Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።... more
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.
September 24, 2023«በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል ። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቋረጥ ይስተዋላል ።...more41minPlay
September 17, 2023አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?በሀገሪቱ በተለይ የመሰረታዊ ፍጆታ ቁሶች እና የቤት ኪራይ በየጊዜው ያለከልካይ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳዩ ሰራተኛው በወር በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ጭማሪ ስለመደረጉ ብዙም አይሰማም ወይም ቢኖርም ያለውን የገበያ እና የኑሮ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘቱ ነው የሚነገረው ።...more46minPlay
September 10, 2023የመጪው የ2016 ዓም ተግዳሮችና ተስፋ2015 ግጭቶች የተካሄዱበት፣ የመንግሥት ተባባሪ የነበሩ ውጊያ የገጠሙበት ፣ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የደረሰበት ፣ቤቶች የፈረሱበት ሰዎች የተፈናቀሉበት፣ የኑሮ ውድነት እጅግ የናረበት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ኢንተርኔትም የተቋረጠበት ዓመት ነበር። እነዚህ ችግሮች ወደ 2016 ዓም እንዳይሻገሩ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?...more42minPlay
August 27, 2023የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋንአዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?...more40minPlay
August 21, 2023እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?ተወያዮች፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተፈጥሮዉ መብት ገዳቢ ነዉ፤ኢትዮጵያም ተሞክሮ ይህንኑ ያሳያል። መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዝም ያለዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ ለሰላም ወደ ድርድር እንዲመጡ፤ጦርነትም ይቁም ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።መንግሥት የጅምላ እስሩን ያቁም፤የአማራ ክልልን ጥያቄዎች ይመልስ ብለዋል። እርሶስ? አስተያየት አሎት?...more43minPlay
August 14, 2023የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋበአማራ ክልል ሲብላላ የቆየው ቅራኔ በሣምንቱ መጀመሪያ ወደ ውጊያ ቢያመራም የመረጋጋት ዝንባሌ አሳይቷል። የቀውሱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው? በውይይት ካልተቋጨ በአማራ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ዳፋ ምን ሊሆን ይችላል? ዶክተር ታደሰ ጥሩነህ፣ ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።...more40minPlay
FAQs about እንወያይ | Deutsche Welle:How many episodes does እንወያይ | Deutsche Welle have?The podcast currently has 488 episodes available.