Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና ... more
FAQs about The Rising South:How many episodes does The Rising South have?The podcast currently has 102 episodes available.
July 29, 2025የምግብ ቅኝ ግዛት እና የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ፍልሚያ"የውጭ ኩባንያዎች እና የውጭ መንግስታት በዘረመል የተሻሻሉ ሰብሎችን በዋናነት ይቆጣጠራሉ። በእነሱ ቁጥጥር ስር ናቸው። ምናልባት በነጻ ይሰጡናል ማለት ትችል ይሆናል። አንዴ መጠቀም ከጀመርክ በኋላ ግን፣ በብዙ ሌሎች ሀገራት ዘንድ እንዳየነው፣ የእነዚህ ሰብሎች ምርታማነት ይቀንሳል፣ በአካባቢያዊ ስነ-ምህዳር፣ በነፍሳት፣ እንስሳት እና በሌሎችም ይጠቃሉ። [...] የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች በአፍሪካ ድህነትን አልቀነሱም፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን አላጠፉም፣ የገበሬዎችንም ገቢ አልጨመሩም። ያደረጉት ነገር በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ወሳኝ፣ ወሳኝ ምግቦችን መተካት ወይም መቀነስ ነው።”በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ህብረት /AFSA/ ዋና አስተባባሪ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል ፤ ዉይይትም እናደርጋለን።የሚመረቱ፣ የሚበስሉ እና ከምንመገበውም ምግብ ጀርባ ያለ ድብቅ ፖለቲካም እንፈትሻለን።...more1h 0minPlay
July 25, 2025ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ“አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነቱ ትልቅ ዕድል አለው። በ2045 የአፍሪካን ንግድ በ45 በመቶ ገደማ ማለትም በ275.7 ቢሊዮን ዶላር ይጨምራል […] እንዲሁም የአፍሪካ አገሮች የግብርና ምርቶችን ወደ ውጭ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲልኩ ይረዳቸዋል።”በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ ከሆኑት አበበ አምባቸዉ (ዶ/ር) ጋር በመሆን የታሪፍ ቅነሳን በማስወገድ እና የኢንዱስትሪ እድገትን በማበረታታት የአህጉሪቱን የንግድና ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ስለሚያሳድገው የዓለም ትልቁ የነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ ተወያይተናል ፤ የኢትዮጵያን የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅቶችንም ዳስሰል።...more30minPlay
July 23, 2025የጤፍ ባለቤትነት፦ የኢትዮጵያ ትግል ከብዝሃ-ህይወት ሃብት ዘረፋ ጋርየአፍሪካ ሼፎች ጉባኤ እና የሥርዓተ ምግብ የፖሊሲ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፤ ጉባዔው ማጠንጠኛ ካደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ የምግብ ሉዓላዊነት ይገኝበታል፡፡ ይህን ከሚፈታተኑ ተግባራት ውስጥም በምዕራቡ ዓለም ኩባንያዎች የሚፈጸሙ የ'ባዮፓይሬሲ' ወይም የብዝሃ- ህይወት ሃብት ዘረፋ አንዱ ነው፡፡ “የብዝሀ ሕይወት ዘረፋ 'ባዮፓይሬሲ' ለደቡባዊ ዓለም ሀገራት አሳሳቢ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በተፈጥሮ የአዝርዕት ዘረመል ሀብት የበለፀጉ ናቸው። የሰሜኑ ዓለም ሀገራት ኩባንያ ባለቤቶች ግን እነዚህን የአዝርዕት ዘረመል ሀብቶችን ለመጠቀም [በራሳቸው ስም ለማስመዝገብ] ፍቃድ እየጠየቁ ነው። […] የአዝርዕት ሉዓላዊነት በጣም ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱም የተለያዩ ዘሮች በእጃቸው ከሌሉ የምግብ ዋስትና አይኖርም።”በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት አቅራቢው ኢትዮጵያ ጤፍ ላይ የተፈፀመባትን የባለቤትነት ዘረፋ መነሻ አድርጎ የተፈጥሮ ሃብት ዘረፋ የ'ባዮፓይሬሲ'ን ዓለም አቀፍ ኢፍትሃዊነት በሰፊው ይዳስሳል፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶች እና የአግሮኢኮሎጂ ኮንሰርቲየም ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
July 22, 2025የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ቴክኖሎጂ እና የአፈር ማዳበሪያ ምርት፦ የኢትዮጵያ ልዕልና ሰንሰለቶችየሉዓላዊነት ትርጉም ከድንበር ያለፈ ነው። “የአፍሪካ ሉዓላዊነት መከበር አለበት — ድሃ ሀገር መሆን ሉዓላዊነትን አይቀንስም።” ሙሉጌታ ደበበ (ዶ/ር) በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምዓቀፍ ግንኙነት መምህር፡፡በዚህ The Rising South የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅትም የኢትዮጵያን የልዕልና እና የሉዓላዊነት ሰንሰለቶች የምንችላቸውን ከህዳሴ ግድብ እስከ ቴክኖሎጂያዊ የፈጠራ መንገዶች ደግሞም በምግብ ራስን ለመቻል መሰረት እስከሆነው የአፈር ማዳበሪያ ምርት ውጥን በጥልቀት እናያለን። የሳይበር ደህንነት ባለሙያዉ ፋሪስ ሙባረክ እና የግብርና ተመራማሪዉን ሲሳይ ሃይሉም ዕይታቸውን አጋርተውናል፡፡...more1h 0minPlay
