Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣... more
FAQs about Sovereignty Sources:How many episodes does Sovereignty Sources have?The podcast currently has 119 episodes available.
September 10, 2025ለምንም የውጭ እርዳታ እና ገደብ ፦ ኢትዮጵያን በውስጣዊ አቅሟ መተማመንን ያረጋገጠችበት ግድብ''የህዳሴ ግድብ መሠራት አንዱ ሞዕራፍ ነው። ወንዙ ግን የኢትዮጵያ ልብ ውስጥ ከፍተኛ፣ ሚና ያለው የሶሺዮ - ፖለቲካ መገለጫ፣ የኢትዮጵያ ማንነትና ባህል ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያለው ነው - ብለዋል የውጭ ጉዳዮች ኢንስትቲዩት ምክትል ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አብዲ ዘነበ።''ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፡-''አባይ፣ በአፍሪካ ትልቁ ግድብን መገደብ ከተቻለ፣ ሌሎች ግድቦችን ለመገንባት የሚያግደን ምንም ነገር የለም።''የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በይፋ መመረቁን መሠረት አድርገን ከውጭ ዕርዳታ ውጪ በሰፋ የህዝብ ተሳትፎ መሠራቱ ያለው አንድምታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በሰፊው እንዳስሳለን። የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው፣ የውጭ ጉዳዮች ኢንስትቲዩት ም/ዳይሬክተር ዶ/ር አብዲ ዘነበ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በተጨማሪም ዶ/ር ኢንጂነር ታምሩ ተሠማ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እና ተስፋዬ ዳኜ ድሪባ፣ በስፔስ ስሳይንስና ጂዮስፓሺያል ተቋም የዲጂታል ኢሜጅ ፕሮሰሲንግ ሊድ ኤክስኪዩቲቭን ጋብዟቸው በጥልቀት አወያይቷቸዋል።...more1h 0minPlay
September 08, 2025አረንጓዴ አሻራ፡ አካባቢን ከጥፋት ለመታደግ የሚደረግ ችግኝ የመትከል ዘመቻ“በአረንጓዴ አሻራው ደስተኛ ነኝ፣ እናም የኢትዮጵያን አርአያነት በመከተል ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ቢያንስ በወር አንዴ ተግባራዊ ልናደርገው የተገባ ነው'' ሲሉ ሚስ ጆይስ ሜንዴዝ ኮል ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በኢትዮጵያ ለተከታታይ ዓመታት እየተተገበረ ያለውን የአረንጓዴ አሻራን፣ የአፍሪካ የሴቶች ቀን እና ስለ ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች በሶስት ክፍሎች ለመወያየት የአፍሪካ የሴቶች አመራር ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር ሚስ ጆይስ ሜንዴስ ኮልን ጨምሮ በርካታ እንግዶችን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
September 05, 2025የኢትዮጵያ እግርኳስ እና የአፍሪካ ጨዋታዎች መልክየአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት፣ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ፣ ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የውጭ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች በኢትዮጵያ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደ ሚካኤል፣ የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ እና የፓን አፍሪካ ፉትቦል ጸሐፊው ኦምና ታደለን በጥልቀት አወያይቷቸዋል።...more1h 0minPlay
September 03, 2025የኢትዮጵያ የጤና ስርዓት ወደ ቱሪዝም መዳረሻነት የመለወጥ ተስፋዎች“የጤና ስርዓት ቱሪዝምን መገንባት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የሰው ኃይልን መገንባት ስለሚኖርብን። ብዙ ሙያተኞቹን እያበቃን ነው። ብቃት ያላቸው በርካታ ሀኪሞች እየተፈጠሩ በመሆናቸው በየቦታው ሙያቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛሉ። ስለዚህ መሠረተ ልማቶችና ማዕከላት ለጠቅላላ ሀኪሞችና ስፔሻሊስቶች ምቹ ከሆኑ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ በርካታ የውጭ ዜጎችን ለህክምና እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል" ብለዋል የኢትዮጵያ ጋስትሮኢንትሮሎጂ ማኅበር ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ካሳ ታምሩ።በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች በተለይም እንደ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ሶማሌ ላንድ ያሉት የተሻለ ህክምና ለማግኘት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኢትዮጵያን ተመራጭ እያደረጓት ነው ።በህክምና ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢ የኢትዮጵያ ጋስትሮኢንትሮሎጂ ማኅበር ኤክስኪዩቲቭ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊው ዶ/ር ካሳ ታምሩ፣ የላንሴት ሆስፒታል ማዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አቤል ሀይሉ፣ የኦፕታልሚክ ሰርጅን ኮርኒያ የዓይን የውጭ ክፍል ህመም ሰብ - ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ኤሌያስ እና የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ሀኪሙ ዶ/ር መሃመድ አወል አህመድን በጥልቀት አወያይቷቸዋል።...more1h 0minPlay
September 01, 2025ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የተለወጠው የወያኔ ዛፍ ወይም 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ'“ሀሳቤ ለሞቃታማ ሥፍራዎች ተስማሚ ጥሩ የግንባታ መሣሪያ ማምራት ነበር። ስለዚህ ዋናው ሀሳቤ ከሄምፕክሪት ግንባታ ነበር የመነጨው። ከዛ ነበር ቴክኖሎጂውን የቀዳሁት። ፕሮስክሪት ወደተባለው የራሳችን ምርት ነበር የቴጂክኖሎጂ ሽግግር የተደረገው” ሲል ሲቪል መሃንዲሱ ሱራፌል በላይ ተናግሯል። 'ጁሊፍሎራ' በኢትዮጵያ በረባዳማ ሥፍራዎች ወይም በቆላማ አካባቢዎች የብዝሃ ህይወትን የሚያዛንፍ የአርሶ አደርና አርብቶ አደሩን ህይወት እየጎዳ ያለ መጥፍ ዕፅ ነው። ይህን ተክል ለማስወገድ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። በዚህ ረገድ የሶቨርኒቲ ሶርስስ አቅራቢ በተለምዶ 'የወያኔ ዛፍ' ተብሎ የሚጠራዉን 'ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' ን ከጎጂ ተክልነት ወደ ግንባታ መሣሪያ ግብዓትነት የለወጠው የሲቪል ምህንድስና ባለሙያው ሱራፌል በላይን በመጋበዝ ጥልቅ ወይይት አከናውኗል። የፀሐይ እና ታዳሽ ኃይል በተመለከተ ከኢትዮጵያ የፀሐይ ሃይል ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ የምሥራች ሲሳይ ጋር የተደረገው አጭር ቆይታም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።...more30minPlay
August 28, 2025የጤናው ዘርፍ የቴክኖሎጂ ዐቢዮት በአፍሪካ“የዲጂታል መሩ ጤና የወደፊቱ የዓለም ስርዓተ ለውጥ ነው። ፕላኔታችን የዓለም ምጣኔ ሐብት ነው። የዲጂታል መር ጤና ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ጉዳይ ነው። የእናቶች ሞት፣ ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች፣ በፅኑ ህመም ያሉ ህመምተኞች ባሉበት ሁኔታ የዲጂታል መር ጤና ተግዳሮቶቹን የመቋቋሚያ ሁነኛ መላ እየሆነ መጥቷል” ሲሉ የፓን - አፍሪካ ዲፕሎማቲክ ማኅበር ዋና ኃላፊ ዶ/ር ሶስተንስ ባጉሜምሄ ተናግረዋል።ዶ/ር ሶስተንስ አክለውም፡- “የእርዳታ ድጋፍ መቋረጥ የዓለማችን ዋነኛ እክሎች ቢሆኑም የተለያዩ ዲጂታል መር የጤና ባለድርሻዎች እንዳተባበሩ በማድረግ በዋሻው ጫፍ ላይ ጮራ እንዲፈነጥቅ የሚያደርግ ነው'' ብለዋል።...more30minPlay
August 26, 2025በአፍሪካ የጋዜጠኝነት ትምህርት ተግዳሮትና ተስፋዎቹ“የቅኝ ግዛት ሚዲያዎች በአህጉሪቱ ላይ ችግሮችን ይፈጥራሉ። ምክንያቱም ምዕራባዊያን ሚዲያዎች የአፍሪካ መልካም ጎኖችን ሊዘግቡ ስለማይችሉ። አፍሪካን ሁልጊዜ እንደ ጦርነት፣ ርሃብ እና በሽታ መናኸሪያ ብቻ አድርገው ነው የሚስሉት" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህር ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ ተናግረዋል።የአፍሪካ የጋዜጠኛነት ትምህርትን ዳግም ማጤን በርካታ ችግሮችን እንደሚፈታ ይታመናል። በዚህም የዘርፉን ጠቀሜታ እና ተፅዕኖ ለማሳደግ እምቅ መፍትሔዎችን የሚያመጣ እንደመሆኑ በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ት/ቤት መምህራን የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻን እና ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይን በመጋበዝ ጥልቅ ወይይት አከናውኗል።...more1h 0minPlay
August 22, 2025ሰው ሰራሽ አስተውህሎት:- የኢትዮጵያ የኪነ ህንፃ ታሪክና ባህል ከቴክኖሎጂ አኳያ''አዲሱን ቴክኖሎጂ ከቀደምቱ የኢትዮጵያ ኪነ ህንፃ ጋር ለማዋሃድ በቅድሚያ መደረግ ያለበት ጥናት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩት ኪነ ህንፃዎች ምን ምን የተለየ የራሳቸው ነገሮች አላቸው፣ ጠባያቸው ምንድነው፣ በምን አይነት ቴክኖሎጂ ነው እየተሰሩ የነበሩት፣ ማቴሪያል ምናምን የሚሉ ነገሮችን በደንብ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም አዲሱን ቴክኖሎጂ መላመድ ያስፈልጋል'' ሲል የዘርፉ ባለሙያ ዳንኤል ተመስገን ይናገራል ።🎙 በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በኢትዮጵያ የኪነ ህንፃ ዘርፍ ታሪክና ባህልን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማዋሃድ ሰው ራሽ አስተውህሎት የሚጫታወቸው ወሳኝ ሚና እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የምህንድስና ባለሙያና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህንፃ ኮሌጅ መምህር ታደሰ ግርማይ እንዲሁም ወጣቱን የዘርፉ ባለሙያ ዳንኤል ተመስገንን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
August 20, 2025እናትን ከሞት መታደግ ቤተሰብን ማዳን ነው፦ የእናቶች ጤና አገልግሎት በኢትዮጵያ"የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእናቶች ሞት ጉዳይ በትኩረት ሲሰራ የተሻለ በጀት፣ ትኩረት፣ የስልጠና ዕድሎች፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የጤና ባለሙያዎችን በጎለበተ እውቀትና መሠረተ ልማት ማስታጠቁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል። የእናቶች ሞት ብዬ መናገር እችላለሁ። ለዚህም ሁልጊዜም አመስጋኞች ነን። አንዲት እናትን ማዳን አንድ ቤተሰብ እንደመታደግ ነው'' ሲሉ የጽንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶ/ር ምስክር አንበርብር ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በወሊድ ሆነ በድህረ ወሊድ ወቅት ስሚፈጠር የእናቶች ሞት፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ እያደረገች ያለችውን አበረታች ሥራዎች እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመወያየት የጽንስና የማህፀን ስፔሻሊስቶቹን ዶ/ር ምስክር አንበርብር እና ዶ/ር ታጠቅ ተስፋዬን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
August 18, 2025የፑቲን እና ትራምፕ ስብሰባ መልዕክት ፦ ዓለም በባለብዙ ዋልታ ማዕቀፍ“ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ይልቅ ፕሬዝዳንት ፑቲን ያሸነፉ ይመስለኛል። ትራምፕ በድጋሚ ከተመረጡ በኋላ ዩክሬንን በተመለከተ የታዘብነው አንድ ነገር፣ በምዕራባውያን ኃይላትና አጋራት መካከል ትልቅ ክፍፍል ተፈጥሯል። ቀደም ባሉት ጊዜያት በባይደን አስተዳደር ዘመን አውሮፓውያን ከዋሽንግተን የሚወጣውን ማንኛውንም ነገር በጥብቅ ይከታተሉ ነበር። አሁን ግን ግልጽ ተቃውሞ አይተናል። ዜለንስኪ ቢሆን ፕሬዚዳንት ትራምፕን ይቃረናቸዋል። ስለዚህ አንድ ግልጽ የሆነው ነገር በምዕራባውያን አጋራት መካከል መለያየት ያለ ይመስለኛል " ሲሉ ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፋለ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ ያደረጉት ውይይትን በስፋት ያስቃኛል።በመሪዎቹ ጉባዔ የተነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታ፣ ከጉባዔው መነሻነት ወደፊት የሚጠበቁ ጉዳዮችና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦችን ለመወያየት ምሁሩና የፖለቲካ ሳይንቲስቱ ዶ/ር አስናቀ ከፍለ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እንዲሁም ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን እንዲሁም ሱዳናዊው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ፣ ዲፕሎማትና ጋዜጠኛው መኪ ኤልሞግራቢን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
FAQs about Sovereignty Sources:How many episodes does Sovereignty Sources have?The podcast currently has 119 episodes available.