Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 120_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 2 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ

    ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: -

    ርዕስ: ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ

    1) መግቢያ

    2) በልጆች ጉዳይ ወላጆች ላይ መሥራት የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶች

    3) በልጆችና ወላጆች መካከል ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር የሚያደርጉ ነገሮች

    4) ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ጤንነት ለመጠበቅ የሚረዱ ነገሮች

    1 hr 47 min
  • 119_ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት || ክፍል 1 || ዶ/ር ሙላቱ በላይነህ

    ይህ ትምህርት ጤናማ ቤተሰባዊ ግንኙነትን መገንባት በሚል ርዕስ፣ የቤተሰብና ጋብቻ አማካሪ በሆነው በዶ/ር ሙላቱ በላይነህ በፊንላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የቀረበ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው:: በዚህ ክፍል የሚከተሉት ዋና ዋና አሳቦች ተዳስሰዋል: -

    ርዕስ: ባልና ሚስት እርስ በርስ ያላቸውን የግንኙነት ጤንነት መጠበቅ

    1) የትምህርቱ ዓላማዎች

    2) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ ሁለንተናዊ አሉታዊ ተጽዕኖዎች

    3) የጤናማ ግንኙነት ወይም ትዳር (መኖር/አለመኖር) መለኪያ መስፈርቶች

    4) ግንኙነቶቻችንን ሊረብሹ የሚችሉ የታወቁ ምክንያቶች

    5) የትዳርና የቤተሰብ ግንኙነትን ጤንነት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች

    2 hr 19 min
  • 118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን

    118_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 3 / በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን 

    10. በጊዜውም ያለጊዜውም ቢመችም ባይመችም ተዘጋጅቶ መኖር 2 ጢሞ4:2

    11. እስከ መጨረሻው መጽናት ማቲ 10:22

    እንድንፀና የሚረዱን 4 ነገሮች

    1 . የእግዚአብሄር ቃል በመታዘዝ ማቲ 7:26 እና 1 ዜና 28:5-7

    2. ፀሎት  1ጴጥ  5:10

    3. የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ  ሐዋ 1:8

    4. ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች  ሉቃ 22:32

    37 min
  • 117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ

    117_ፅና ወይም ፅኑ ክፍል 2 / በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ

    እንድንጸናባቸው ከታዘዝንባቸው 6 ነገሮች የመጀመሪያዎቹ 4ቱ

    በ 2ቆሮ 12: 9 እና ምዕ 8:1 ጀምሮ ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ

    6.በጸጋ መጽናት

    7.በፍቅር መጽናት

    8.በአገልግሎት መጽናት

    9.በወንጌል እውነት መጽናት

    38 min
  • 116_ፅና ወይም ፅኑ በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/

    116_ፅና ወይም ፅኑ  በዘገዬ መኮነን/ወንጌላዊ/

    ፅና ወይም ፅኑ  በኢያሱ 1:6 እና  በዘዳ 31:7 ላይ የተመሰረተ የእ/ር ቃል መልእክት

         መፅናት በግል: በቤተሰብ: በሕብረት

         መፅናት ለአማኞች የተሰጠ ትእዛዝ ነው::

    ሀ.በመፅናት ምሳሌ የሆኑን :

         ሐና: ዳዊት: አሳ

    ለ.እንድንፀናባቸው የታዘዝንባቸው ነገሮች

         1.  በተስፋ መጽናት

        2. በእምነት መጽናት

        3. በጸሎት መጽናት

    4. በፈተና መጽናት

    5. በትእግስት መጽናት

    41 min
  • 115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን || ክፍል 2 || ያቬሎ ናታዬ

    115_ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግሮቻችን /ክፍል 2  / ያቬሎ ናታዬ

    የንግግሮቻችን 7 መመዘኛዎች

    1- እያንዳንዱን ሰው ታሳቢ ማድረግ አለበት :

