Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

By DW.COM | Deutsche WelleEducation
Download on the App Store

Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle episodes

  • Mission Berlin 05 – አንተዋወቅም?
    አና የመጫወቻ ቀፎውን ለማስጠገን ሰዐት ሰሪ ጋር ትመጣለች። ለፓውል ቪንክለር ግን ነገሩ ከጥገና ትዛዝ በላይ ነው።
    ፓውል ቪንክለር የመጫወቻ ቀፎውን ሲከፍት ውስጡ አንድ ወረቀት ላይ የቁጥር ቁልፍ 19610813 ያገኛል። ምን ማለት ነው? ፓውል ቪንክለር ስለ ምንድን ነው የሚያወራው? አና የመጫወቻ ቀፎውን ልጠግንልህ ትላለች። እሱ ደግሞ ከዚህ በፊት እንደሚተዋወቁ ይገምታል። በመካከልም አና ጨዋታውን መዝግባ ታስቀምጣለች። ከአሁን በኋላ 90 ደቂቃዎችና ሁለት ህይወት አሏት። ሙዚቃውን ተከትላለች ግን "In der Teilung liegt die Lösung" ምን ማለት ነው?
    5 min
  • Mission Berlin 04 – ማስጠንቀቂያዎች
    አና የካንት መንገድ ላይ አንድ የተዘጋ የሰዐት መሸጫ ታገኛለች። የሱቁ ባለቤት አንድ ካፍቴሪያ እንደተቀመጠ ትሰማለች። ሁለቱም ሳይተዋወቁ አይቀሩም። አና 100 ደቂቃዎች ብቻ ነው ያሏት። ጊዜው ይበቃት ይሆን?
    አና ሊዮ ቪንክለር በህይወት እንዳለ ትሰማለች። አንድ የፊልሙ ውስጥ የሚሰማውን ሙዚቃ የሚጫወተው ተጫዋች የሱቁ ባለቤት የ ሊዮ ቪንክለር ልጅ ፓውል እንደሆነ ይነግራታል። በቅርብ በሚገኘው ካፍቴሪያ በየቀኑ ቸኮላት ይጠጣል። አናም ወደዚያ ትሄድና ቡና ታዛለች። ካፍቴሪያ የተቀመጠ አንድ የብር ቀለም ያለው ቫይሊን ያነገተ ሰውዬ ሳቅ ይልላታል። መርማሪ ኦጉር ብቅ ይልና አናን ተልዕኮዋ አደገኛ እንደሆነ ይነግራታል። የ RATAVA ማህበር ጨምሮ። አና በጉጉት የብር ቀለም ያለው ቫይሊን ያነገተውን ትልቅ ሰውዬ ትከታተላለች።
    5 min
  • Mission Berlin 03 – ወደ ካንት መንገድ አቅጣጫ
    አና ወደ ካንት መንገድ አቅጣጫ ታመራለች። መንገድ መጠየቅ ስላለባት ሰአቷ ይባክናል። ጥቁር ኮፍያ ያደረጉ ሞተር ሳልክል ነጂዎች ይደርሱባትና ይተኩሳሉ።
    ሞተር ሳልክለኞቹ አናን ፋታ አይሰጧትም። በተልዕኮዋ ላይ በተጨማሪም ይረፍድባታል። ተሽከርካሪ ጎማ ያለው ጫማ የሚሄዱትን ልጆች መንገድ ስትጠይቅ ሞተር ሳልክለኞቹ ተኩሰው ይገድሏታል። ጨዋታው በድጋሚ ከተጀመረ በኋላ በመጨረሻ ካንት መንገድ ላይ ትደርሳለች። ግን እዚያ የምትፈልገውን ታገኝ ይሆን?
    5 min
  • Mission Berlin 02 – በማምለጥ ላይ
    አና የመርማሪውን ጥያቄ እየመለሰች ሳለ የሞተር ሳይክል ድምፅና ተኩስ ይከፈታል። አና ትጠፋለች።የመጫወቻ ቀፎ ላይ አንድ አድራሻ ታገኛለች። ይኼ እሷን ይረዳት ይሆን?
    አና ከአባራሪዎቿ ወደ አንድ ሙዜም ማምለጫ አጋጣሚ ታገኛለች። ፓሊሶች ወይም ጥቁር ኮፊያ ያደረጉ ታጣቂ ሞተር ሳይክል ነጂዎች እንዳያገኝዋት ስለፈራች የወንዶች መፀዳጫ ቤት ትደበቃለች።
    5 min
  • Mission Berlin 01 – ተንኮል የተሞላነት ቅስቀሳ
    የአና ተልኮ ጀረመንን ከአደጋ መጠበቅ ነው። እሷም እንቆቅልሹን መፍታትና እራሷን ሞተር ሳይክል ከሚነዱት ወንዶች መጠበቅ አለባት።ለዚህም 130 ደቂቃዎች አሏት። ግን የመጀመሪያዋ ምንጭ የታለ?
    አና በክፍል 14 የአንድ የጀርመን ሆቴል ከእንቅልፏ ትነቃለች። አንድ የወንጀል ተመራማሪ ወደ ክፍሏ እያመራ ነው። መርማሪ ኦጉር እራሱን ያስተዋውቅና የክፍል ቁጥር 40 አንድ የሆቴል እንግዳ መገደሉን ይገልፃል። የመታጠቢያ ቤቷ መስታወት ላይም: "In der Teilung liegt die Lösung; folge der Musik". የሚል መልዕክት ተፅፎ ያገኛል። አና መርማሪውን ወደ ሆቴሉ አዳራሽ ለጥያቄና መልስ ትከተለዋለች። ግን አና እክፍሏ ያገኘችው አሮጌ የመጫወቻ ቀፎና ይሄ ግራ የሚያጋባ መልዕክት ምንድን ነው?
    5 min

About Mission Europe – Mission Berlin | ጀርመንኛ መማር | Deutsche Welle

From the publisher's feed

Mission Europe ለጀማሪዎች የተዘጋጀ የቋንቋ ትምህርት ሲሆን ፦ Mission Berlin ፦ Misja Kraków እና Mission Paris የሚሰኙትን ልብ ሰቃይ ወንጀል ነክ ታሪኮችን አካቶዋል። ወደ ቋንቋው ዓለም በመዝለቀ የፖላንድኛ፣የ ጀርመንኛ ወይም የፈረንሳይኛ ቋንቋ ይማሩ።