Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 30_ንጉሥ ለሚወደው ሰው እንዲህ ይደረግለታል!

     

    "ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይደረግለታል!" በሚል ርዕስ በአስቴር ምዕራፍ 6 ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ ንጉሥ ሲወድ በንጉሥ አቅም ልክ መሆኑን ለማስገንዘብና እኛም በእግዚአብሔር የተወደድነው ለመረዳት ከአቅም በላይ በሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን ማስገንዘብ ነው::  

    53 min
  • 29_የእግዚአብሔር ክብር

     

    "የእግዚአብሔር ክብር" በሚል ርዕስ በፓስተር ዮሴፍ ፈንታው በ2ኛ ዜና 7:1-10 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ሲሆን በመልዕክቱም የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የሚሆኑ 4 መሠረታዊ ነገሮች ተዳስሰዋል::

    51 min
  • 28_ምርኮው ይመለሳል!

     

    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ምርኮው ይመለሳል"  በሚል ርዕስ በ1ሳሙኤል ምዕራፍ 30 ላይ ተመሥርቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ማዕከላዊ አሳብ "ነገራችን በጠላት ሲወሰድብንና የሚናደርገው ግራ ሲገባን 1) ልባችንን በእግዚአብሔር ማበርታት አለብን 2) ማድረግ የሚገባንን እንዲያሳውቀን እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ አለብን 3) ምርኮአችንን ለመመለስ እግዚአብሔር አድርጉ የሚለንን ማድረግ አለብን" የሚል ነው:: 

    45 min
  • 027_ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል!
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ህዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" በሚል ርዕስ የገና በዓልን አስመልክቶ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የመልዕክቱ ዋና ማዕከላዊ ትኩረት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋና ዋና ዓላማዎች መተንተን ነው::
    44 min
  • 026_ምንጭ
    ይህ የእግዚአብሔር መልዕክት "ምንጭ" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ ሲሆን የካሌብ ሴት ልጅ በነበረችው በአክሳ ህይወት ላይ ተመሥርቶ የቀረበ ነው:: የመልዕክት ዋና መልዕክት ስለምንጭ አስፈላጊነት ነው [ኢያ. 15.16-19ና መሳ. 1:11-15]:: ምንጭ ለአንድ የእርሻ መሬት ፍሬያማነት አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም በአንድ ሰው ህይወት ውስጥ ላለ የእግዚአብሔር ጸጋ ፍሬያማነት እጅግ አስፍላጊ ነው::
    49 min
  • 025_ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል?
    ይህ መልዕክት "ምን አላችሁ? ምን ይዛችኋል?" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ ሲሆን የመልክቱ ማዕከል እግዚአብሔር ባልተጠበቀ ሁኔታ ወስጥ ባልተጠበቁ ሰዎች ሌሎችን መርዳት እንደምችል የሚያስረግጥ መልዕክት ነው:: ለምሳሌ: 1) አንድ ህጻን ልጅ በያዘው ዳቦና ዓሣ አምስት ሺህ ህዝብ መመገቡ 2) በሰታፕታ መንደር እፍኝ ዱቀት ብቻ በነበራት ባልተት ኤልያስን መመገቡና 3) ባዶ የሚመስል የዘይት ማድጋን ተጠቅሞ የነቢይ ሚስት የነበረችን ባልቴት ባለዕዳ ልጆቿን እንዳይወስድባት መርዳቱ::
    49 min
  • 24_እግዚአብሔርን መከተል
    ይህ "እግዚአብሔርን መከተል" በሚል ርዕስ በወ/ዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት ነው:: መልዕክቱ በኦሪት ዘኁልቁ ምዕራፍ 13 ላይ የተመሠረተ ሲሆን ማዕከላዊ አሳቡም እግዚአብሔርን በመከተል ሂዴት ውስጥ ትኩረታችን መሆን ያለበት ዙሪያችን ላይ በሚታየው ላይ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰጠን የተስፋ ቃል ላይ ነው የሚል ነው::
    57 min
  • 023_የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች
    "የመንግሥተ ሰማያት መክፈቻዎች" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው::
    የመልዕክቱ ጭብጥ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሥራ ለመሥራት የሚረዱ ቁልፎች 1) የእግዚአብሔር ቃል 2) የኢየሱስ ስም 3) ጸሎትና 4) መንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ማስገንዘብ ነው::
    1 hr 9 min
  • 022_የአካል መታነጽና መክበር
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የአካል መታነጽና መክበር" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ እግዚአብሔር በቃሉና በመንፈሱ አማካይነት ቅዱሳንን ያንጻል የሚል ነው::
    44 min
  • 021_ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል" በሚል ርዕስ በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) የቀረበ ነው:: የመልዕክቱም ዋና ጭብጥ የአካል ብልቶች ሁሉ ለአካላቸው ህልውና መቀጠል ተግባብተውና ተሳስበው እንደሚሠሩ፣ በቤተ ክርስቲያን ያሉ አማኞችም የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ህያው ሆና ተግባሯን በሚገባ መፈጸም እንድትችል በመተሳሰብ አብረው ለአንድ ዓላማ ሊቆሙ ይገባል የሚል ነው::
    1 hr 1 min