በዙርያችን ባለው ወጀብ እና አውሎንፋስ ሳንናወጥ እግዚአብሔርን ለመስማት በእግዚአብሔር ፀጥታ ውስጥ መገኘት ያስፈልገናል::
ትልቁ የህይወታችንየእምነት ደረጃ ልኩ በእግዚአብሔር ፀጥታ ውስጥ መገኝታችን ሲሆን በመለኮት ፀጥታ ውስጥ በመሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድና ምሪት ትክክለኛውን የእግዚአብሔር ድምፅ እንሰማለን::
በመለኮት በፀጥታ ውስጥ ያለች ነፋስ እግዚአብሔርን ትጠብቃለች :: በፀጥታ ውስጥ ለመሆን እግዚአብሔርን በቃሉ ማወቅና መጠጋት አለብን::