የእግዚአብሔር ፍትሀዊነት: Is God A fair and Just God?
ሰላም እንዴት ናችሁ? በዚህ በሁለተኛው Podcast የፌሎሽፓችን አባል ከሆነችው ከእህታችን ቃልኪዳን ጋር የእግዚአብሔርን ፍትሀዊነት በተመለከተ ውይይት አድርገናል፤ በዚህ ውይይትም የሚከተሉትን ጥያቄዎች መነሻ አድርገን ተወያይተናል፤
¶እግዚአብሔር ፍትሀዊ ነዉ ማለት ምን ማለት ነው?
¶መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ለእ/ር ፍትሀዊ መሆን ምሳሌ የሆኑ ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?
¶በህይወታችን ለምን መጥፎ ነገር ይገጥመናል?
¶እግዚአብሔር ደስ የሚለንን ነገር ብቻ ለምን አያደርግልንም?
-እ/ር የአብርሃምን እምነት ለማየት ልጁን ሠዋ ማለቱ Fair ነው?
-አብርሀምን ተስፋ ከሠጠው በኋላ 25 አመት ዝም ማለቱ ልክ ነው?
-ለዬሴፍ ህልም አሳይቶት ለ13 አመት ዝም ማለቱስ?
-ሙሴ እና እስራኤላውያን ቃል ከተገባላቸው በኋላ 40 አመት ለምን ባከኑ?
-ሙሴ 40 አመት ከመራ በኋላስ የተስፋዋን ምድር አትወርስም መባሉስ?
-እዮብ ላይ መጨከኑስ? ለ32 ምዕራፍ ዝም ማለቱ?
¶ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች ስለ እ/ር ፍትሀዊነት ምን ይነግሩናል?