የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የማዕድን ሀብቶች አላት ፤ ከእነዚህም መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም እና ሌሎቹ በምድሯ ይዛለች።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ትናንት ለምክርቤት አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ማዕድንን በተመለከተ "ኢትዮጵያ ከፍተኛ ማዕድን ሀብት ያላት ሀገር ናት [...] ዘንድሮ ከወርቅ ብቻ [አምና ከነበረው በ10 እጥፍ ዕድገት] 3.5 ቢሊየን ዶላር ከዉጪ ንግድ አግኝተናል" ብለዋል።
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ማዕድን እና ጂኦሎጂካል ሀብት ፍለጋ ከሩሲያ ጋር ስላለው ስትራቴጂያዊ ትብብርና ሌሎች ተያያዥ ሀሳቦች በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር በቀለ አየለ በዳዳ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ረዳት ፕሮፌሰር እንዲሁም በማዕድን ዘርፎች አማካሪ ሙስጠፋ ሻይኮ ሼኩን ጋብዟቸዋል።