መንፈሳዊ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የሚመራ ነው:: ይህ ምሪት ለሰው ከመዳኑ ከበረከቱ ከጥበቃው ጋር እና ለፈቃዱ ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ሲሆን የእግዚአብሔርን ሰዓት ይመለከታል:: በመንፍስ የሚመራ ሰው በእምነትና በመታመን እያደገ በሕይወት ይኖራል:: ሆኖም ሰው ከራሱ መንፍስ ከሚሰማው ልምምድ ብቻ ያደገ ሆኖ በእምነት እና በመታመን ላያድግ ይችላል:: የዚህም ኪሳራ በፍሬው ይታወቃል:: አለማመን ወይንም አለመታመን ለእግዚአብሔር ዘላለማዊ ሀሳቡን ከማከናወን አያግደውም :: እግዚአብሔርን
በማውቅ በፀጋ እና በእውቀት ለማደግ ለፈቃዱ የተሰጠ አይምሮ እና ልብ ሊኖርን ይገባል::