Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና ... more
FAQs about The Rising South:How many episodes does The Rising South have?The podcast currently has 102 episodes available.
July 07, 2025ዲግሪ ወይስ ጥበብ? “የተማረ”፦ ሊጤን የሚገባው ሃሳብዛሬ ሰኔ 30 ነው! ሰኔ 30 በተለምዶ የየዓመቱ የትምህርት ጊዜ መዝጊያ ተደርጎ ይወሰዳል ። ይህንኑ ዕለት መነሻ ያደረገዉ የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ላይ በጊዜ ሂደት የታዩ ለውጦችን - ንድፈ-ሃሳብ ላይ ብቻ ወይም 'ሽምደዳ' ላይ ከማተኮር ይልቅ ተማሪዎች በነጻነት ምክንያታዊ አስተሳሰብን እንዲያጎለብቱ ወደሚያስችል የመማር ማስተማር ሂደት መቀየርን እንዳስሳለን። ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ ማሞ መንገሻ ጋር በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ስለታዩ ለውጦች እና አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የብቁ መምህራን እጥረት ዙሪያ ውይይት እናደርጋለን፡፡...more1h 1minPlay
July 04, 2025ቢትኮይን ፣ ባህል እና ደቡባዊው ዓለም፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል እድገትና የባህል አንድነትበክፍል አንድ፡ የቢትኮይን ባለሙያው ቃል ካሳ የኢትዮጵያ እያደገ የመጣዉ የኤሌክትሪክ ኃይል የክሪፕቶ ኢንደስትሪውን እንዴት እየመገበው እንደሆነይናገራል፤ በያዝነው ዓመት ብቻ ዘርፉ ከ200 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ አስገብቷል፡፡በክፍል ሁለት፡ ራይዚንግ ሳዉዝ የደቡባ ትብብር ካውንስል ፌስቲቫልን መነሻ አድርጎ፣ የባህል ነጻነትን ስለመቀዳጀት የተለያዩ ሀሳቦችን ራይዚንግ ሳዉዝ በሰፊው ዳስሷል፡፡...more1h 0minPlay
June 30, 2025የትናንቱን ዕውቀት መመለስ፡ ትምህርትን ከቅኝ ግዛት ተፅዕኖ ማላቀቅ በአፍሪካየአፍሪካ ትምህርት በቅኝ ግዛት ከመታወኩ በፊት በአገር በቀል እውቀት የተቀረፀ ጥልቅ፣ የተለያየ ታሪክ ያለው ነበር። ዛሬም አህጉሪቱ የራሷን እሴቶች እና እውነታዎች ለማንፀባረቅ ከቅኝ ግዛት ዘመን የተወረሱ ስርዓቶችን የመቀየር ፈተና ተጋርጦባታል።በዚህ የራይዚንግ ሳዉዝ መሰናዶም የሚዲያ እና ትምህርት ለልማት አፍሪካ ፎረም ጥምረት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ላዋሊ ኮል ጋር ያልተነገረውን የአፍሪካን ትምህርት ታሪክ ፤ የቅድመ ቅኝ ግዛት የእውቀት መገለጫዎችና፣ የቅኝ ግዛት ዘመን ጥፋቶችን በሰፊው እንመረምራለን።...more1h 0minPlay
June 25, 2025ሉዓላዊነትን እና ትብብርን ማዳበር፡ የአፍሪካ የግብርና ለውጥ ሥር እየሰደደ ነው“የትሮፒካል ክልል [የደቡባዊ ዓለም] ሀገራት ድህነትን እና ረሃብን በጋራ ለመጋፈጥ አንድ ላይ መሆን በሚያስፈልግበት ወቅት ላይ ነን” ሲሉ የብራዚል የግብርናና የእንስሳት እርባታ ም/ ሚኒስትር ክሌበር ሶአሬስ ከ7ኛው የአግሮ ፉድ ኢትዮጵያ ሁነት በጎንዮሽ ተናግረዋል። ...more30minPlay
June 23, 2025ከተረጅነት ወደ አጋርነት ፦ የምዕራባውያን ዕርዳታ መቀነስ እና ብሪክስ ይዞት የመጣው ዕድል በኢትዮጵያየዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት ዝላታን ሚሊሲች አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዓለም የምግብ ፕሮግራም የሚያደርጉትን ዕርዳታ በመቀነሳቸው ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ሊደረግ ከታሰበው ዕርዳታ በግማሽ ያህል እንደሚያንስ ተናግረዋል። የሚቀነሰው የዕርዳታ መጠን በአሀዝ ሲገለጽ 222 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 28 ቢሊየን ብር ገደማ እንደሚሆን ጠቁመዋል።...more30minPlay
June 19, 2025የወደፊቱ የዲጂታል ዓለም ፦ አፍሪካ በቴክኖሎጂ ዘመን ያላት ድምፅአፍሪካ በዲጂታሉ ዓለም መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆማለች። የምዕራባውያን ቴክኖሎጂ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት የበላይነት በያዙበት በዚህ ወቅት ጥያቄው ግልጽ ነው፡- አፍሪካ ማንነቷን ጠብቃ ዲጂታል ዓለሙን በመምራት ቀዳሚ መሆን ትችላለችን ?...more30minPlay