July 18, 2025የኢትዮጵያ ፋሽን ፈተና፦ ያገለገሉ ልብሶች /ቦንዳ/ ገበያየኢትዮጵያ የፋሽን ኢንደስትሪ ፈተና መልኩ እንዲህ ነው “ድሮ የቦንዳ ልብሶችን ሰው ተሸማቆ ነበር የሚገዛው [...] አሁን ግን ትልልቅ ሞሎች ላይ የቦንዳ ልብሶች ይሸጣሉ።” ስትል ዲዛይነር ኢክራም መሐመድ ነግራናለች። ከዚህ መውጫው መንገድ ደግሞ የህንድ ምሳሌ ነው። "የኢትዮያ ታምርት ፅንሰ ሃሳብን ማስረፅና በኢትዮጵያ ምርት የምንኮራበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት፣” ሲል በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ፋሽንና ጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲትዩ አፓረል ዲን ቢኒያም...more1h 0minPlay
July 16, 2025የአፍሪካን ዕጣፈንታ መገንባት፦ የህዝብ አገልግሎት — በሀገር በቀል ፈጠራ እና ትብብርዛሬ በናይሮቢ በተካሄደው 'የስማርት ገቨርንመንት' ጉባኤ የአፍሪካ ዲጂታል ሉዓላዊነት በዋናነት ተነስቷል — የህዝብ አግልግሎትን በእምነት፣ ግልጽነት እና ለዜጋ ቅድሚ በሰጠ ፈጠራ መምራት የሚለው ሀሳብም በሰፊው ተዳስሷል።ዘንድሮ በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 21 — ሰኔ 23 የተከበረው በ10ኛው የአፍሪካ የህዝብ አገልግሎት ቀን ከአዲስ አበባ እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ የአፍሪካ ሀገራት በአገር ውስጥ ፈጠራ፣ ፍትሃዊነት እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር የህዝብ አገልግሎትን መቀየር ላይ ትኩረት የሰጡበት ሆኗል።...more30minPlay
July 15, 2025የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲሱ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ማንነትን ለመጠበቅ የሚደረገው ትግልዛሬ በጎርጎሮሳዊያኑ ሐምሌ 15፣ በዓለም የወጣቶች ክህሎት ቀን ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እያንዳንዱ ኢንቨስትመንት የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራን ለማስቀደም ያስችላል የሚለውን ስርዓት አስተዋውቋል። ባንኩ የ10 ዓመት ስትራቴጂ አካል የሆነ የወጣቶች የስራና ክህሎት 'ማርከር' ስርዓትን ከዓለም የስራ ድርጅት ጋር በመሆን ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ የመጣው ባንኩ ሲዲ ኡልድ ታህን (ዶ/ር) ዘጠነኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ ከመረጠ በኋላ የሆነ ነው። እንዲህ ያሉ የአፍረካ ለውጦችን ዕውን ለማድረግ የአፍሪካ ማንነትን መጠበቅና የወደፊት ትውልድን ማብቃት አስቸኳይ እንደሆነ ባለሙያዎች አጽንኦት ሰጥተዉ ይናገራሉ።...more1h 0minPlay
July 11, 2025"የሌማት ትሩፋት"፦ የኢትዮጵያ የውስጥ አቅምና ዕውቀት ለምግብ ሉዓላዊነትእ.ኤ.አ በ2022 የተጀመረው የሌማት ትሩፋት፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት ለመቀየር መንግስት ከፍተኛ ትኩረት የሰጠው ኢኒቬቲቭ ነው። ኢኒሼቲቩ የወተት፣ የዶሮ እርባታ፣ የማርና የአሳ ምርትን እያሳደገ፣ አምራቾችን እያበረታታ እንዲሁም እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱን ምግብ እንዲያመርት፣ በአካባቢ ገበያዎች እንዲሳተፍ እያደረገ ስለመሆኑም ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ዉጥን ከግብ ለማድረስም አጋዥ ነው ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።...more30minPlay
July 10, 2025አፍሪካ የቱሪዝም አቅምን መክፈት፡- ዕድሎችን ማሰስ እና እንቅፋቶችን ማለፍአፍሪካ አስደናቂ መልክዓ ምድር፣ የበለጸገ ባህል እና በፍጥነት እያደገ ያለው የዲጂታል ገጽታ በዓለም ቱሪዝም ውስጥ ያንቀላፋው ዘርፍ አድርጎት ቆይቷል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ክፍል፣ ስለዚሁ የአፍሪካ ያልተነካው ዘርፍ በስፋት እንዳስሳለን፡፡ይህንን ያልተነካ እምቅ ሀብትም ከታላቅ ኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር መስራች ናሆም አድማሱ ጋር በመሆን እንመረምራለን።ከሥነ-ምህዳር ቱሪዝም እስከ ጂኦፓርኮች፣ አፍሪካ ለውጥ የመፈጠር መንገድ ላይ ነች — ነገር ግን እንቅፋቶችም አሉ፤ በቅጡ ያልለሙ መሠረተ ልማቶች፣ የደህንነት ስጋቶች እና በቂ ያለሆነው ኢንቨስትመንት ዘርፎን ወደኋላ ጎትተው ይዘዉታል።...more1h 0minPlay
July 08, 2025የብሪክስ ሪዮ መግለጫ፦ ተጨባጭ የኃይል ሽግግርበብራዚሏ መዲና ሪዮ ዴ ጄኔሮ የተካሄደው የ2025 የብሪክስ ጉባኤ ለደቡባዊው ዓለም ትልቅ ለውጥ ያመጣል። የብሪክስ ሀገራት የፋይናንስ ነፃነትን፣ የተባበሩት መንግስታት ማሻሻያን እና የቴክኖሎጂ ማካተትን የሚጠይቅ 126 ነጥቦችን የያዘ ሰፊ መግለጫ በማውጣት የዓለምን ሥርዓት በመቀየር ላይ መንገዳቸው ቀጥለዋል።...more1h 0minPlay
FAQs about The Rising South:How many episodes does The Rising South have?The podcast currently has 102 episodes available.