Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle

Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle

By DW.COM | Deutsche WelleEducation
Download on the App Store

Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle episodes

  • Mission Berlin 17 – የአጥር ግንባታ
    50 ደቂቃዋች ይቀራሉ። ተጫዋቹ ገንዘብ ተቀባይዋን ማመን እንደሚሻል በሙሉ ሀላፊነት ይወስናል። በሬድዮ ምስራቅ ጀርመን አጥሩ ጋር ስለቆሙ ወታደሮች ይወራል። ይኼ የ RATAVA መልስ ይሆን?
    አና እስካሁን ገነዘብ ተቀባይዋ ሀይድሩን ድራይ እንደሆነች አላወቀችም። ተጫዋቹ ለርዳታ ፍቃደኛ የሆነችውን ሴት ምንም እንኳን ወንድሟ ፓውል አጠራጣሪ ቢሆንም አና እንድታምናት ይመክራታል። ሆኖም እሱ አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን እንድታመልጥ እንደሚረዳ ፍቃደኛ ይሆናል። በኋላም አና ፤ፓውልና ሀይድሩን የምስራቅ ጀርመን ወታደሮች እንዴት የሚዋጋ ሽቦ መንገድ ላይ እንደሚያስቀምጡ ያያሉ። ተጫዋቹ አናን የግንብ ግንባታው ስራ ማስጀመሪያ እንደሆነ ይነግራታል። አና ጀርመንን ለማዳን 45 ደቂቃዋች ብቻ ናቸው የቀሯት።
    5 min
  • Mission Berlin 16 – የድሮ ጓደኛ
    በ 1961 ኛው ዓ ም አናን የታጠቁት ሞተር ሳይክል ነጂዋች ያባርሯታል። በዚህ አስፈሪ ጊዜ አንዲት የማትታወቅ ሴት ትረዳታለች። ግን ለምን ትረዳታለች? አናስ ልታምናት ይገባል?
    ሞተር ሳይክል ነጂዎቹ አናን ይከታተሏታል። እሷም ወደ ምግብ መሸጫ መደብር እሸሻለች። የሱቁ አለቃ እየዘጋ እንደሆነ ሲነግራት አንዷ ተቀጣሪ አና ጓደኛዬ ነች ትላለች። ገነዘብ ተቀባይዋ አናን ወደ ቤቷ ትወስድና የ ት/ ቤት ጓደኛዋ ነኝ ትላለች። አና ትጠራጠራለች ግን ተጫዋቹ አና ሴትዬዋን ማመን እንዳለባት ይነግራታል። አና የ ገነዘብ ተቀባይዋ ቤት የሴትየዋን ወንድም ፓውል ቪንክለር ትተዋወቃለች።
    5 min
  • Mission Berlin 15 – የጊዜ ጉዞ
    አና ከተከፈለችው ምስራቅ በርሊን ወደ ምዕራብ በርሊን መመለስ አለባት። ግን ይህ ብቻ አይደለም። በ 55 ደቂቃዎች ውስጥ RATAVA ምን እንደሆነ ጭምር፤ የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርስ?
    አና 1961 ኛው ዓ ም እንደደረሰች ወደ ካንት መንገድ ለመሄድ ትሞክራለች። ይህ ግን ሊሳካ አይችልም። ምክንያቱም የDDR መንግስት የግንብ ግንባታውን ስለጀመረና አና ደግሞ በምስራቁ በኩል ስላለች። ግን የካንት መንገድ ምዕራብ በርሊን ነው የሚገኘው። ጨዋታውን እንደ አዲስ ካደሱ በኋላ አናና ተጫዋቹ ሁለት ታሪካዊ ክስተቶች ያገኛሉ፦ የ RATAVA አላማ ሊሆን የሚችሉ። የበርሊን ግንብ ምስረታ ወይስ ፍርሰት። ተጫዋቹና አና ይህንን ለማወቅ 55 ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚቀራቸው።
    5 min
  • Mission Berlin 13 – የእግዚያብሄር እርዳታ