June 16, 2025የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ:- የአዋጁ ይዘት እና ቅጣቶቹበኢትዮጵያ የከተሞች መስፋፋት እና እድገት፣ ከሕዝብ ቁጥር እድገትና ለዉጥ ጋር ተዳምሮ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ የራሱን የሆነ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ግንቦት 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ በዋለው የ33ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ን በሙሉ ደምጽ አፅድቋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ቆይታችን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አወቀ አምዛዬ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡🔇ዶ/ር አወቀ ስለዚህኛው አዋጅ ሲያብራሩ:-“ባለፉት ጊዜያት የወጡ ወጥቶ የነበረው አዋጅ ያስከተለው ችግርና ምንም መተግበር ስላልተቻለ፣ ሀገሪቱ እየተበከለች ስለሆነ ቀስ በቀስ ሺፍት እንዲያደርግ ነው። ሁለተኛ ዛሬውኑ ይታገድ ብሎ አይደለም በነገራችን ላይ የወጣው አዋጅ። ስድስት ወር የሽግግር ጊዜ አለ ገና። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከባለ ኢንዱስትሪዎች ጋራ ምክክሮች ይደረጋሉ፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ 💸አዋጁ ቅጣትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ሲገልጹ፡-“ባለሱቁና አምራቹ ይቀጣል በነገራችን ላይ፤ ሁለት ሺህ ብርና ሶስት ሺህ ብር ለግለሰብ ነው። አምራቾች የእነርሱ ቅጣት ከ50 ሺህ ብር በላይ ነው። እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚደርስ ነው።” በማለት ዶ/ር አወቀ አክለው ተናግረዋል፡፡''ስለ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ይዘት እና አዋጁን መተላለፍ ስለሚያስከትላቸው ቅጣቶች የበለጠ ለማወቅ ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተሉ፡፡ ...more30minPlay
June 10, 2025የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካን የዕዳ ጫና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ይቀይረዋልን?የአፍሪካ የዕዳ ጫና ከጠቅላላ የአህጉራዊ ምርት ውስጥ ከ 66 በመቶ በላይ ሆኗል ። ለዚህም ደካማ የብድር ስርዓት እና ሙስና ምክያቶቹ ናቸው፡፡ ይህ የጤና ስርዓት ላይ እና ትምህርትን በማደናቀፍ ረገድም አሉታዊ ሚናን እየተጫወተ ነው። በዛሬው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የጋበዝናቸዉ ዶ/ር ጀማል መሐመድ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ።“ብድር በግድ ውሰዱ ብለው አያስወስዱንም፡፡ [...] ከጀርባ ግን ብድር እንድንጠይቅ የሚገፋፉ ነግሮች አሉ ፡፡ ወርልድ ባንክም አይ ኤም ኤፍም፡፡ [...] በተለይ አፍሪካ አካባቢ ደግሞ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማት ስለሌሉ አብዛኛው [ብድር] በካፒታል ፍላይት [ብድሩ በሃገር ስም ቢመጣም] ብሩ ተመልሶ ወደ አዉሮፓ እና አሜሪካ ይሄዳል፡፡ በተመሳሳይ [ዕዳዉን ] እኛ እንከፍላለን ፣ አበዳሪዎች ያተርፋሉ" ብለዋል፡፡የምስራቃዊ ቡድን አቀራረቦችን በተመለከተም ዶ/ር ጀማል መሐመድ:-"የሩሲያ እና የቻይና አቀራረብ በምጣኔ ሃብታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተለይ የሩሲያ አቀራረብ ከዚያ በላይም ሊሄድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከነጻነት ትግል ወቅት ጀምሮ ሀገራት ነጻ እንዲሆኑ ሃቀኛ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት ሩሲያዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ያላቸው እሴት ይመስለኛል፡፡ [...] ሌሎቹም አገራት የእነሱን ዓርዓያነት ተክትለው ነበር፡፡ ለአብነት ኩባን መጥቀስ ትችላለህ፡፡ እነ ፊደል ካስትሮ ለኢትዮጵያ እና አንጎላ ድጋፍ ያደረጉት [ለዚያ ነው]” ሲሉ ተናግረዋል።ዶ/ር ጀማል እንደ መፍትሄ ባሉት ሀሳብ:-"አፍሪካውያን እንደመሆናችን መጠን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በማጠናከር የውጭ ኃይሎች ላይ ጥገኝነትን መቀነስ አለብን። 54 የተለያዩ ኢኮኖሚዎች ያሏት አፍሪካ ታሪፎችን እና የገበያ እንቅፋቶችን በማስወገድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሚስብ አንድ ወጥ ገበያ መፍጠር ትችላለች" ብለዋል፡፡ስለ አፍሪካ የእዳ ጫና እና ከእዳ መውጫ መንገዶች ለማወወቅ ይህንን የ ራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተላሉ።...more1h 0minPlay
