Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 185 ለሚያምን ሁሉ ይቻላል! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

    "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። 

    ማር. 9፥2-25፣ ዘፍ. 17፥1 

    1) ለሚያምን መዳን ይቻላል / ሉቃ. 18፥18-27፣ ማር. 16፥16 

    2) ለሚያምን ለእግዚአብሔር ካህን መሆን ይቻላል / ራዕ. 1፥5-6፣ 1 ጴጥ. 2፥9 

    3) ለሚያምን እባቡን እና ጊንጡን መርገጥ ይቻላል / ራዕ. 12፥9፣ ሉቃ. 10፥19 


    58 min
  • 182_ቀናችንን እንዋጅ በእህት ለምለም ጌታቸው (ሲ/ር)

    182_ቀናችንን እንዋጅ   በእህት ለምለም ጌታቸው  (ሲ/ር)

    ዘመናችንን ለመዋጀት ስናስብ ቀናችንን  እንዋጅ በ ኤፌ 5:8-17 በዘፍ 1:1-5 እና ፊል 4:9 ላይ የተመሰረተ  የእ/ር ቃል መልእክት  

    "ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥  ....

    ....እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤

    ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።" ኤፌ 5:8-17

    "በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።

    እግዚአብሔርም። ብርሃን ይሁን ኣለ፤ ብርሃንም ሆነ።  እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፤ እግዚብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።

    እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።"ዘፍ 1:1-5

    በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ፊል 4:9

    38 min
  • 181_መታዘዝ (ክፍል 2) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር )

    181_መታዘዝ (ክፍል 2) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር  )

    ለመታዘዝ ምሳሌያችን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ::

    እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌ 2:10

    ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን። ያዕ 1:18

    ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም። ዕብ 11:31

    47 min
  • 180_መታዘዝ (ክፍል-1) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)

    180_መታዘዝ (ክፍል-1) ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር

    በግላችን ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ምን እንማራለን:: መታዘዝ የበረከትም መንገድ ነው

    ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።ዮሐ14:15

    እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ :- ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።ሮሜ 12.1

    እንዲህም አለው፦ እግዚአብሔር፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ አንድ ልጅህንም አልከለከልህምና

    በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤

    የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።

    ዘፍ 22:16-18

    1 hr
  • 179_ ከእኔ ተማሩ (ክፍል 6) ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)

    179_ ከእኔ ተማሩ (ክፍል 6)  ዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)

    ክፍል 6 ከእኔ ተማሩ በዘገየ መኮንን (ወ/ዊ)

    መንፈስ ቅዱስን ከጌታ እንማር

    ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ። ሉቃ 2:40

    በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፥... ኤፌ 3:16

    46 min