Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
June 17, 2021በእግዚአብሔር ፊት የሆነ ፀሎት የማቴዎስ ወንጌል 7:1-8ፀሎት ማለት ሐይማኖታዊ ልምምድ ሳይሆን ከምንጠይቀውና ከምንቀበለው ያለፈ፣ በመንፈስ ቅዱስ መገኘት፣ ወደ ውስጠኛው የጌታ ህልውና ውስጥ ገብተን ከጌታ ጋር የአባትና የልጅ ሕብረት ማድረግ ማለት ነው። ለዚህም ነው መፅሐፍ ቅዱሳችን የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ብሎ የሚመክረን።...more47minPlay
June 16, 2021በእግዚአብሔር ፊት ስለ አለመረሳት ዕብራውያን 6:10-12እግዚአብሔር በባሕሪው ማንንም አይረሳም። በሰው አይምሮ ነገራቸው ሁሉ ያለቀና የተረሱ የሚመስሉ ብዙ ሰዎች በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌነት ተጠቅሰውልናል፣ በመጨረሻ ግን በእግዚአብሔር ታስበው፣ ዛሬም ያለፉበትን የሕይወት ውጣ ውረድ ስንማር ያስደንቀናል። እግዚአብሔር ፍርድ የሚያደላድለው፣ ሰውን የሚያስብ አምላክ በመሆኑ ነው።...more36minPlay
June 16, 2021ቃሉን ሰምቶ መታዘዝቃሉን ሰምቶ መታዘዝ የሉቃስ ወንጌል 10: 1-11መታዘዝ ቃሉን ከማድመጥ ይጀምራል። ጌታ እየሱስ በመጀመሪያ ደቀ መዛሙርቶቹ እንዲለማመዱ የፈለገውና ዛሬም አማኞች የሆንን ሁላችን ልናደርገው የሚገባን፣ ለሰማነው ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝን ነው። ለክርስቶስ ያለንን ፍቅር የምንገልፀው፣ ቃሉን በመስማትና በመታዘዝ ሲሆን፣ ይህ ለቃሉ በመታዘዝ መኖር ደግሞ ክርስቶስን ወደ መምሰል ያደርሰናል።...more54minPlay
June 15, 2021የምናገለግልበት ሀይልኢያሱ በፊቱ ተሰብስቦ ላለው ለእስራኤል እግዚአብሔርን ፍሩ ብሎ አወጀ::በጉዞው ሁሉ ደግሞም ወደፈት ሊኖርበት ባለውም ምድር የእስራኤል ጉልበት እግዚአብሔርን መፍራቱ ነውና::በክርስቶስ ኢየሱስ ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የተጠራን አኛ ሁልጊዜም በልባችን ሊኖር የሚገባው አንድ ነገር እርሱም ከራሳችን የሆነ አንዳች የሌለ ደካሞች እንደሆንን ነው:: በመንግስቱ ውስጥ ግን በእግዚአብሔር ሀይል እንወጣለን እንገባለን ደግሞም በእርሱ ሀይል እናገለግላለን እርሱንም ለማክበር እንኖርማለን::...more46minPlay
June 15, 2021መለወጥየአማኝ መንፈሳዊ ጉዞ ከሀይል ወደ ሀይል ከክብርም ወደ ክብር ነው:: ደግሞም የማያቋርጥ ለውጥ በህይወቱ ይኖራል:: በህይወታችን የሚኖረው ለውጥ እንዲያድግ እግዚአብሔር የወደደው የልጁን መልክ ወደ መምሰል ነው:: ይህ ደግሞ ራስን ከመካድና ዝቅ ከማለት ደግሞም ከመታዘዝ ይጀምራል::በዚህ መልዕክት በቀደሙት የተለያዩ ሰዎች በህይወታቸው የተገለጠውን የለውጥ አይነት በማየት ዛሬ ደግሞ ለእኛ የህይወት ለውጥ ይጠቅመን ዘንድ በስፋትና በዝርዝር ቀርቧል::...more46minPlay
June 13, 2021እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን ሊሰራ ፈቃዱ ነውእግዚአብሔር እርሱ በሰማይና በምድር አምላክ ነው::ብላ ያመነች ደግሞም የመሰከረች ረዓብ ከሚጠፉት ጋር አብራ አልጠፋችም:: ምንም ታናሽና ደካማ ብንሆን በእምነት በፊቱ እንሁን እንጂ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን ሊሰራ ፈቃዱ ነው::በዚህ መልዕክት ትናንት በረዓብ ህይወት ድንቅን ያደረገ ጌታ ዛሬም በእኛ እንዴት እንደሚሰራ እንማራለን::...more41minPlay
June 12, 2021እግዚአብሔር እንደተናገረው ነውእግዚአብሔርን እንደትናገረው ካላመንን አይመችንም ስንታመነው እንደቃሉ ስናየው ንብረታችን አቅማችን ነው ችግር የለም ማለት አይደለም ከችግር በላይ ነው ማለትና ማመን ግን ሃይል ማግኘት ነው ነገር ግን ሰይጣን ይህ እውነት እንዳይገባን ይታገልናል ስለዚህ ጨለማውን እያየን ተስፋ መቁረጥ የለብንም...more36minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.