Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
September 17, 2021የኋለኛው ቤት ይበልጣልየኋለኛው ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ነው ደግሞም ቃሉ እንደሚል የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እኛ አማኞች በደሙ ነጽተን በክርስቶስ እየሱስ ልጆች የሆንን ሁላችን ነን፣ ይህንን ቤተ መቅደስ የሚበልጥ ያደረገው በሰው የተሰራ ሳይሆን አግዚአብሔር የሰራውና ህያው በመሆኑ ነው፣ ይህ ህያው ጌታ በመንፈሱ ለእርሱ በተሰጡ አማኞች ውስጥ ይኖራል፣ ከውጪ ሳይሆን በውስጥ ሆኖ ልጆቹን ይመራል፣...more38minPlay
September 16, 2021ራስን በጌታ ማግኘትለአንድ አማኝ ትልቅ በረከት በጌታ መገኘት ውስጥ ራሱን ማግኘት ነው፣ እምነት በእግዚአብሐር መገኘት ውስጥ እንድንገኝ ያደርገናል፣ ለቃሉ ታማኝ ስንሆን አንደ ቃልህ ወይም እንደፈቃድህ ይሁን ብለን ስንፈቅድ ለጌታ እንመቻለን፣ የምንኖረው ለህይወት እንጂ ኑሮአችን በህይወታችን ላይ ተፅእኖ እንዲያደርግ መፍቀድ የለብንም፣ የምናስበውን ለእግዚአብሔር ክብር ስናስብና በርሱ መገኘት ውስጥ ስንሆን ኑሮ ላይመቸን ይችላል ህይወት ግን ይመቸናል፣...more38minPlay
September 16, 2021በልሳን ስለ መናገር የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላልመንፈስ ቅዱስ በሙላት የሚሰራብን እራሳችንን የሰጠነውንና የተጠማነውን ያህል ነው፣ የሰዎች ቋንቋ የተደበላለቀው ለክፉ ስራ ስለተባበሩ ሲሆን ይህንን የተለያየውን ቋንቋ ወደ አንድነት መንፈስ ለማምጣት ጌታ ለቤተ ክርስቲያን ይህንን የልሳን ስጦታ ሰጠ፣ ይህ ልሳን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሰረተ እውነት ለመሆኑ ምስክር አንዲሆን ሰው በሚሰማውና በሚረዳው ቋንቋ ይነገራል፣ አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት የሚስጥር ቋንቋ ነው ደግሞም በሌሎች ሰዎች የሚተረጎምና ራሳችንን የምናንጽበት ነው፣ ይሀን ልሳን ለመቀበል ሰው ወደ እምነት መምጣት አለበት፣...more36minPlay
September 16, 2021እንዴት እንጸልይ ክፍል 18እንዴት እንጸልይ ያዕ 2:14-26 ዕብ 10:38 ሮሜ 1:17 ገላ 3:11 ክፍል 18...more15minPlay
September 15, 2021ህይወትን መጠበቅ መጽሐፈ ኢያሱ 6:1-25ህይወትን የተቀበልነው በነጻ ቢሆንም ይህን ህይወት ለመጠበቅ ግን ዋጋ ያስከፍላል፣ በጥንቃቄ ያልተጠበቀ ህይወት አጥር እንደሌለው ቤት ነው፣ ህይወትን በጥንቃቄ ለመጠበቅ ዕለት ዕለት ስጋችንን እየጎሸምን አይናችንንና ጆሮእችንን ከክፉ በመጠበቅ መንገዳችንን በቃሉና በጸሎት ማንጻት ይኖርብናል፣ በተጨማሪ በአንድ አማኝ በረከት ሌላው አማኝ ሁሉ ስለሚባረክ ለራሳችን ህይወት መጠንቀቅ ማለት ለህብረትም መጠንቀቅ ነው::...more42minPlay
September 15, 2021እግዚአብሔር ያከበሩትን ያከብራል ትንቢተ ዳንኤል 6:28ለዳንኤል የስኬት ምክንያቶች ለእግዚአብሔር በመቀደስ በጽድቅ ከመኖሩ ጋር በተጨማሪ የእምነት አጋሮችን ማግኘቱ ነው፣ ዛሬም እኛ በአካል ውስጥ እንዳሉ ብልቶች ከእግዚአብሔር በታች አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን፣ በተከፈተው በር ሁሉ በመግባት ህብረት ማድረግ ሳይሆን በእውነት ጌታን ከሚወዱ በጽድቅ መንገድ ከሚሄዱ ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ ያስፈልገናል፣ ቃሉም እንደሚያስተምረን በአንድነት ተስማምተን የምንጸልየው ጸሎት በእግዚአብሔር ይሰማል::...more45minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.