Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 140 ጌታ እኮ ነው - መልሶ ያቆማል!

    "ጌታ እኮ ነው - መልሶ ያቆማል!" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ጥናት የመጀመሪያው ክፍል::

    ተጨማሪ ጥቅሶች: ዮሐ. 20፡30፣31 / ማቴ 4:18-20/ ማቴ 16:16, 22, 23/ ሉቃ. 22:33, 56-61

    1 hr 10 min
  • 139 ታማኝ ባሪያ || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

    "ታማኝ ባሪያ" በሚል ርዕስ በማቴ. 25:14-30 ባለው ክፍል ላይ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::

    ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ኤፌ 4፡6-8/ 1 ቆሮ. 12፡4-11/ ዕብ. 3፡2-6/ 1ቆሮ. 4፡17/ ኤፌ. 6፡21/ 1 ጴጥ. 5፡12/ 3ኛ ዮሐ. 1፡5

    55 min
  • 136_የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? በወንድም ያቬሎ ናታዬ

    136_የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? በወንድም ያቬሎ ናታዬ

    "እውነተኛ አምላክ ብቻየሆንክ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት::" ዮሐ17:3  ላይ የተመሰረተ የእለቱ ከ እግዚአብሔር ቃል መልእክት

    ሰዎች የዘላለምን ሕይወት እንዴት ያገኛሉ?

    1. እውነተኛ  የሆነውን እግዚአብሔር አምላክ እርሱን ማወቅ:

    ስለ እግዚአብሔር ማወቅ እና እግዚአብሔርን ማወቅ ይለያያልና::

    2. ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ማወቅና ማመን እና መቀበል

    መልእክተኛ የ እግዚአብሔር ልጅ እርሱ ኢየሱስ እንደሆነ ማወቅ

    1 hr 5 min
  • 131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)

    ጌታ ቅርብ ነው  በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)

    በአባቶች ቀን ፕሮግራም ላይ  በፊሊ 4:6 ላይ የተመሰረተ ከ እ/ር ቃል መልእክት የቀረበ

    "ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።

    አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።"ፊሊ 4:4-6

    "እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።  እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።"ኤር 29:12-13

    "እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።"ዘፍ 8:21

    "ኢየሱስ ግን፦ አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ።  ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።"ሉቃ 8:46

    40 min