Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣... more
FAQs about Sovereignty Sources:How many episodes does Sovereignty Sources have?The podcast currently has 119 episodes available.
August 15, 2025የፑቲን - ትራምፕ ውይይት፡ የዓለም ዓይኖች ሁሉ አላስካ ላይ አማትረዋል"ከአውሮፓውያኑ እና ዩክሬን የበለጠ አስፈላጊው የሩሲያ እና የአሜሪካ ንግግር ስለሆነ ዩክሬን ብቻ ሳትሆን አውሮፓውያኑም ከዚህ ሂደት ውጭ ናቸው። ስለዚህ ትራምፕ ራሳቸውን አጋር ለማድረግ ከሌሎች ኃይሎች የበለጠ ጠንካራ ከሆነችው ሩሲያ ጋር ለመነጋገር ብልህ መሆንን የተረዱ ይመስለኛል" ሲሉ የታሪክ ምሁሩና የፖለቲካ ተንታኙ ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ኃያላኑ የዓለም መሪዎች ቭላድሚር ፑቲንና ዶናልድ ትራምፕ በአላሳካ በሚያደርጉት ተጠባቂ ስብሰባ በሰፊው ይዳስሳል።በስብሰባው የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች፣ የግንኙነታቸው ፖለቲካዊ አንድምታና ሌሎች በርካታ ተያያዥ ሀሳቦች ለመወያየት ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፣ የታሪክ ምሁርና ተመራማሪ እንዲሁም ዶ/ር ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ ፣ የታሪክ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ እና ጉምቱው ዲፕሎማት አምባሳደር ጥሩነህ ዜናን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
August 13, 2025ከሩሲያ ለዘመናት የተዘረጋው የትምህርት ዕድል ለወጣት አፍሪካዊያን“በውጤቱ እኛንና መሰል ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ አሁን በአብዛኛው በተለያዩ የህክምና፣ የእርሻ እና ሌሎች ዘርፎች የሚሰሩ የቀድሞ ተማሪዎች አሉ፤ በፖለቲካው ረገድም ትልቅ ቦታ የደረሱ ሰዎች አሉ፤ በከፍተኛ የስልጣን ወይም የሥራ አመራር ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡ በዚህም በአገሪቷ የተማረው የሰው ኃይል ቁጥር እየጠነከረና እየሰፋ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ በምርምሩም የተሰማሩ ሰዎች አሉ ዛሬም ድረስ - ሲሉ ዶ/ር ክብሩ ቸርነት ተናግረዋል”በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በየጊዜው እየጨመረ የመጣው ሩሲያ ለወጣት አፍሪካዊያን ተማሪዎች እያመቻች ያለችው የትምህርት ዕድልና ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት ተማሪዎች ዶ/ር ክብሩ ቸርነት እና ዶ/ር ደረጄ ጌታሁንን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
August 11, 2025ኢትዮጵያ - ለተመራማሪዎች የተፈጥሮ ቤተ- ሙከራነት ለምን ተመራጭ ሆነች?'የመሬት መንቀጥቀጥ ብዙ ቦታዎች ላይ ቢፈጠርም በአብዛኛው ከባህር ወይም ከውቅያኖስ በታች የሚፈጠር ነው፡፡ አትላንቲክ ውስጥ አለ፣ ህንድ ውቅያኖስ ውስጥ አለ፣ ልዩ ልዩ ቦታ አለ፡፡ በደንብ ግን የመፈጠሩ ሂደት የሚታየው ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሰምጥ ሸለቆ አካባቢ ነው ።'' የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በዛሬው መሠናዶው በርዕደ መሬት እና ተያያዥ ጉዳዮች ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) ጋብዟቸዋል።...more1h 1minPlay
August 07, 2025ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኢ-ፍትሃዊነትና ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ፦ በፓን አፍሪካኒዝም ዕይታ"የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተመለከታቸው 33 ጉዳዮች መካከል 90% በላይ የሚሆኑት የደቡባዊ ዓለም ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። በአጋጣሚ ብቻ የሆነ አይደለም፤ ይልቁን የምዕራባውያንን ጥልቅ አድልዎ የሚያሳይ ነው። አንድም ክንደ ፈርጣማ የምዕራቡ ዓለም መሪ ወደ ፍርድ ቤቱ አልቀረበም፣ ይህም እምነትን ያዳክማል። ስለዚህ ለተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ህጎች እንዳሉ ያረጋግጣል።" ሲሉ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት ምሁሩ መሀመድ አወል ሀጎስ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለፓን አፍሪካኒዝም፣ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አድሏዊ ፍትህና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በጥልቀት ለመወያየት በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ አንትሮፖሎጂስት ምሁሩ መሀመድ አወል ሀጎስን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
