Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
June 24, 2021ከጌታ የተቀበልነው ያሸናፊነት ህይወትየክርስትና ህይወት የተጀመረው ካሸናፊነት ነው። ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ሞታችንን ሞቶ፣ የዕዳችንን ጽሕፈት ደመስሶ፣ በእርሱ የኃጢአትን ስርየት አግኝተን የድል ሕይወትን ስጥቶናል። የድል ሕይወትን ስለሰጠን ደግሞ የድል ኑሮን እንድንኖር ይጠብቅብናል። የድል ኑሮን ለመኖር፣ እርሱን ድል የሰጠንን አምላካችንን በማክበር፣ ሁልጊዜ እራሳችንን በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ማየት ይኖርብናል። የተለያዩ ችግሮች በመነንገዳችን ሲገጥሙን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመስማማት፣ የገባልንን የተስፋ ቃል አያሰላሰልን፣ አልፈን ማየት መቻል ይኖርብናል።...more51minPlay
June 23, 2021ጌታን መጠበቅማርያምና ሌሎችም የእግዚአብሔርን ቃል በመተማመን የጠበቁ ሰዎች፣ በትልቅ ድል ውስጥ እንዳለፉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎልናል። የምንሰማውን ቃል ሁለንተና ካደረግነው እንጠብቀዋለን፣ በመጠበቃችን ደግሞ እንከብራለን ያልጠበቅነው ቃል ደግሞ ሕይወት አይሆንልንም። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ያለን ቃልና እኛ የምናልፍበት ሁኔታ በጣም የተራራቀና ያለንን የሚያስጥል ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን እግዚአብሔር አንዱ መንፈሳዊነትን የሚያለማምደን መንገዱ በመጠበቅ ውስጥ ነው።...more45minPlay
June 23, 2021የደቀመዝሙር ህይወት:: ማቴ.10:5-24 ክፍል 1በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ በምድር ሲኖር ተልዕኮ አለው:: ተልዕኮውም ጌታ ኢየሱስን ለሌሎች ማሳየት ነው:: በቃልና በሰራ በኑሮ:: ይህንንም ተልዕኮ እለት እለት ለመፈፀም መታዘዝ ስርአትና እምነት ከእኛ የሚጠበቁ ናቸው::- ለጌታ ፈቃድ ለቃሉ በመታዘዝ እንዲሁም የራሳችንን ክብር ጥለን ለሌሎች እንቅፋት ባለመሆን ደግሞም በእምነት መራመድ::...more40minPlay
June 22, 2021የሚያስብ አምላክእግዚአብሔር ባሰበን ጊዜ የእርሱ ባርኮት ወደ ህይወታችን ይፈሳል:: የፀሎት መልስ ይሆናል:: ተስፋ ያደረግነውም እውን ይሆናል:: የሚሆነው ሁሉ የሚሆነው ግን በእኛ ጊዜ አይሆንምና አንዳንድ ጊዜ ተስፋ እንቆርጣለን:: ከምናልፍበት ሁኔታ የተነሳ እግዚአብሔር እኔን ረስቶኛል ለማለትም ደፍረን ይሆናል:: ጌታ ግን ሁሉን በራሱ ጊዜና ሰአት በወደደውም መንገ ውብ አድርጎ ይገልጠዋል::እግዚአብሔር እርሱ አይለወጥም:: ዛሬም ያስባል::ይጎበኛልም:: እኛ ግን በጊዜውም አለጊዜውም በምስጋና ሆነን በፊቱ ልንቆይ ያስፈልጋል::...more38minPlay
June 22, 2021ኢያሪኮን ለመውረስ የተሰጠ መመሪያ (ኢያሱ 1 : 1-11 )እግዚአብሔር ለእስራኤል የተናገረው የተስፋ ቃል ሁሉ ተፈፅሟል :: መንገዳቸው በበረሀ ውስጥና በብዙ ፈተናም የተሞላ ቢሆንም በእግዚአብሔር ላይ የታመኑ እንደተባለላቸውም በተስፋው ቃል የፀኑ የጉዟቸውን ፍፃሜ መዳረሻ አይተዋል:: ወደ ተስፋውም ምድር በድል በሞገስ ገብተዋል::በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ከኃጢአት ባርነት ተላቀን ከአለም ወጥተን ወደ መንግስቱ የፈለስን አኛም እንደ እስራኤል ሁሉ ለህይወት ጉዟችን የተሰጠ መመሪያ አለ:: ይህንን በዚህ መልዕክት በጥልቀት እንማራለን::...more51minPlay
June 21, 2021መንፈሳዊ ውጊያ ኤፌ.6:10-18የክፉ መናፍስት ሥራ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የለውን ህብረት ማበላሸት ደግሞም በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነትና መታመን መሸርሽር ያለንንም ተስፋ ማጨለም ነው:: ስለዚህ ሁልጊዜ ለክፋት በተለያየ መንገድ የሚተጋ ጠላት እንዳለብን አማኞች ልናስተውል ፀንተንም በእግዚአብሔር ቃልና በፀጋው ልንዋጋውና በአሸናፊነት መንፈስ ልንቆም ያስፈልጋል::በዚህ መልዕክት የክፉውን አሰራርና በሌላ በኩል ደግሞ በክርስቶስ ያገኘነውን የአሸናፊነት ህይወትና የፀጋውን ጉልበት እንማራለን::...more38minPlay
June 21, 2021አይኖቹ የተከፈቱለት ሰው::መንፈሳዊ አይኖቻችን ሲከፈቱ የምናየውና የምንሰማው ደግሞም ሁለንተናችንን የሚወርሰው የሚገዛው የሚመራውም የእግዚአብሔር ድምፅ ይሆናል:: ለተጠራንለትም አላማ እንኖራለን:: በህይወታችን የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በስሜት ሳይሆን በማስተዋልና በጥንቃቄ ማየት እንጀምራለን:: አሻግረን ወደፊት ማየት እንችላለን:: በእምነት እንበረታለን ሀይልና ጉልበት ተስፋም ይሆንልናል::...more32minPlay
June 20, 2021እግዚአብሔር በሞተ ነገራችን ላይ ይመጣልእግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው:: እርሱ የእኔ ነው :: ለሚል ደግሞም በስፍራው ፀንቶ ለቆመ ለእርሱ የታመነበት ደግሞም አለኝ ያለው ጌታ ባለበት በሁኔታው ላይ ይመጣል:: ክብሩንም ይገልጣል:: ታምኗልና:: በእኛ ዘንድ ያበቃለት ተስፋም የተቆረጠበት ጉዳያችን ሁሉን ቻይ በሆነው ጌታ የእኛ በሆነው በእርሱ ዘንድ ቀላል ነው:: ሞቷል ለምንለውም እንኳ ህይወት ይሰጠዋል:: እንዴት ይሆናል ተብሎ አይጠረጠርም...more24minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.