Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት... more
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,858 episodes available.
May 02, 2024የዓለም ዜና፦ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም.የሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴና የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ እንዲሁም የራያ አላማጣ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው ሰሞኑን በታጣቂዎች ተግደለዋል ሲሉ ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ገልጸዋል። የጋዛው ጦርነት ጦርነቱ ዛሬ ቢቆም እንኳን የወደሙትን ቤቶች መልሶ ለመገንባት ቢያንስ 16 ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል የተመድ አስታወቀ። የአውሮጳ ኅብረት ለሊባኖስ አንድ ቢሊዮን ዩሮ ወይም 1.07 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የፋይናናስ እርዳታ ለመስጠት ቃል ገባ።...more11minPlay
May 01, 2024DW Amharic የሚያዝያ 23 ቀን 2016 የዓለም ዜናየአውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያውያን የቪዛ አሰጣጥ ሒደት እንዲጠብቅ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያጤን ኢትዮጵያ ጠየቀች። የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንቶች 6 ሚሊዮን ዶላር ለማጭበርበር የተደረገ ሙከራ ማክሸፉን አስታወቀ። ከ7 ሚሊዮን በላይ ደቡብ ሱዳናውያን የምግብ ዋስትና እጦት ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመድ አስጠነቀቀ። እስራኤል በጋዛ ወደምትገኘው ራፋ ያቀደችውን ወታደራዊ ዘመቻ አሜሪካ አሁንም እንደምትቃወም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገለጹ። ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የማረከቻቸውን የምራባውያን የጦር መሣሪያዎች፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች እና ወታደራዊ ሠነዶች በሞስኮ ለዕይታ አቀረበች።...more9minPlay
April 29, 2024DW Amharic የዓለም ዜና፤ የሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ--የአውሮጳ ህብረት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች የሚሰጠውን ቪዛ ለመገደብ መወሰኑን ዛሬ አስታወቀ። --በኬንያ ስምጥ ሸለቆ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝ አንድ ግድብ ተንዶ በትንሹ 42 ሰዎች ሞቱ። -ቡርኪናፋሶ ወታደራዊ ጁንታ የዶቼ ቬሌን ራድዮ ጨምሮ የተለያዩ ዓለምአቀፍ የዜና ማሰራጫዎችንና ጋዜጦችን ማገዱ አስታወቀ። -የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት ሲያበቃ፤ ከአረብ ሀገራት መሪዎች ጋር በጋዛ ጉዳይ ላይ ለመምከር በሳዑዲ ዋና ከተማ ሪያድ መግባታቸዉ ተዘገበ። ዝርዝሩን ያድምጡ!...more10minPlay
April 29, 2024DW Amharic የሚያዝያ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜናበኬንያ ከመጋቢት ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 76 አሻቀበ። ሱዳን በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች “ትንኮሳ” ላይ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በአስቸኳይ እንዲወያይ ጥያቄ አቀረበች። የፖርቹጋል መንግሥት አፍሪካውያን በባርነት ሲሸጡም ሆነ በቅኝ ግዛት ወቅት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ካሳ ለመክፈል ምንም አይነት ሒደት እንደማይጀምር አስታወቀ። ወግ አጥባቂው የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች በራፋ የታቀደው ወረራ ከተሰረዘ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁን መንግሥት እንደሚያፈርሱ ዛቱ። ሁለት ዩክሬናውያን በላይኛው ባቫሪያ በስለት ተወግተው መገደላቸውን የጀርመን ፖሊስ አስታወቀ።...more10minPlay
April 27, 2024የሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜናየኦፌኮ አመራሮች እስራት፤ የፓርቲው መግለጫሩዋንዳ፤ ለዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውንጀላ ምላሽ ሰጠች ቤኒን፤ ፖሊስ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሰሃማስ አዲሱን የእስራኤል የእርቅ ሃሳብ እንደሚያጤን አስታወቀየዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጥሪአትሌት መዲና ኢሳ በ 5ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች...more10minPlay
April 26, 2024የዓለም ዜና፦ ሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም.የሚያዚያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕሰተ ዜና የአፍሪቃ ሕብረት «የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው» በሚል የተሰራጨው መረጃ «የተሳሳተ» ነው ሲል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ። የሶማሊያ መንግሥት ራሽን በመስረቅ የተጠረጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሰለጠኑ የልዩ ኮማንዶ አባላት ማገዱንና ማሰሩን አስታወቀ። በጋዛ ሰርጥ አስቸኳይ ፣ቅድመ ሁኔታ የሌለውና ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ቻይና ጥሪ አቀረበች። የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ በጸጥታው ምክር ቤት የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እንዲቆምም ጠይቃለች።...more11minPlay
FAQs about የዓለም ዜና:How many episodes does የዓለም ዜና have?The podcast currently has 2,858 episodes available.