Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ፣ የአውሮፓ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዜናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ... more
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,994 episodes available.
April 17, 2026የሚያዝያ 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ዜና መጽሔትበዓለም ዜና የሚጀምረዉ የአንድ ሰዓቱ ስርጭታችን፤ በዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ 1, የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና መልስ የማግኛዉ መንገድ 2, በአማራ ክልል መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀያችን እንመለስ ጥሪ3, ሕገ ወጥነትን ሕግ እንዴት ይቆጣጠረው?4, በግጭት አፈታት እና በሰላም ግንባታ ላይ የተካሄደ ጉባኤ እንዲሁም 5, ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊነት የሚወዳደር የጋራ ዕጩ ያላፀደቀችዉ አፍሪቃ የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።...more21minPlay
April 16, 2026የዜና መጽሔት፤ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ሐሙስበአማራ ክልል ራያ ቆቦ ወረዳ በጸበል ቦታ በደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 8 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአደጋው ከ30 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም። የአዲስ ስታንዳርድ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ማኔጂንግ ኤዲተር ትላንት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከሥራ ገበታው ከተወሰደ በኋላ ዛሬም የደረሰበት አልታወቀም። ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ሁለት የፖሊስ መኮንኖች እና አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በታጣቂዎች ተገድለዋል። በዛሬው ዜና መጽሔት ከሚቀርቡ ዘገባዎች መካከል እነዚህ ይገኙበታል።...more29minPlay
April 15, 2026የሚያዝያ 7 ቀን 2018 የዜና ፅሔትበዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ኢሕአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በሚመለከት ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ መጻፉን ገለፀ፤ ደቡብ ወሎ ዞን ፓስፖርት ለማውጣት 161 ሐሰተኛ ሰነዶች፤ የኢራኑ ጦርነት፣ ለሱዳኑ ግጭት የሚሰጠው ትኩረት እንዲቀንስ ማድረጉ ተገለፀ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የመርከቦች እገዳ በፍኖተ ሆርሙዝ ለኢራን ምን አመጣ? ይሰኛሉ ዘገባዎቹ፣...more20minPlay
April 14, 2026የሚያዚያ 6 ቀን 2018፤ የዜና መፅሄትዜናውን ተከትሎ በሚቀርበው የዛሬ የዜና መፅሔታችን ፤መራጮች ምን ይላሉ?፣በነጻ የንግድ ቀጠና ባለሃብቶችን ከገቢ ግብር ነጻ የሚያደርገው መመሪያ፣በአማራ ክል ተፈናቃዮች የምግብ ዕርዳታ ከተሰጠን 2 ወራት አለፉ ማለታቸውን ፣እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዳስሱ ጥንቅሮች አካቷል።ሳምንታዊዎቹ ጤና እና አካባቢ እና አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅቶችም ተካተዋል።...more23minPlay
April 13, 2026የመጋቢት 5 ቀን 2018 የዜና መፅሔትዜና መጽሔት ጥንቅሩ፤ የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በሂደት የሚያስከትለው ጫና፤2, በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ነዋሪዎችን እየፈተነ ያለዉ የኤሌክትሪክ መቋረጥ፤ በተለያዩ የዓማር ክልል ከተሞች የንግድ ማህበረሰቡን የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ባለፈዉ ሰሞን በባሌ ሮቤ መናኸሪያ ላይ በወጣት ወንጀለኞች ተደበደቡት አባት የተሰኙ ርዕሶችን አካቷል።...more20minPlay
April 10, 2026DW Amharic የሚያዝያ 02 ቀን 2018 ዜና መጽሔትየነዳጅ እጥረት፣ የመጓጓዣ ዋጋ እና የጤፍ አቅርቦት፤ የመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ዋጋ መጨመር፤ ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ሕብረት የሠላምና ፀጥታ ምክር ቤት የአንድ ወር ሊቀመንበር ሆነች፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ተኩስ አቁም ያሳደረዉ ተስፋ በኢትዮጵያ፤ የአሜሪካና ኢራን ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት...more24minPlay
April 08, 2026የመጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ ም ዜና መጽሔትየዜና መፅሔት ዝግጅታችን፣የትግራይ ክልል ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የጄኔራል ታደሰ ወረደ ዘመነ-ሥልጣን ለተጨማሪ አንድ ዓመት መራዘሙንና ያስከተለዉን ቅሬታ የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል።በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞንን የመታዉ ድርቅ ከሁለት ወረዳ ብቻ ከ4000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸዉ ተሰምቷል።የአፍሪቃ ሕብረትና የኢትዮጵያ መሪዎች በአንጋፋዋ ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ሞት የተሰማቸዉን ሐዘን እየገለፁ ነዉ። ዜና መፅሔቱ ዩናይትድ ስቴትስ፣ እስራኤልና ኢራን ለሁለት ሳምንት ተኩስ ማቆማቸዉን፣ ምክንያቱንና የወደፊቱን ሁኔታ በተመለከተ ከባልደረቦቻችን ጋር የቀጥታ ዉይይት ይሰማበታልም።...more33minPlay
April 07, 2026የመጋቢት 29 ቀን 2018 የዜና መጽሔትበዜና መጽኄት አራት ዘገባዎችን እናስተነትናለን ። ዘገባዎቹ፦ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል?፤ በነዳጅ እጥረቱ የተስተጓጎለው ትራንስፖርትና መጪው የበዓል ሸመታ፤ የነዳጅ እጥረት በአማራ ክልል የፍትህ ስርዓት ላይ እንቅፋት እየሆነ ነው መባሉ ይሰኛሉ ። እንዲሁም የዪናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን የሰጡት ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ጫፍ መድረሱ እና ያጠላው ሥጋት የሚዳስስ ቃለ መጠይቅ ይኖረናል...more18minPlay
April 06, 2026የመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የዜና መጽሔትበዜና መጽሔት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ማራዘሙበመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በማዳበሪያ አቅርቦት ላይ የፈጥረው ተፅዕኖ የለም መባሉበአረብ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እሳት እየለበለባቸው የሚያገኙትን ገንዘብ እንዲያጠራቅሙላቸው ወደ አገር ቤት ሲልኩ መከዳታቸውየአሜሪካው ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ የባሕር በር ለመክፈት ስምምነት ላይ እንድትደርስ የሰጡት ቀነ ገደብ ነገ ያልቃል በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ከዋሽንግተን ዲሲ ወኪላችን አጭር ቆይታ ይኖረናል።...more18minPlay
FAQs about ዜና መጽሔት:How many episodes does ዜና መጽሔት have?The podcast currently has 1,994 episodes available.