Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

Download on the App Store

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland episodes

  • 020_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 3
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ባልንጀራችንን እንደራሳችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? ባልንጀራችንስ ማን ነው? ባልንጀራችንስ እንደራስ መውደድ ይቻላል ወይ? ባልንጀራችንን እንደራስ መውደድ የሚገለጽባቸው መንገዶችስ ምን ምን ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::
    1 hr 8 min
  • 019_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 2
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት ሁለተኛው ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔርን በሁለንተናችን መውደድ ያለብን ለምንድን ነው? የሰው ሁለንተናስ ምንድን ነው? እግዚአብሔርንስ በሁለንተናችን መውደድ የምንችለው እንዴት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን መመለስ ነው::
    1 hr 2 min
  • 018_የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች ክፍል 1
    ይህ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት "የእግዚአብሔር ህግጋት ማዕከላዊ እሳቤዎች" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ እየቀረበ ያለ ተከታታይ ትምህርት የመጀመሪያ ክፍል ነው::
    የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ለህዝቡ የሰጣቸውን ህጎች መዳሰስ ነው:: እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራ በተሻሩና ባልተሻሩ የእግዚአብሔር ህጎች መካከል መለየት ነው::
    1 hr 15 min
  • 017_በመንፈሱ መታጠቅ!
    በዮሐንስ ወንጌል 21:15-19 ባለው ክፍል ላይ ተመሥርቶ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና ጭብጥ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ በሥጋ ማንነቱ የሚፈራውን በመንፈስ ቅዱስ ሲታጠቅ እንደማይፈራና ለእግዚአብሔር ክብር እስከ ሞት ድረስ እደሚጨክን ያስረዳል:: በመንፈስ ቅዱስ መታጠቅ ፈሪን ደፋር ያደርጋል:: ለዚህም የጴጥሮስን ህይወት ልብ ይሏል::
    1 hr 1 min
  • 016_ይቅርታ
    "ይቅርታ" በሚል ርዕስ በሉቃ. 23:32-43 እና ማቴ 6:14-15 ባለው ክፍል ላይ የተመሠረተና በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
    41 min
  • 015_ዘመኑን ማወቅ
    "ዘመኑን ማወቅ" በሚል ርዕስ በእህት ለምለም ጌታቸው የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: የመልዕክቱ ዋና በዘመናት መካከል ህዝቡን አገሮችን እና ቤተሰቦችን በማስተዋልና በጥበብ ለመምራት እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚያስነሳ የሚያገነዝብ ነው:: በዘመናችንም ምልልሳችን በጥበብና በማስተዋል መሆን እንደሚገባና ጥበብንም ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠየቅ እንደሚቻል ይመክራል::
    30 min
  • 014_በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል
    "በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገዬ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት::
    የመልዕክቱ ዋና አሳብ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በአማኝ ህይወት ውስጥ የሚያደርጋቸውን ለውጦች የሚያስረዳ ነው::
    45 min
  • 013_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 3
    "የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻ ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ምዕመናን መሪዎችን በመምረጥ ጉዳይ ልዩ ጥንቃቄ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ማስገንዘብና ትክክለኛ መሪዎችን መለየት የሚችሉባቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመዘኛዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::
    1 hr 9 min
  • 012_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 2
    "የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ለሰው የተሰጡ አራት የሥልጣን ደረጃዎችን መተንተንና ከሰው ሥልጣን ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን መጠቆም ነው::
    1 hr 6 min
  • 011_የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን ክፍል 1
    "የሥልጣን አጠቃቀም በቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ በወንድም ያቬሎ ናታዬ የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት:: ይህ መልዕክት "ቤተ ክርስቲያን" በሚል ርዕስ እየቀረበ ያለው ተከታታይ ትምህርት ክፍል ነው:: የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት ከሰው በላይ የሆኑና የእግዚአብሔር ብቻ ስለሆኑ የሥልጣን ደረጃዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው::
    1 hr 3 min