    ቤተ ክርስትያኒትቱ መረጃ ለመሰብሰብ ትክክለኛ ቦታ ሳትሆን አትቀርም። ቄሱ ለአና የሙዚቃው ቅንብር የድሮውን ነገር የሚያስታውስ ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል።ግን ምን አይነት መሳሪያ ማለቱ ነው?
    ጨዋታው እንደ አዲስ ከተጀመረ በኋላ አና ከቀይ ለባሿ ሴት ታመልጣለች። ቄሱ ለአና መርማሪ ኦጉር እንደቆሰለና ሆስፒታል እንደተኛ ይነግራታል። ለአናም የሙዚቃውን ቅንብር በድጋሚ ያሰማትና የሙዚቃው ኖት አደራደር D A C H F E G የድሮውን ነገር የሚያስታውሰን ቁልፍ እንደሆነ ያብራራላታል። ይኼ ድል ለተጫዋቹና ለአና የአስር ደቂቃዎች ሽልማት ያስገኛቸዋል። ግን ጊዜው ይበቃቸው ይሆን?
    5 min
  • Mission Berlin 12 – የ ቤተ ክርስትያን መዝሙር
    አና 65 ደቂቃዎች ይቀሯታል። የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ትደርስበታለች። ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ከአና ቁልፍ ትጠይቃለች። ግን ምን አይነት ቁልፍ?
    የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን ከመጫወቻው ቀፎ ጋር አንድ አይነት የሙዚቃ ቅንብር ይጫወታል። አና ቀረብ ብላ የቤተክርስትያን አገልጋዩ ለጎብኝዎች የሚለውን ታዳምጣለች። ኦርጋኑ መታደሱን፤ የበርሊኑ ግንብ ከተሰራ በኋላ ግን ኦርጋኑ አንድ አካል እንደሚጎለው ይናገራል። አና የመጫወቻው ቀፎ የቤተ ክርስትያኑ ኦርጋን አካል መሆኑን ይገባታል። ኦርጋኑ መጫወት ሲጀምር አንድ በር ይከፈትና ቀይ ለባሿ ሴት ፊት ለፊቷ ትቆማለች። አና አንዱን ህይወቷን ታጣለች። የቀራትም 60 ደቂቃዎች ብቻ ነው።
    5 min
  • Mission Berlin 11 – ፈጣን ምግብ
    አና ምግብ ከፓውል ጋር እየበላች ስለሚገርመው አረፍተ ነገር ፤ "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ታወራለች። እሱም አደጋውን ያውቅና ወደ ቄስ ካቫሊር ጋር ይልካታል። ግን ይኼ ትክክለኛው መንገድ ነው?
    ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ጠግኗል። ግን የሙዚቃውን ቅንብር እስከ መጨረሻው ለማጫወት አንድ ነገር ይጎለዋል። አና ስለሚያስደንቀው መልዕክት ትነግረዋለች "In der Teilung liegt die Lösung. Folge der Musik!" ፓውል የመጫወቻ ቀፎውን ይሰጣትና ወደ ቄስ ማርኮስ ካቫሊር ጋር ጌትሰማኔ- ቤተ ክርስትያን ይልካታል። ተጫዋቹ ይኼ ቤተ ክርስትያን የምስራቅ ጀርመን (DDR) መንግስት ተቃዋሚዎች መገናኛ ቦታ እንደነበር ለአና ይነግራታል።
    5 min
  • Mission Berlin 10 – መውጫ የሌለው መንገድ
    ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተሰራበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ይደርስበታል። የአና ተልኮ ከነዚህ ቀናቶች ጋር የተያያዘ ነው። አና ምን ማድረግ ትችላለች?
    ፓውልና አና ካድቬ ወደሚባል ገበያ አዳራሽ ከቀይ ለባሿ ሴት እየሸሹ ነው። የገበያ አዳራሹ አና የጨዋታዋን ውጤት የምታስቀምጥበት ቦታ ነው። ተጫዋቹ እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 የበርሊኑ ግንብ የተመሰረተበት ቀን እንደሆነና ህዳር 9 ደግሞ ግንቡ የፈረሰበት ቀን እንደሆነ ለአና ያብራራል። አና የተልኮዋ ሙሉ መልስ ከበርሊን መገንጠል ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይገባታል።
