
Sign up to save your podcasts
Or


ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት አምስተኛውና የመጨረሻው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 5: የሰው ዋጋ
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ አሳቦች: -
-–ሌሎች ሥልጣኔዎችና ባህሎች ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–እስልምና ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–ምዕራባዊያን ስለሰው ዋጋ ያላቸው ዕይታ
–መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰው ዋጋ ምን ያስተምራል?
–መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ዕይታ መከተል ያሉት ክትለቶች (implications)
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት አራተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 4: "ሰው ሰው የሆነው ለምንድን ነው?/ሰው የተፈጠረበት ዓላማ ምንድን ነው?"
ሰው በዋናነት የተፈጠረው ለኅብረት የሚለው አሳብ በስፋት ይተነተናል::
1) ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የወደ ላይ ኅብረት
2) ሰው ከሌሎች ሰዎችና ከተፈጥሮ ጋር ያለው ኅብረት
3) የክርስቶስ መስቀል ምሳሌነት ለሁለቱም የሰው የኅበረት አቅጣጫዎች
4) ፍቅር - ኅብረትን መተግበሪያ ዓይነተኛ መሣሪያ የሚሉ አሳቦች በስፋት ተዳስሰዋል::
የጌታ መንገድ በሚል ርዕስ በወንድም አስቻለው ወልዴ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች: ዮሐ. 14:6/ ማቴ. 18:21-35 / ገላ. 5:19-21
"የልብ መዝገብ ቢከፈት ምን ይወጣል?" በሚል ርዕስ በ2ኛ ዜና 5 ላይ ተመሥርቶ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመልዕክቱ ጭብጥ: ቁጣንና ጦርነትን የሚያስቀር የልብ መዝገብ አለ/በተቃራኒው ደግሞ ቁጣና ጦርነትን የሚቀሰቅስ የልብ መዝገብ አለ/ለፈውስ የሚሆን የልብ መዝገብ አለ/ለደዌ የሚዳርግ የልብ መዝገብ አለ::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 2 ነገ. 5:1> /ምሳ. 20:21 /1 ነገ. 19:15-19 /ሉቃ. 6:43-45
"እግዚአብሔር ያያል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ ፋሼ (ዶ/ር) የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱድስ ጥቅሶች: ዘፍ. 16:1-16/ኢዮብ 40:1-2/ኢዮብ 42:1-6/ሮሜ 5:3-4/
"የመጥምቁ ዮሃንስ ምስክርነት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
በዮሐ 1:20-30 እና በሉቃስ 1:76 ላይ ባለው የእግዚአብሄር ቃል ላይ የተመሰረተ መልእክት::
"የሚያስፈልገው ጥቂት ነው!" በሚል ርዕስ በሉቃ. 10:38-42 ባለው ክፍል ላይ ተምሥርቶ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: ሉቃ. 10:38-42/ኢየሱስ በነ ማርታና ማሪያም ቤት || 1 ነገ. 17:7-14/ነቢዩ ኤልያስና የሰራፕታዋ ባልቴት || ማቴ. 15:32-38/ኢየሱስ 4000+ ሰዎችን በሰባት እንጀራና በጥቂት ዓሣ መመገቡ || መዝ. 37:16 ||
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሦስተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 3: "ሰው መንፈስ ነው፤ ነፍስ አለው፤ በሥጋ ውስጥ ይኖራል!" ባዮች ስህተታቸው ምንድን ነው?
1) የቃል እምነት እንቅስቃሴ ስለሰው ምንነት ያላቸውን አመለካከት በጥልቀት እንመለከታለን
2) የሚጠቅሷቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችና እንዴት እንደተሳሳቱ እንመለከታለን::
3) ከስህተት ራሳችንን ለመጠበቅ ከእያንዳንዳችን ምን እንደሚጠበቅ እንመለከታለን::
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች / ዘፍ. 1:26-27 / መዝ. 82:1-8 / ዮሐ. 10:34-36 / ዮሐ. 3:1-6 / ዕብ. 4:12 / 1 ጢሞ. 4:12 / 2ጢሞ. 2:14 /
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 2: ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሰው ምንነት ዕይታ
ሀ) ሰው በትክክል ምንድን ነው?
ለ) የሰው ማንነት ክፍሎች
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች: 1 ተሰ. 5:23/ዕብ. 4:12/ኢዮብ 32:8/ሉቃ. 9:56/ማር. 14:34/ሉቃ. 23:46/ሐዋ. 7:59/መክ. 12:7/ፊል. 3:20-21
ይህ "ሰው ምንድን ነው?" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያው ክፍል ነው::
ዘፍ. 1:26-28/ዘፍ. 2:7
በዚህ ክፍል የተዳሰሱ ዋና ዋና አሳቦች:-
ርዕስ: ሰው ምንድን ነው?
ክፍል 1: ዓለም ለሰው ያላት ዕይታ
1) የማቴሪያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ
2) የአይዲያሊዝም ንጽረተ ዓለም አራማጆች ስለሰው ምንነት ያላቸው ዕይታ
3) ክርስቲያናዊ የሰው ምንነት ዕይታ
From the publisher's feed
Ranked by our users in the last 21 days