August 05, 2025ኢትዮጵያን እንቃኛት፡ የእምቅ ብዝሃ ህይወት እና የአካባቢ ጥበቃ ተምሳሌት"ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የብዝሃ ህይወት ምንጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ነች። ለዚህም ከ125 ሜትር የባህር ወለል በታች፣ ዳሎል እስከ ከፍተኛው የተራራ ጫፍ ወይም 4620 ሜትር የሚረዝመው ራስ ዳሽን ተራራ በአብነት ይጠቀሳሉ። በደን ብዝሃ ህይወት ረገድ በርካታ የዱር እንስሳት፣ እፅዋት፣ አዕዋፋት እና ሌሎቹ ሀገሪቷን ልዩ እንድትሆን አድርገዋታል።”በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የዱር እንስሳትን እና ቱሪዝምን የሚደግፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የብዝሃ ህይወት እና አረንጓዴ እድገት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት የብዝሃ ህይወትና አካባቢ ጥበቃ አማካሪው ስሜነህ አድማሱን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
August 01, 2025የአፍሪካ የማዕድ ጥበብ ሲገለጥ“የአፍሪካ አህጉር የበርካታ ሀገር በቀል የምግብ ስርዓቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የምግብ ስርዓቶች በእምቅ እውቀት፣ በዘላቂና ዘመን ተሻጋሪ አውዶች የተሞሉ ናቸው'' ሲሉ ሼፍ ፋትማታ ቢንታ ተናግረዋል። 🎙 በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው ስለአፍሪካ የምግብ ስርዓትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ለመወያየት እንደ ሼፍ ቢንታ ያሉ ሙያተኞችን ጨምሮ በርካታ የዘርፉ ባለሙያዎችና የባህል መሪዎችን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
July 30, 2025የኒውክለር ኢነርጂ ትግበራ በጤናው ዘርፍ - የሮሳቶም አሻራ በኢትዮጵያ“ኢትዮጵያ ከሮሳቶም ጋር በመደራደር ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን፣ ለሌሎች ሀገራት ባለሙያዎች እና ተማሪዎች ክፍት የሚሆን፣ የኒውክሌር ማሠልጠኛ ማዕከል ወይም የነፃ ትምህርት ዕድል ፕሮግራም ማቋቋም ትችላለች'' ሲሉ በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክለር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ ተናግረዋል።በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የኒውክለር ኢነርጂ ትግበራ በጤናው ዘርፍ እና ሌሎች ጉዳዮች ለመወያየት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ፊዚክስ ተመራማሪው ቸሬ ሲሳይ እና በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የኒውክለር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኩሩቤል ተስፋዬን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
July 28, 2025ገዳይ ግን ቀድመው የሚከላከሉት፦ የኢትዮጵያ ትግል ከጉበት በሽታ ጋር“ባለን መረጃ መሠረት የጉበት በሽታ ከባድ ችግር ነው። ምናልባት ተኝቶ ህክምና ከሚገቡት 12% የሚሆኑ ታካሚዎች ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በሆስፒታል ውስጥ የሟቾችን መጠን በተመለከተ 30 ወይም 31% ሟቾች በቀጥታ ከጉበት በሽታ ቫይረስ ጋር የተገናኙ ናቸው።” በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ አቅራቢው የዓለም የጉበት በሽታ ቀንን መሠረት በማድረግ በዓለም ላይ ገዳይ ከሆኑ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ ስለሆነው የጉበት በሽታ እና ቫይረሱን ለማጥፋት ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለችው ትግል ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጨጓራ እና ሄፓቶሎጂስት ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ረዘነ በርሄን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
July 24, 2025የዲጂታል መር የጤና ሥርዓት ዐቢዮት በኢትዮጵያ!"ዲጂታል መፍትሄዎች የጤና አጠባበቅ ስርዓቱን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የምንሰጥበትን መንገድ በአዲስ መልክ ፈጥረውታል። በዚህ ሂደት ውስጥ ዲጂታል አገልግሎቱ የጤና አሰጣጥ ስርዓትን የሚያሻሽልባቸው በርካታ ተግባራዊ መፍትሔዎቼ አሉት።"በዚህ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት አቅራቢው ስለዲጂታል መር የጤና አልግሎት ስርዓትና የስታርታፖች ሚና በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመነጋገር ጋይኒኮሎጂክ ኦንኮሎጂስት እና የዊኬር ኢንተገሬትድ የጤና ኔትወርክ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቤተል ደረጄን ጋብዟቸዋል።...more30minPlay
July 22, 2025የቴአትር ጥበብ፦ የኢትዮ-ሩሲያ የትስስር መልክየባህል ገፆች፣ መንፈሳዊ፣ አካላዊ እና ቁሳዊ ባህሎችን መለዋወጥ መቻል ትልቅ ዕድል ነው። ይህም ጸሐፊያን በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለ የቀደመ መስተጋብራዊ ልማትን በአንክሮ እንዲፈትሹ ያደርጋቸዋል።''በዚህ Sovereignty Sources የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፖድካስት፣ አቅራቢው ስለ ቴአትር ጥበብ፣ የኢትዮ - ሩሲያ ግንኙነትን ለማጠናከር ስላለው ፋይዳ ለመወያየት ጳውሎስ አዕምሮ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትሪካል ጥበባት እና የባህል ማዕከል አካዳሚክ ዲን ጋብዟቸዋል።...more1h 0minPlay
FAQs about Sovereignty Sources:How many episodes does Sovereignty Sources have?The podcast currently has 119 episodes available.