Continental Drift

Continental Drift

Download on the App Store

All Continental Drift episodes

  • የባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና የዉዝዋዜዎች ኃይል - ማንነትን ለመግለጥና ለምጣኔ ኃብታዊ እድገት

    ኢትዮጵያ የብዝሃ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ተፈጥሮ ካደላት መገለጫዎቿ እኩሌታ ብዙኃ ቋንቋና ባህል ያላት መሆኑ የልዩ መልካነቷ ማሳያ ነው፡፡ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎቿም ትናንቷን የሚዘክሩ ፣ የነገን መልክ ዛሬ ላይ ለመቅረጽ በብዙ የሚጥሩ ናቸው፡፡ እንዴት ?

    “ አንደኛ የስራ እድል ምንጭ ይሆናል። የሚጫወቱ ሰዎች ቢበዙ የስራ እድል ነው ብዙ ሙዚቀኛ በዚህ ሙያ ላይ ያሉ ሙዚቀኞች እንደመኖሪያቸው ይሆናል። ሁለተኛ ደግሞ የሀገር ሀብት ነው። እንደ ሀገርም መሸጥ ይቻላል ሙዚቃን መሸጥ ይቻላል ፣ በነገራችን ላይ ያው [ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አንጻር] በተለያየ መንገድ ገቢ ማግኘት አለብን ብዬ አስባለሁ። እና አንደኛው ሙዚቃ ነው፡፡ ሙዚቃ በትልቁ ገቢ ማምጣት ይችላል ብዬ አስባለሁ ፤ ከሌላው አለም። ሙዚቃችንን ብንሸጠው እንደ ሀገር እንጠቀማለን። ዋናው ደግሞ የኢትዮጵያን ጥሩ ገጽታ ታስተዋውቂበታለሽ። ” ሲል የሙዚቃ አጥኚው እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡

    በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያዊያንን ማንነት ለመላዉ ዓለም ስለሚያንጸባርቁ ባህላዊ ዉዝዋዜዎች እና በኢትዮጵያዊያን መገለጫ ስለሆነው ዋሽንት አንስተን ስለባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችና ሁሉንአቀፍ አቅማቸው በሰፊው እንነጋገራለን ፤ ለዚህም የፈንዲቃ ባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ እና የሞሰብ ባንድ መስራች ጣሰው ወንድም ጋብዘናቸዋል፡፡

    ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

    1 hr
  • መጭውን ጊዜ መቅረጽ፡ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ፈጠራ ኢኮኖሚ
    ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ170 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከውጪ ለምታስገባው የእንጨት ዉጤቶች ወጪን ታወጣለች ።

     [...]መንግሥት የእንጨት ሥራ ውጤቶች ከውጭ እንዳይገቡ ለማድረግ ወይም ቢያንስ ለመቀነስ ዉሳኔ አሳልፏል። ነገር ግን በውስጡ ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ምክንያት ይህ ውሳኔ ተሰርዟል፣ የእንጨት ውጤቶች እንደገና ለማስገባት ተፈቅዷል። ነገር ግን ክልከላው በተጣለበት አስር ወራት ጊዜ ውስጥ እንኳን በሀገር ውስጥ ገበያው ፍላጎት ምክንያት ብዙ ሀገር በቀል የእንጨት ሥራ ውጤት ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየአቅጣጫው መጥተው አይተናቸዋል።” ሲሉ የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ።

    በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን የኢትዮጵያ የእንጨት ስራ ዉጤቶችና የፋሽን ዘርፍ ለሀገሪቱ የፈጠራ ኢኮኖሚ ያላቸውን ሚና ፣ ፈተናና እድሎች በሰፊው እንመለከታለን፡፡ ለዚህም የዋሪት ሙሉጥላ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ማህበር ፕሬዚዳንት ትህትና ለገሰ እና የፓራዳይዝ ፋሽን ባለቤትና ዲዛይነት ገነት ከበደን ጋብዘናቸዋል፡፡ 

    መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

    1 hr