደግሞ ሙዚቃው ነው። ግን መጥፎውን ነገር እንዳይከሰት ለማድረግ በሰዐቷ ትደርስ ይሆን? ተልኮዋን ለማሳካት 5 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የሚቀሯት።
    5 min
  • Mission Berlin 26 – የጊዜ ተሞክሮ
    ወደ አሁን ስንመለስ አና ከፓውል ጋር የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር ለመዝጋት ትሞክራለች። ግን የሚስጥር ቁልፉ ይጠፋታል። አና ሙዚቃውን ትከተላለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ሀላፊዋ የ አናን እቅድ ግብ ከመግባቱ በፊት ታበላሽ ይሆን?
    አና ወደ ጥንት ትመለሳለች። ፓውልን የዛገውን ቁልፍ ታሳየዋለች የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዲቀረቅርበት። ግን ለዛ የሚስጥር ቁልፉ ያስፈልጋታል። እሱ ደሞ የላትም። አና የዳህፌግስን ስም በመስጠት ለመዝጋት ተሞክራለች። ባለቀ ሰዐት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ቁልፉን እንድትሰጣት ትጠይቃለች። አና ቁልፉን ማሽን ውስጥ ትከትና የሚስጥር ቁልፉን ትሰጣለች። ቀይ ለባሿ ሴት የድሮውን የሚያስታውሰውን ነገር እንዳይበላሽ ማድረግ ትችል ይሆን ወይስ እሷም እንደ ማሽኑ ታሪክ ሆና ትቀራለች?
    5 min
  • Mission Berlin 23 – እስከ በኋላ
    አና በሞተር ሳይክል ወደ በርንአወር መንገድ ትወሰዳለች። የሚወስዳት ሰው ኤምረ ኦጉር ይባላል። መልካም ጊዜ በበርሊን ይመኝላታል። ግን ከቀይ ለባሿ ሴት ለማምለጥና የብረቱን ሳጥን ለማግኘት ይበቃት ይሆን?
    ተጫዋቹ አና ጊዜ ስለሌላት ወደ በርንአወር መንገድ የሚወስዳት ሰው እንድትፈልግ ይመክራታል። አናን በሞተር ሳይክል አንድ ወጣት ሰውዬ ፤ የበኋላው መርማሪ ኤምረ ኦጉር ይወስዳታል። ከዚያም አና ሀይድሩንና ፓውልን ስታገኝ ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ፓውልና የሀይድሩን ባል ሊያባርሯት ይችላሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ አና ማህሌቱን ለማምጣት መንገድ ትጀምራለች። ግን ማህሌቱ ከብዙ አመታት በኋላ አሁንም እዚያው ይሆን ያለው?
    5 min
  • Mission Berlin 22 – እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጂ
    አና ወደ በርሊን 1989 ዓ ም ፤ በግንቡ መፍረስ የተነሳ ትልቅ ደስታ ወደሚታይበት ከተማ ትመለሳለች። በዚህ ግርግር ተጋፍታ ማህደሩን መውሰድ አለባት። ይሳካላት ይሆን?
    ልክ አና ወደ 1989 ዓ ም ልትጓዝ ስትል ጥቁር ኮፍያ የሚያደርጉት ብቅ ይላሉ። ቀይ ለባሿ ሴት አናን እንዲፈልጉ ትዕዛዝ ትሰጣለች። በህይወት እንዲያመጧት! አና ግን የድሮውን ነገር በሚያስታውሰውን ነገር በሰዐቷ የበርሊን ግንብ ወደ ፈረሰበት ቀን ትመለሳለች። የብራንድቡርገር በር ጋር ግርግር ውስጥ ቆማለች። ግን ወደ በርንአወር መንገድ መሄድ አለባት። 30 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው የቀሯት። ግን ከዚህ ግርግር በሰዐቷ ተከፋፍላ ከነበረችው ከተማ መውጣት ትችል ይሆን?
    5 min
  • Mission Berlin 21 – አዲሱ ዕቅድ
    አና ወደ 2006 ዓ ም ትመለሳለች። ቀይ ለባሿ ቄስ ካቫሊርን ትጠልፋለች። አና ቄሱ የት እንዳለ ስላላወቀች ወደ ህዳር 9 1989 ዓ ም ትጓዛለች።
    አና ወደ 2006 ዓ ም ስትመለስ ፓውል ቄሱ የት እንዳለ እንደማይታወቅ ይነግራታል። ፓውል የበለጠ ስለ ቄሱና የድሮውን ስለሚያስታውሰው ነገር ሳያውቅ አይቀርም። ግን ስለዚህ ለማውራት ጊዜ አይበቃም። አና ወደ ህዳር 9 1989 ዓ ም ምሽት ለመጓዝ ፍቃደኛ ነች። እዛም ስትደርስ በግንቡ መፍረስ የተነሳ በደስታ የምታከብር ከተማ ታገኛለች። በዚህ ግርግር ተደብቃ ማህደሩን ለመውሰድ ትሞክራለች።
    5 min
  • Mission Berlin 20 – ከጊዜ ወደ ጊዜ
    አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ አልደረሰችነትም። RATAVA የትኛውን ክስተት ሊያሰናክል ይፈልጋል? አና ወደ 2006 ዓ ም ከተመለሰች በኋላ ወደ 1989 መጓዝ አለባት። ግን ጉዞው ምን ያህል አደገኛ ነው?
