
Sign up to save your podcasts
Or


"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሁለተኛው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 2፡1-7
ይህ ክፍል ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን የተላከ መልዕክትን ይመለከታል።
መልዕክቱ ውስጥ ያሉ 6 ነጥቦች፡
በዚህ ክፍል ውስጥ ጌታ ለኤፌሶን መልዓክ/አገልጋይ ያስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የሚከተሉት 6 ነጥቦች እንመለከታለን።
1) የምሥጋና መልዕክት (ቁ.2-3)
2) የተግሳጽ መልዕክት (ቁ.4)
3) የምክር መልዕክት (ቁ.5ሀ)
4) የማስጠንቀቂያ መልዕክት (ቁ. 5ለ፣ሐ)
5) የማበረታቻ መልዕክት (ቁ. 6)
6) የጥሪ መልዕክት (ቁ. 7)
"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 1 ሙሉ
ምዕራፍ 1 ውስጥ ልብ ማለት የሚገቡን 7 ነጥቦች፡-
1) የመልዕክቱ ባለቤት፡- እግዚአብሔር ራሱ ነው።
እግዚአብሔር > ኢየሱስ > መልዓክ > ዮሐንስ
2) የመልዕክክት ተቀባይ፦ ዮሐንስ ነው።
3) መልዕክቱን የተቀበለበት ቦታና ሁኔታ፦ ቦታው ፍጥሞ በተባለ ደሴት ሲሆን፣ በእሥር ላይ ሆነ ነበር መልዕቱን የተቀበለው።
4) የመልዕክቱ ዓላማ፦ ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እና የመልዕክቱ ተደራሲያን የሆኑ 7ቱ አቢያተ ክርስቲያናትን ለማንቃት ነው። በተጨማሪም በመጨረሻው ዘመን በዓለም ላይ ሊሆን ያለውን ለማመልከት ነው።
5) ሰባት ቁጥር በመጽሐፉ ውስጥ መደጋገሙ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው። በተጨማሪም ብፁዓን የሚለው ቃል ራሱ 7 ጊዜ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተደጋግሟል።
6) ኢየሱስ ለሐዋሪያው ዮሐንስ ከዚህ በፊት ባልተለመደ አቀራረብና መንገድ ራሱን ገልጧል። ለምሳሌ መልኩን ለመግለጽ ሐዋሪያው የተጠቀመባቸውን አገላለጾች ልብ ማለት ይቻላል።
7) ጌታ ወደ ዮሐንስ ሲመጣ ዮሐንስ የነበረበት ሁኔታ፦ ስለክርስቶስ መከራን እየተቀበለ ያለበት ሁኔታና በዚያ ችግር ውስጥም ቢሆን በጌታ ቀን በመሆን ከመሆን እንዳላገደው እንመለከታለን።
"በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መኖር" በሚል ርዕስ በ1 ሳሙ. 1-3 ባሉት ምዕራፎች ላይ ተመሥርቶ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"ራስንና የራስን ሚና ማወቅ" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ ያታሣ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ ዮሐ. 1፡19-28፣ 35-37
ነህምያ ምዕራፍ 1-8 ላይ ተመሥርቶ በአገልጋይ ሄለን መስፍን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ?" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የአመት መጨረሻ መልዕክት።
ዳዊት እስከዚህ ያደረስከኝ እኔ ማን ነኝ ያለባቸው ምክንያቶች፡-
1) ለንግሥና መመረጡና መቀባቱን አስቦ ነው 1 ሳሙ. 16፡ 1፣13
2) የእግዚአብሔርን ምህረት እያሰበ ነው 2 ዜና 21፡1፣13
3) የእግዚአብሔርን ጥበቃ እያሰበ ነው መዝ. 23
4) የእግዚአብሔርን እርዳታ እያሰበ ነው
መጪው አመት የብርታት አመት ነው
1 ነገ. 2፡1-3
1) የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ እንበርታ
2) በእግዚአብሔር ጸጋ እንበርታ (ዕብ. ፡1)
"የምንሻገረው ለምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በፓስተር ኃይላቸው ታየ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት።
"በመንፈስ ኃይል መሻገር" በሚል ርዕስ በማቴ. 14፡22-27 ባለው ክፍል ላይ በፓስተር ኃይላቸው ታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር መልዕክት።
"የዕንባቆም ክርክርና የእግዚአብሔር መልስ" በሚል ርዕስ በትንቢተ ዕንባቆም ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛውና የመጨረሻ ክፍል።
"የዕንባቆም ክርክርና የእግዚአብሔር መልስ" በሚል ርዕስ በትንቢተ ዕንባቆም ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል።
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days