    2-አውዳዊ ስልትን የተከተለ መሆን አለበት

    3-እውቀትን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት

    4-ትክክለኛ መልእክት የያዘ መሆኑን መረጋገጥ አለበት

    5-ሁልጊዜ ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን አለበት

    6-ንግግራችን የተቀመመ መሆን መረጋገጥ አለበት

    7-ጸጋን የተሞላ መሆን አለበት

    በጠብ ሳይሆን በጥበብ ለመመላለስ ንግግራችን እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል::

    ቆላ 4:5-6 በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል መልእክት ላይ የተመሰረተ

    1 hr
  • 114_ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10 በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን

    114_ ራዕይ ምዕ 5 ቁ 1-10  ባለው ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት /በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን

    መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።ራዕ 5:9-10

    1. ጥቅልሉ መጽሐፍ ራዕ 5: 1-3

    2. ከሽማግሌዎች አንዱ  ራዕ 5: 4-7

    3. ለበጉ ክብር የምስጋና ዝማሬ ራዕ 5: 8-10

    47 min
  • 113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን || ክፍል 1 || በወንድም ያቬሎ ናታዬ

    113_ ዘመኑ: በውጪ ያሉ ሰዎችና ንግግራችን    ተከታታይ ትምህርት :: በወንድም ያቬሎ ናታዬ

    ዘመኑን እየዋጃችሁ: በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ ::

    "ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመላለሱ እንደሚገባ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ :በጨው እንደ ተቀመመ :በጸጋ ይሁን"::ቆላ 4:5

    ክፍል 1

    1:1 ዘመኑ ምን አይነት መልክ አለው? የሚዋጅ ዘመን  በኤፌ 5:15 እና 2ኛ ጢሞ3:1-5 ላይ የተመሰረተ ቃል::

    1)ዘመኑ የሚዋጅ ነው 2) ዘመኑ ክፉ ነው  3)ዘመኑን ዋጁ

    1-2 ዘመኑን የምንዋጀው እንዴት ነው? በውጪ ባሉት ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ::  ቆላ 4:5

    1)ዘመኑን መልክ በመረዳት 2)የራሳችንን ሓላፊነት በሚገባ በመወጣት 3)ቃሉ በሚሰጠን መመሪያ መሰረት ወደ እርምጃ መግባት

    1-3 ትእዛዙን ተፈጻሚ የምናደርገው በ እነማን ዘንድ ነው? የእግዚአብሔርን ፈቃድ በንግግራችን ውስጥ::  ኤፌ 5:17

    በጥበብ መመላለስ

    ከማያምኑት ጋር ባለን እለታዊ መስተጋብር

    በስራ:በሰፈር...

    58 min
  • 112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/

    112_እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: በዘገዬ መኮንን /ወንጌላዊ/

    1/ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው :: እግዚአብሔር ስሙን ከፍ ለማድረግ ይዋጋል::  ዘጸ 15:1-3

    እግዚእብሔር  ያለማንም ጣልቃ ገብነት  ለህዝቡ ብቻውን ተዋግቶ : ድል ሲነሳ ስላዩ: ሙሴና የእስራኤል ህዝብ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው" አሉት::

    2/ እግዚእብሔር  የራሱን ህዝብ ከጠላቶቻቸው ጥቃት ለመታደግ 2ዜና 20: 14-15

    3/ እግዚእብሔር ህዝቡን ወደ አሰበለት ስፍራ ለማስገባት:: ዘጸ 14: 14-23

    1 hr 5 min
  • 111_እግዚአብሄር መሐሪ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን

    111_እግዚአብሄር መሐሪ   በወንጌላዊ ዘገዬ መኮነን

    የእግዚአብሄር መሐሪነት የገባው እግዚአብሄር የሚምር የሚራራ መሆኑንን የተረዳው አብርሃም ስለሌሎች ያደረገውን ጸሎት እና ልመና ላይ የተመሰረተ ቃል ነው:: እኛም የእግዚአብሄር ምህረት እንደገበው ሰው እግዚአብሄር ለብዙዎች ምህረትን እንዲያደርግ  አጥብቀን እንጸልይ ዘንድ ያስፈልገናል::

    51 min