    አና ወደ 2006 ዓ ም ከመመለሷ በፊት ከፓውል ጋር በደስታ ትሰናበታለች። 35 ደቂቃዎች ብቻ ናቸው አላማውን ለማሳካት የሚቀሯት? ተጫዋቹና አና አሁንም የእንቆቅልሹን መልስ ለማግኘት ይሞክራሉ። ለምሰሌ RATAVA የትኛውን ታሪካዊ ክስተት ሊያሰናክል እንደሚፈልግ። ወዲያው ሽብር ፈጣሪዎቹ የግንቡ ግንባታ ሳይሆን የግንቡን መፍረስ አንደሚፈልጉ ይደርሱበታል። ተጫዋቹ ወዲያው አና ወደ 1989 ዓ ም እንድትጓዝ ይወስናል። ግንቡ ሲፍረስ አና በቦታው እንድትገኝ።
    5 min
  • Mission Berlin 19 – ፍቅር በቀዝቃዛው ጦርነት
    የቀሩት 40 ደቂቃዎች ናቸው። አናና ፓውል ቀይ ለባሿን ሴት አምልጠው ምዕራብ ጀርመን ይገባሉ። ፓውል ነገሮቹን ግራ የሚያጋባ ያደርጋል። ከአና ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ዕድል ወይስ እንቅፋት?
    አና ተልኮዋን ለመወጣት ምስራቅ ጀርመን መግባት አለባት። ግን ምዕራብ ነው ያለችው። ሌላም ችግር አለ። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ፓውል ከሷ ፍቅር እንደያዘው ይነግራታል። ተልኮዋን እንድታቋርጥ ይፈልጋል። ተጫዋቹ ደግሞ ተመልሳ ወደ 2006 ዓ ም እንድትመለስ ይፈልጋል። በተጨማሪም አዲስ አላማ እንድታዘጋጅ ይፈልጋል። የቀሩት 35 ደቂቃዎች ይበቃቸው ይሆን አላማውን ለማሳካት?
    5 min
  • Mission Berlin 18 – የተደበቀው ማህደር
    አና ቀይ ለባሿ ሴት የ RATAVA ሀላፊ መሆኗን ትደርስነታለች። 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት። ለአና ወሳኝ ምንጭ አሁን ቀይ ለባሿ የደበቀችው ማህደር ነው። አና ከተደበቀበት ማውጣት ትችል ይሆን?
    ሀይድሩን ፓውልና አና ወደ በርንአወር መንገድ ሲሄዱ የሀይድሩን ባል ሮብርት ያገኙታል። እሱም ከተማው በሙሉ በወታደር እንደተሞላ ይነግራቸዋል። ከዛም በላይ የሚያስፈራው ግን ጥቁር ኮፍያ ያደረጉት ሞተር ሳይክል ነጂዎች ጉዞ መጀመራቸው ነው። ኣራቱም አንድ ቢራ የሚመረትነት ቤት ይደበቃሉ። ቀይ ለባሿ ሴት እዛ ብቅ ስትል ፓውል ለአና የ RATAVA ሀላፊ መሆኗን ይነግራታል። አናና ፓውል ይከታተሏታል። እሷም እንዴት ብላ አንድ የብረት ማህደር እምድር ቤት እንደምትደብቅ ያያሉ። እነሱም ይህንኑ ለመውሰድ ሲሉ ይረበሻሁ። ስለዚህ ማህደሩን ሌላ ቦታ መደበቅ አለባቸው። ተጫዋቹ እንዴት ብለው ማህደሩን በኋላ ሊወስዱ እንደሚችሉ ዘዴ አለኝ ይላል። ግን የቀሩት 40 ደቂቃዎች ይበቃቸው ይሆን?
    5 min
  • Mission Berlin 17 – የአጥር ግንባታ
    50 ደቂቃዋች ይቀራሉ። ተጫዋቹ ገንዘብ ተቀባይዋን ማመን እንደሚሻል በሙሉ ሀላፊነት ይወስናል። በሬድዮ ምስራቅ ጀርመን አጥሩ ጋር ስለቆሙ ወታደሮች ይወራል። ይኼ የ RATAVA መልስ ይሆን?
    አና እስካሁን ገነዘብ ተቀባይዋ ሀይድሩን ድራይ እንደሆነች አላወቀችም። ተጫዋቹ ለርዳታ ፍቃደኛ የሆነችውን ሴት ምንም እንኳን ወንድሟ ፓውል አጠራጣሪ ቢሆንም አና እንድታምናት ይመክራታል። ሆኖም እሱ አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን እንድታመልጥ እንደሚረዳ ፍቃደኛ ይሆናል። በኋላም አና ፤ፓውልና ሀይድሩን የምስራቅ ጀርመን ወታደሮች እንዴት የሚዋጋ ሽቦ መንገድ ላይ እንደሚያስቀምጡ ያያሉ። ተጫዋቹ አናን የግንብ ግንባታው ስራ ማስጀመሪያ እንደሆነ ይነግራታል። አና ጀርመንን ለማዳን 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት።
    5 min

About Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

From the publisher's feed

Mission Europe ለጀማሪዎች የተዘጋጀ የቋንቋ ትምህርት ሲሆን ፦ Mission Berlin ፦ Misja Kraków እና Mission Paris የሚሰኙትን ልብ ሰቃይ ወንጀል ነክ ታሪኮችን አካቶዋል። ወደ ቋንቋው ዓለም በመዝለቀ የፖላንድኛ፣የ ጀርመንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ይማሩ።