June 04, 2025ያረጁ ትርክቶችን ልሳን መዝጋት: ደቡባዊ ዓለም መጪውን ጊዜ የሚቀረጽበት ሂደትበዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በደቡባዊው ትብብር ድርጅት /Organization of Southern Cooperation/ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ዲጂታላይዜሽን ማበልጸግ ምክትል ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሹመቴ ግዛው /ፒ.ኤች.ዲ/ የዓለም አቀፉ የኃይል ሚዛን ስለሚቀየርበት መንገድ ወሳኝ ነጥቦችን አጋርተዋል።“የደቡባዊው ትብብር ድርጅት በታላቁ ደቡባዊ ዓለም ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን እና ማኅበረሰቦችን አቅም ማጎልበት ላይ ያምናል። ለአብነት ያህል ባህላዊ እና ሀገር-በቀል ዕውቀቶቻቸውን በመውሰድ ዓለም-አቀፍ በሆኑ መድረኮች ላይ እንዲሰሙ ያደርጋል።" በማለት ተናግረዋል።ምክትል ዋና ሥራ ፈጻሚዉ የዓለም-አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ሀገራትን ዕዳ ውስጥ የሚዘፍቅ ነው በማለት ተችተዋል። የብሪክስን እሴቶች በሚጋራ መልኩ ባለብዙ ዋልታ እና ባለብዙ ዘርፍ የሆነ አዲስ ሞዴል እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።የዓለምን ሥርዓት በመቀየር ሂደት ሚዲያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ሲሉ አስረድተዋል ፤ "ስፑትኒክ ሚዲይ እዚህ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሮውን በመክፈቱ እና ፍትህን፣ እኩልነትን፣ ሁሉን አካታችነትን እንዲሁም በራስ ፈጠራ ላይ መሠረትን ያደረገ ትርክት ሳይሆን መሬት ላይ ባለ ተጨባጭ እውነት ላይ ስለሚሠራ ያለኝን አድናቆት መግለጽ እፈልጋለሁ።" በማለት ገልጸዋል። የመጪውን ዓለም ሥርዓት የሚያስቃኘውን ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተላሉ።...more1h 0minPlay
June 03, 2025የለዉጥ ጎዳና - የኢትዮጵያ ሽግግር ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችየኤሌትሪክ ኃይልን በመጠቀም ከብክለት የጸዳ የትራንስፖርት ማዕከል ለመሆን የሚደረግ ኢትዮጵያዊ ጉዞ!🎙በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የትራንስፖርት ባለሙያው አቶ ሞገስ ነጋሽ ኢትዮጵያ ከፖሊሲ እስከ ትግበራ ድረስ በትራንስፖርት ረገድ የያዘችውን ጉዞ ፣ እንዲሁም በኬንያ ስለሚካሄደው አውቶኤክስፖ ከቡርኪናፋሶ እና ናይጀሪያ የተሽከርካሪ ምርት ስኬት ጋር አያይዘው ስለ አፍሪካ አረንጓዴ ጉዞ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። 🌍 "በኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ የሰው ኃይል አለ....የፀሐይ ብርሃን፣ መልክዓምድራዊ አቀማመጡን ስትመለከት ኢትዮጵያ የቃጣናውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ምርት በበላይነት ለመምራት የሚያስችላት ትልቅ ዕድል አለ።""ኢትዮጵያ ተሽከርካሪን ከመገጣጠም አልጀመረችም....አሰቀድመን መማር ነበረብን። ሥልጠናውን ጋገኘን በኋላ ግን አሁን ላይ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እየገጣጠምን ነው። ስለ ኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችም ሥልጠና ብናገኝ፣ አቅሙም ፣ ልምዱም እንዲሁም የተማረ የሰው ኃይል ስላለን የሚከብደን አይደለም።" በማለት አክለዋል። ኢትዮጵያ ስለተያያዘችው የኃይል ለውጥ የበለጠ ለማወቅ ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተሉ።🔌🌿...more30minPlay
FAQs about The Rising South:How many episodes does The Rising South have?The podcast currently has 102 episodes available.