የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የታኅሳስ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    የኢራን የፍትሕ ሚኒስትር በሐገሪቱ ሰልፍ በሚያካሂዱት ላይ በቸልታ እንዳማያልፉ አስጠነቀቁ። የቀድሞው የሩስያ ፕረዚደንት ዲሜትሪ ሜድቪዴቭ፤ «የጀርመን መራሔ መንግስት ፍሬደሪሽ ሜርስም እንደ ቬንዙዌላው ፕረዚደንት በተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ ሊታገቱ ይገባል» ሲሉ የሰጡትን አስተያየት በርሊን በጥብቅ አወገዘች። ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ዓለም ዳኛ ሆና እየተንቀሳቀሰች ነው ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰሰ።
    12 min
  • የታኅሳስ 26 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • በናይጄሪያ ማዕከላዊ ኒጀር ግዛት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች ተገደሉ • የየመን ተገንጣይ ቡድን በትንሹ 80 ያህል ወታደሮቼ ተገድለዉብኛል አለ። •በአሜሪካ ወታደሮች ተይዘው የተወሰዱት የቬንዙዌላው ፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮ የዕጽ ዝውውር የሽብር ወንጀል ክስ ሊመሰረትባቸው ነው። • ሩስያ በአውሮጳዉያኑ አዲስ ዓመት ሰሞን በዩክሬን ላይ ከ2000 በላይ የአየር ጥቃት መፈጸሟን ፕሬዚዳንት ቮልዶሚር ዜሌንስኪ አስታወቁ። • ጀርመን ውስጥ ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ።
    9 min
  • የታኅሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በተከሰተው የናፍጣ እጥረት መቸገራቸውን አሽከርካሪዎች አማረሩ። የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ኻመኒ ሐገራቸው «ጠላት» ላሏት አሜሪካ እጅ እንደማትሰጥ አስታወቁ። ዩናይትድ ስቴትስ በቬንዙዌላ ላይ ከባድ ጥቃት በመፈጸም የሐገሪቱን ፕሬዚደንት መያዝዋን አስታወቀች።
    11 min
  • የታኅሣሥ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    «ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት» የተባለ አራት የፖለቲካ ድርጅቶችን ያቀፈ ቅንጅት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ማግኘቱን ዛሬ አስታወቀ።
    ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌደሬሽን ባለፈው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2025 128 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች መገደላቸውን አመለከተ።
    እራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና ከሰጠቻት እስራኤል ጋ ፍልስጤማውያንን በግዛቷ ለማስፈር ተዋውላለች መባሉን አስተባበለች።
    ኢራን ውስጥ ለተቀጣጠለው የሕዝብ ተቃውሞ ፕሬዝደንቱ ባለሥልጣናቱን ተጠያቂ ነን አሉ። የጸጥታ ኃይሎች ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ከቀጠሉ አሜሪካ ልከላከልላቸው ዝግጁ ነኝ እያለች ነው።
    11 min
  • የታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    የታኅሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
    የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አንደኛ የፀረ-ሽብርና ሕገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ ከቀረቡት ሶስት የክስ ጭብጦች አንደኛው እንዲሻሻል ዛሬ በየነ። የተጠየቀው የዋስትና መብት ውድቅ እንዲሆንም ወስኗል።
    በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ህዝቡ አዲሱን ጎርጎሮሳዊውን 2026 ዓ.ም. በፌሽታና በቀለማት ያሸበረቁ ርችቶችን በማፈንዳት ተቀብሏል።
    ስዊስ አልፓይን በሚገኝ አንድ ቡና ቤት ውስጥ በተካሄደ የአዲስ ዓመት አከባበር ላይ በተነሳ እሳት በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ አስግቷል።
    13 min
  • የታኅሣሥ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    ጋምቤላ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የሰላም ጉባኤዎች እየተካሄዱ ነው።
