''የሩሲያዊያን ስነፅሁፎች ጭፍን ጥላቻን አያንፀባርቁም፤ ይልቁን የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንፀባርቁ ናቸው - ከታላላቅ ፀሃፊዎች መካከል የአንቶን ቼክሆቭ ሥራዎች በዓለም ላይ ምርጥ 50 ተውኔቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። በዚህም በሥራዎቹ በትልቅ ደረጃ የሚገለፅ ነው - ሲል'' ከቼክሆቭ ሥራዎች ውስጥ አራቱን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎመው ተዋናይ ሳምሶን ብሬ ለግሃር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድቷል።
በመጀመሪያው የፕሮግራሙ ክፍል የታላላቅ ራሺያውያን ፀሃፊዎችን ዘመን ተሻጋሪ አሻራን መሠረት በማድረግ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ ያሉ ታላላቅ የስነ ፅሁፍ ሰብዕናዎችን ከተርጓሚ፣ ተዋናይና በጥብቅና ሙያ ላይ ከሚገኘው ሳምሶን ብሬ ለግሃር ጋር እንዳስሳለን።