መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደ ጊዜና የመጀመሪያውን የወንጌል ምስክርነት አሰምተው ሰዎች በኢየሱስ ባመኑ ጊዜ የቤተክርስቲያን ውበት መገለጥ ጀመረ:: በአመታት መካከል በቁጥር እየበዛችና እያደገች ደግሞም እየተገለጠች መጣች:: መከራ እየጨመረ በመጣ መጠንም በቤተክርስቲያን አብዝቶ ድንቅና ተአምራት ይሆን ነበር:: ፀጋም ይገለጥ ነበር::
በጉዞ ውስጥ ድካም ሲኖር ዝለት ሲመጣ ጌታ ደግሞ ተሃድሶን ያደርጋል:: ጉብኝት ይሆናል:: ሀይል ይታደሳል:: እንደ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሀይል ይገለጣል:: በዚህን ጊዜ ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእርሱ ጋር ያለው የሰው ግንኙነት እንዲታደስ ይፈልጋል::