    ማሊ እና ቡርኪና ፋሶ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የሚያግድ ደንብ ይፋ አደረጉ። የትራምፕ አስተዳደር የሁለቱን ጨምሮ ወደ 40 ገደማ ሃገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ በቅርቡ አግዷል።
    ተርክዬ እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለው በእንግሊዝና ምህጻሩ IS በተባለው ቡድን አባልነት የተጠረጠሩ 125 ሰዎች አሠረች። በዘመቻው እስካሁን የታሰሩት 600 ደርሰዋል።
    የአውሮጳ ሕብረት እስራኤል ጋዛ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የረድኤት ድርጅቶችን ማገዷ ሕይወት አድን እርዳታዎች ወደ ሕዝቡ እንዳይደርሱ ያደርጋል ሲል አስጠነቀቀ።
    12 min
  • የታኅሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    እስራኤል ለሶማላንድ የሉዓላዊ ሀገርነት ዕውቅና መስጠቷን የተቃወሙ በሺዎች የሚቀጠሩ ሶማሊያዊያን ዛሬ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች አደባባይ ወጡ።
    ሳዑዲ አረብያ ዛሬ የየመንን የወደብ ከተማ ሙካላን በቦምብ ደበደበች።
    ከፕሬዝዳንት ፑቲን ፕሬዝዳንታዊ መኖሪያ ቤታቸው በአንዱ ላይ ዩክሬን ጥቃት ለመፈጸም ሞክራለች ስትል ሩስያ ከከሰሰች በኋላ ፑቲን የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም በሚካሄደው ድርድር ላይ የያዙትን አቋም እንደገና እደሚመረምሩ ለትራምፕ ተናገሩ።
    11 min
  • የታኅሣሥ 20 ቀን 2018 ዓም የዓለም ዜና
    በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲች ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣሥ 14 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ 19 ሰዎች መገደላቸውን እናት ፓርቲ አመለከተ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው ከ500 በላይ ቤቶች፤ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎችም መውደማቸውን ገልጸዋል።
    የሱዳኗን አል ፋሸር አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙ የተመድ ባለሙያዎች በደረሰባቸው ጥቃት ስቃይ ላይ የሚገኙ ሲቪሎችን መመልከታቸው ይፋ አደረጉ።
    በተሰናባቹ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2025 ወደ ስፔን ለመግባት የሞከሩ ከሦስት ሺህ በላይ ስደተኞች ሕይወት ማለፉን የስፔን የስደተኞች መብት የተሰኘ ቡድን ዛሬ ይፋ አደረገ።
    11 min
  • የታኅሳስ 19 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና
    • 103 ህገ ወጥ ኤርትራዊያን ስደተኞች እና 5 የሰዎች አዘዋዋሪ ደላሎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡
    • እስራኤል ለሶማሊ ላንድ የሰጠችው ዕውቅና ለዓለም እና ለቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ስጋት መደቀኑን የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ተናገሩ ።
    • ጣልያን ለፍልስጤማዉያኑ ታጣቂ ቡድን ሐማስ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር ያለቻቸውን 9 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች።
    • የዩክሬይኑ ፕረዚደንት ቮለደሚር ዘለንስኪ ደም አፋሳሹን ጦርነት ለማስቆም አጋሮቻቸው በሩስያ ላይ ጫናቸውን እንዲያበረቱ ጥሪ አቀረቡ።
    9 min
  • የታሕሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
    በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ታጣቂዎች በወርቅ እና በእምነበረድ ማውጫ ሥፍራዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ስምንት ሰዎችን ገደሉö የአፍሪካ ሕብረት፤ እስራኤል ለሶማሊላንድ ነጻ ሉአላዊት ሐገር አድርጋ እውቅና መስጠቷን አወገዘ። ሩስያ በዩክሬይን ዋና ከተማ ክዬቭ በፈጸመችው የሚሳይልና የድሮን ጥቃት 1 ሰው ሲሞት ከ20 በላይ መቁሰላቸው ተሰማ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…