የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

Download on the App Store

የዓለም ዜና episodes

  • የመስከረም 22፣2017 የዓለም ዜና
    -የኢትዮጵያ መንግሥት የአማራ ክልል ነዋሪዎችን በጅምላና በዘፈቀደ ማሰሩ የሕግ የበላይነትን ይበልጥ መሸርሸሩን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።---የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ ደቡባዊ ሊባኖስ ዉስጥ በቅርብ ርቀት እየተዋጉ ነዉ።----በወርሮበሎች ጥቃትና አመፅ በተመሰቃቀለችዉ ሐይቲ ከ7 መቶ ሺሕ በላይ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀሉ ተነገረ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ካረቢያይቱ ሐገርን ከጥፋት ለማደን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አበክሮ መጣር አለበት።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር
    11 min
  • የመስከረም 20 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኻርቱም የሚገኝ የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት በወታደራዊ አውሮፕላን ተደብድቧል በሚል ያቀረበችውን ክስ የሱዳን ጦር አስተባበለ። በደቡብ አፍሪካ ምሥራቅ ኬፕ ክፍለ ግዛት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 አሻቀበ። ርዋንዳ ኃይለኛ ተላላፊ በሆነው ኢቦላ መሰል የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀች። እስራኤል ሊባኖስን በእግረኛ ወታደሮች ከወረረች ሒዝቦላሕ ለውጊያ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ሀገራቸው እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ልታዘምት እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ኢራንን አስጠንቅቀዋል
    11 min
  • የመስከረም 18 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ይጥሳል ሲሉ ከሰሱ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሀገራቸው “ዓላማ በቀጠናው የጋራ ዕድገት እና ብልጽግና መፍጠር” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ግምገማ ተስማሙ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በምትገኘው አል-ፋሽር ለሁለት ቀናት በፈጸመው ጥቃት 48 ሰዎች ተገደሉ። የሊባኖሱ ሒዝቦላሕ መሪው ሐሳን ናስረላሕ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።
    11 min

About የዓለም ዜና

From the publisher's feed

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት…