ከዕውቀት ሽግግር እስከ ኢነርጂ ሉዋዓላዊነት፣ ብሎም እስከ ጤናው ዘርፍ - አዲስ ምዕራፍ ተጀምሯል።
የኒውክለር ሳይንስን ለሰላማዊ ጉዳይ የማዋል ቁርጠኝነት በጤናው ዘርፍ አንድ ብሏል።
የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መርሃ ግብሩ ስለኒውክለር ኢነርጂ በኢትዮጵያ እንዲሁም በዘርፉ ከሩሲያ ጋር ስላለ ትብብርና አጋርነት በጥልቀት ለመወያየት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው፣ በኢትዮጵያ የኒውክለር ኢነርጂ ሶሳይቲ ዳይሬክተር እንዲሁም ዶ/ር ጥላሁን ተስፋዬ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል ፣ የኒውክለር ፊዚክስ ስትሪም ተባባሪ ፕሮፈሰርን ጋብዟቸዋል።