Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
August 11, 2021እግዚአብሔር ያየውን ማየትአሸናፊ ሕይወት እንድንኖር የሚረዳንና መንፈሳዊ ሰው የሚያስብለን እግዚአብሔር ያየውን ስናይና ያወቀልንን ስናውቅ ነው፣እግዚአብሔር ያየውን ካየን በዙሪያችን ያለ ማንኛውም ሁኔታ አያናውጠንም፣ እርሱ ያየውን ካላየን ግን ከእምነታችን እንጎድላለን ተስፋችን የሆነው እየሱስ ይደበዝዝና በምናየውና በምንሰማው እውነት ባልሆነው ሁሉ የምንናወጥ፣ ጭንቀትንና ፍርሃትን ብቻ የምናስተናግድ እንሆናለን፣ እግዚአብሔር ግን ለአምላክነቱ እውቅናን እየሰጠን ቃሉን ተደግፈን በአረፍት እንድንኖር ይፈልጋል፣...more46minPlay
August 11, 2021የቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ትበዛ ነበር የሐዋርያት ሥራ 9:31የቤተ ክርስቲያን መብዛት ማለት የአዳዲስ ሰዎች መጨመር ማለት ነው፣ መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚያስተምረን በስደት የተበተኑት የክርስቶስ ተከታዮች ወንጌልን ለማብሰር ስደታቸው አላቆማቸውም፣ እንዲያውም በደረሱበት ሁሉ የምስራቹን ቃል ያበስሩ ስለነበረ ስደታቸው ለመብዛታቸው ምክኒያት ሆኖላቸዋል፣ ዛሬም እኛ ይህን ደህንነት ያገኘን ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት ሀላፊነት እንዳለብን በመረዳት በግልም ሆነ በሕብረት እግዚአብሔር ባዘጋጀልን ስፍራና በከፈተልን በር ሁሉ የክርስቶስን አዳኝነት ለሰዎች ሁሉ ልንመሰክር ይገባናል፣...more41minPlay
August 10, 2021የሚላችሁን ሁሉ አድርጉእግዚአብሔር ወደእኛ የሚመጣው በሕብረት በአንድነትና በፍቅር ስንቆም ለእርሱ ስንታዘዝና የሚለንን ስናደርግ ነው፣ ጌታ ደግሞ አንድ ነገርን አድርጉ ብሎ ካዘዘን ክብሩን ለመግለጽ ክብሩን ለማየት ተካፋዮች ሊያደርገንና ጎዶሎ የሆነው ነገራችንን ሊሞላ ነው፣ የሚያደርገውን የሚያውቅ ይህ ትልቅ ጌታ አድርጉ የሚለንን ሰምተን ከታዘዝን የበረከቱ ተካፋዮች እንሆናለን የሚለንን ደግሞ ካላደረግን ክብሩን ከማየት እንጎድላለን፣...more29minPlay
August 09, 2021የጠራንን ስለማወቅ 2ጴጥ 1:1-11አማኝ የተጠራበት ጥሪ የከበረ እንደሆነና ያገኘውንም የክብር ታላቅነት አጥርቶ ማየትና ማወቅ ዋነኛና አስፈላጊ ነገር ነው:: የጠራንን አምላክ ልጁንም ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ በተጠራንበትም መጠራት እንደሚገባ ልንመላለስ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድና ደሰ የሚያሰኘውም ነው:: የዚህም መልዕክት ትኩረት በዚሁ ሀሳብ ላይ ነው:: እንዴት እንደሚገባ መመላለስ እንዳለብን በስፋት ይዘረዝራል::...more48minPlay
August 09, 2021እግዚአብሔር ያሳልፋልበህይወት ጉዞ ውስጥ መልካምና በጎ የሀሴትና የደስታ ጊዜዎች እንዳሉ እንዲሁ ደግሞ የምናልፋቸው ብዙ አስጨናቂና አስፈሪ ሁኔታዎች ይኖራሉ:: አናልፍም ያልናቸውን አልፈንና ተሻግረን ዛሬን መድረሳችን ከሚመራንና ካሳለፈን ከእግዚአብሔር የተነሳ ብቻ ነው:: የእግዚአብሔር እኛን የመምራቱ ችሎት ከሚያስጨንቀን ከወጀቡ በማሳለፍ ይገለጣል:: በልጆቹ ላይ ክፉው የክፉውም ማስጨነቅ ስልጣን የለውምና:: ይሁ ደግሞ ለስሙ ክብር ይሆናል::...more26minPlay
August 08, 2021በእግዚአብሔር መታሰብእግዚአብሔር እርሱ የቃል ኪዳን አምላክ ነው:: ስለዚህ የቃል ኪዳኑን ህዝብ ያስባል:: የምናልፍበት ማንኛውም ሁኔታ በፊቱ ነው:: በጊዜው ጉብኝት ይሆናል:: በእግዚአብሔር መታሰባችንም በተለየ ሁኔታ ይገለጣል:: የአስበኝ የፀሎት መልስ እውን ይሆናል:: ጨለማው በብርሃን ይለወጣል:: ከውድቀት መነሳት ይሆንል:: ከድካም መበርታት ይሆናል:: ተስፋም ይሞላል::በህይወታችን ያለው አንዱ ተስፋ እርሱም በእግዚአብሔር የምንታሰብ ሰው መሆናችን ነው::...more29minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.