
Sign up to save your podcasts
Or


"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 7ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡7-13
ይህ ክፍል ለፊላዴልፊያ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
በክፍሉ ውስጥ የተመለከቱ 6 ነጥቦች፡
1) መግቢያ ስለ ፊላዴልፊያ ከተማ
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡7)
3) የምሥጋና መልዕክት (3፡8)
4) ጌታ ሊያደርገው ያለው ዕቅድ (3፡9)
5) ስለጌታ ጥበቃ የተሰጠ መልዕክት (3፡10)
6) እስከ መጨረሻ ስለመጽናት የቀረበ ምክር (3፡11)
7) ድል ለመንሳት የቀረበ የጥሪ መልዕክት (3፡12-13)
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 4፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ነፍስን በመተው ለዘላለም ህይወት መጠበቅ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ጌታ ስለሞቱ ዓላማ ከተናገረበት ክፍል 3 ነጥቦችን እንመልከት
2) ጠላትን በመውደድ ረገድ የጌታ ምሳሌነት
3) ህይወትን በመተው የመጠበቅ ቁልፍ
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ዮሐ. 12፡23-28/ ማቴ. 16፡24-27/ ዕብ. 12፡1-4/ ዮሐ. 10፡17-18/ ቆላ. 3፡1-2/1 ቆሮ. 12፡3
የጌታን መንገድ መከተል ተከታታይ ትምህርት
ክፍል 3፡ የጌታ መንገድ ባህሪያት፡ ጠላትን መውደድ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች፡-
1) ጠላት ምንድን ነው?
2) ጠላትን በመውደድ የጌታ ምሳሌነት
3) ጠላትን የመውደድ 5 ምክንያቶች
4) የካሪ ቡም ታሪክ - ጠላትን ይቅር ብሎ ስለመደድ
በዚህ ክፍል የተጠቀሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዮሐ. 13፡1-17/ ሉቃ. 23፡13-25፣ 32-34/ ማቴ. 27፡24-25/ ማቴ. 5፡43-48/ ዘሌ. 19፡18/ ሮሜ 12፡21/
"ኢየሱስ ማን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም በእምነት ካሳ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ ቆላ. 1፡13-18/ ዮሐ. 8፡58/ ማቴ. 1፡21-24/
በኢትዮጵያ ክርስቲያን ኅብረት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች መካከል የተደረገ ልዩና እግዚአብሔር የከበረበት የዕርቅ መርሃ ግብር።
“እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም። በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።”
መዝሙር 126:1-3
"ከተኩላዎች ተጠበቁ" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፣ ማቴ. 10፡16/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40/ ዮሐ. 10፡1-12/
"እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ መዝ. 100፡2-3/ መዝ. 23፡1-6/ ማቴ. 11፡28/ ኢሳ. 53፡6 / ኢሳ. 40፡11/ ዮሐ. 10፡27-29/ ማቴ. 25፡32-40
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 6ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 3፡1-6
ይህ ክፍል ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለሰርዴስ መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) መግቢያ ስለ ሰርዴስ ከተማ
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (3፡1) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ራዕ. 4፡7
3) የተግሳጽ/የነቀፋ መልዕክት (3፡2) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1ሳሙ. 17፡2፣ ማቴ. 25፡1
4) የምክር መልዕክት (3፡3ሀ) ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 1 ቆሮ. 15፡1፣ ፊልጵ. 4፡19
5) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (3፡3ለ)
5) የማበረታቻ መልዕክት (3፡4-5)
6) የጥሪ መልዕክት (3፡6)
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት 5ተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡18-29
ይህ ክፍል ለትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለትያጥሮን መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) መግቢያ ስለ ትያጥሮን ከተማ (ሐዋ. 16፡14)
2) ጌታ ራሱን የገለጠበት መንገድ (2፡18)
3) የምሥጋና መልዕክት (2፡19)
4) የተግሳጽ/የነቀፋ መልዕክት (2፡20-21)
5) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (2፡22-23)
5) የማበረታቻ መልዕክት (2፡24-28)
6) የጥሪ መልዕክት (2፡29)
"በመጠን ኑሩ" በሚል ርዕስ፣ በወንድም ተከለ ማርቆስ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
መሪ ጥቅስ፡ 1 ጴጥ. 4፡7-8
በመጠን ስንኖር ምን ይሆናል?
1) እንድንጸልይ ይረዳናል 1 ጴጥ. 4፡7-8
2) እንድንነቃ ይረዳናል 1 ተሰሎ. 5፡6-8
3) የጠላትን ሐሳብ እንድንገነዘብ ይረዳናል 1 ጴጥ. 5፡8
4) ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ መሆኑን እንድንገነዘብ ይረዳናል መክ. 3፡11
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days