    5 min
  • Mission Berlin 09 – ያልተሟላ ጥቆማ
    አና ከቲያትር ቤቱ ትጠፋለች። ግን ቀይ ለባሿ ሴት የፓውል ሱቅ እስከምትገባ ድረስ ትከታተላለች። በሀይድሩን እርዳታ አማካኝነት አና ማምለጥ ትችላለች። እንቆቅልሹን ለመፍታት ሙሉ መረጃ የላትም። የተቀረውን ከየት ታገኝ ይሆን?
    መርማሪ ኦጉር አናን ከጊዜው ሽብር ፈጣሪዎች ፤ RATAVA እንድትጠነቀቅ ይነግራታል። ወደ ሰዐት መሸጫው ስንመለስ፤ ፓውል ቪንክለር የተጠገነውን የመጫወቻ ቀፎ ያሳያታል። የ ፍሪድሪክ ኦጉስት ዳህፌግ "Nostalgie" የሙዚቃ ቅንብር ትጫወታለች። "Unsere Melodie, Anna", ይላል ፓውል። ግን አና ምንም አይገባትም። በድንገት ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትልና ተኩስ ትከፍታለች። ሀይድሩን ድራይ በቦታው ትገኝና ፓውልና አና ማምለጥ እንዲችሉ ታደርጋለች። አና አሁን ሁለት መረጃ ነጥቦች አግኝታለች። እ ኤ አ ነሐሴ 13 1961 እና ህዳር 9። ግን የትኛው አመት ነው?
    5 min
  • Mission Berlin 02 – በማምለጥ ላይ
    አና የመርማሪውን ጥያቄ እየመለሰች ሳለ የሞተር ሳይክል ድምፅና ተኩስ ይከፈታል። አና ትጠፋለች።የመጫወቻ ቀፎ ላይ አንድ አድራሻ ታገኛለች። ይኼ እሷን ይረዳት ይሆን?
    አና ከአባራሪዎቿ ወደ አንድ ሙዜም ማምለጫ አጋጣሚ ታገኛለች። ፓሊሶች ወይም ጥቁር ኮፊያ ያደረጉ ታጣቂ ሞተር ሳይክል ነጂዎች እንዳያገኝዋት ስለፈራች የወንዶች መፀዳጫ ቤት ትደበቃለች።
    5 min
  • Mission Berlin 07 – የማይታወቀው ጠላት
    አና ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ወደ ቫሪቴ ቲያትር ቤት ሄዳ ታመልጣለች። እዛም ሀይድሩንንና መርማሪ ኦጉርን ታገኛለች። እሱም RATAVA እያሳደዷት እንደሆነ ይነግራታል። ግን RATAVA እና ቀይ ለባሿ ሴት ከአና ምንድን ነው የሚፈልጉት?
    ተጫዋቹ አና ወደ ፓውል ቪንክለር ሱቅ ሄዳ የመጫወቻ ቀፎውን ይዛ እንድትመጣ ያዛታል። ወደእዛ ስትሄድ ሞተር ሳይክል ነጂዎቹን ታመልጣለች። ቲያትር ቤት ሀይድሩን ድራይ ን በድጋሚ ታገኛታለች። መርማሪ ኦጉርም እዛ ብቅ ይልና ሀይድሩን አና የት እንዳለች ይጠይቃል። አና ቲያትር ቤቱ እንደተደበቀች ይጠራጠርና RATAVA እየተከታተሏት ስለሆነ እንድትጠነቀቅ ይላል። ወዲያው ቀይ ለባሿ ሴት ብቅ ትላለች። ከአና ምንድን ነው የምትፈልገው?
    5 min

About Mission Europe - Mission Berlin | Учить немецкий | Deutsche Welle

From the publisher's feed

Mission Europe - это языковой курс для начинающих. В него входят детективные истории Mission Berlin, Misja Kraków и Mission Paris. Окунитесь в мир немецкого, польского или французского языков!