Sign up to save your podcastsEmail addressPasswordRegisterOrContinue with GoogleAlready have an account? Log in here.
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.
July 24, 2021የእግዚአብሔርን ነገር መጠበቅ የማቴዎስ ወንጌል 1:1-25ከአብርሃም እስከ ዳዊት አስራ አራት ትውልድ አለ፣ ከዚያም እስከ እየሱስ ድርስ ሄዷል፣ አሁንም ሰዎችን ሁሉ በክርስቶስ የማዳን ስራ፣ የመንግስቱ ስራ እየሄደ ነው። ይህ የእግዚአብሔር ሃሳብ ከትውልድ ወደትውልድ እየተላለፈ የመጣው፣ የእለቱን ሳይሆን የዘላለሙን በተመለከቱ ስዎች ነው። ነገሮችን በራሳችን እይታ ማየት ከጀመርን፣ የመለኮትን ሃሳብ አናሳልፍም፣ እየተራመደ ያለውን የእግዚአብሔርን ስራ ያስቆማል። ማለትም፣ ጌታ በራሱ መንገድ ስራውን ይቀጥላል ግን በኛ አልፎ አይሄድም፣ የጌታንም ስራ በትውልዳችን አናይም ይህ ደግሞ ትልቅ ጉዳት ነው።...more19minPlay
July 24, 2021ጥያቄ እና መልስ ክፍል 58የዛሬ ጥያቄዎች1. ጌታ ባደረገልን ነገር ጌታን ማወቅ አንችልም የሚለው ይብራራልን።2. ሰዎች ፅድቅን ለማድረግ ከኢየሱስ ጋር የሆኑ እመመሰላቸው ከቴታ ጋር ላይሆኑ ይችላሉ የሚለው ይብራራልን።3. ለሀጢያት መሞት ማለት ምን ማለት ነው?4. የማላ የተትረፈረፈ በለከት ምንድን ነው?5. የተቀበልነው ወንጌል ኢየሱስ ማን እንደሆነ ለእኛ ይወስነዋል የሚለው ይብራራልን።...more42minPlay
July 23, 2021የልባችሁን በር ክፈቱ::እግዚአብሔር የሰውን ዋና ነገር ይፈልጋል:: ልባችንን:: የሰው ሁለንተና በልቡ ካለው ሀሳብና ፈቃድ ጋር የተያያዘ ነው:: ስለዚህ በፊቱመልካም እንዲሆንልን እንታዘዘውና እንገዛለት ዘንድ ጌታ ልባችንን እንድንከፍት ፈቃዱንም ከቃሉ ምክር እንድንቀበል ይጠይቀናል:: ሰምቶ ለሚከፍት ከጥፋት መዳን ይሆንለታል:: የተራቆትንበት ጉድለታችንም ይሞላል:: በረከትም ወደ ህይወታችነ ይመጣል::* ለወዳጃችን ለጌታ ኢየሱስ ልባችንን ላለመክፈት ምክንያት አይኑረን::...more35minPlay
July 23, 2021የእግዚአብሔርን ነገር መጠበቅማርያም መልአኩ የነገራት መልእክት ምንም እንኳን ለሰው አይምሮ ከባድ ቢሆን፣ እርሷ ግን የእግዚአብሔርን ነገር በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር። መንፈሳዊ ህይወታችን ትክክል አለመሆኑ አንዱ መገለጫው መጠበቅ ሲያቅተን ነው።የምንጠብቀው የእግዚአብሔር እውነት ግን በውስጣችን ካለ፣ ለጠበቅነው ነገር ለመለየትና ዋጋ ለመክፈል አቅም ይሆነናል፣ የሰይጣን ፈተናም ሲመጣብን፣ የጠበቅነው እውነት ራሱ ጋሻ ይሆንልናል። ይህ በውስጣችን ያለው እውነት ደግሞ ተዳፍኖ መቅረት ሳይሆን በጸጋው በእኛ ውስጥ አልፎ ለትውልድ እንዲደርስ ያስፈልጋል።...more40minPlay
July 22, 2021እየሱስን ምን ያህል አውቀነዋል? ( የዮሐንስ ወንጌል 17:3)በዘመናችን እጅግ ብዙ የዕውቀት መገብያ ድርጅቶች ተከፍተዋል ነገር ግን እነዚህ ሁሉ የዕውቀት ስፍራዎች እግዚአብሔርን ወደማወቅ አያደርሱንም። ለኛ ግን በክርስቶስ እውነተኛ የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቦና ተስጥቶናል። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። እግዚአብሔርን ከማወቅ አንዱ ይህን አለም ለኛ እንዳልተገባ አድርጎ መቁጠር ነው።...more51minPlay
July 22, 2021ትንቢተ ኢዮኤል. 28-9 ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ የተሰጠ ተስፋ.የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ተስፋ፣ በክርስቶስ ደም ታጥበን የእግዚአብሔር ልጆች ለሆንን ሁሉ የተሰጠ ተስፋ ነው። መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፣ አዲስ ስውና ትሁት ያደርገናል፣ ሀይላችንና ሰላማችን፣ አፅናኛችን፣ አስተማሪያችን፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያሳስበን ነው። በዚህ ነውጥ በበዛበት አለም ውስጥ፣ ከመቼውም በበለጠ ይህ መንፈስ በሚይስፈልገን ጊዜ፣ ከዚህ ተስፋ ውጪ ብንሆን እጅግ በጣም እንጎዳለን።...more36minPlay
July 22, 2021መንፈሳዊነት ክፍል 2.እግዚአብሔር እንደፈቀደ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በማመን ልጆቹ የሆንን ሁላችን በእኛ ካደረው ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ መንፈሳውያን እንባላለን:: መንፈሳዊነታችንም እንደ ጌታ ፈቃድና ሀሳብ በመመላለስ በተግባር ይገለጣል:: ክርስቶስንም እንመስል ዘንድ እለት እለት በቃሉና በመንፈሱ እንሰራለን:: እኛም ለመሰራት እራሳችንን እናቀርባለንበምድር ላይ በተሰጠን አጭር የእድሜ ዘመን በቅድስና በፅድቅ አና በእውነት ልንመላለስ በጨለማውም አለም የወንጌልን ብርሃን በቃልና በህይወት ልናበራ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው::...more34minPlay
July 21, 2021የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መልክየቀደመችው ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል እውነት የምትመላለስ በፀና መሠረት ላይ የታነፀች ነች:: ይህ ደግሞ ከቃሉ የተነሳ በጌታ ላይ የፀና ህይወት መኖርን ያመለክታል::በእግዚአብሔር ቃል ሥር የሰደደና የፀና ህይወት ከየአቅጣጫው በሚነፍሰው የአመፅና የክፋት ንፋስ አይናወጥም:: ስለዚህም ነው ወንጌል በብዙ ፈተናና መከራ አልፎ ወደእኛ የደረሰው::በዚህ መልዕክት ቅዱሱ የእግዚአብሔር ቃል እለት እለት በህይወታችን ደግሞም በቤተክርስቲያን ያለውን ስፍራና ፋይዳ እንዲሁም ከእኛ የሚጠበቀው ምን እንደሆነ እንማርበታለን::...more41minPlay
FAQs about Voice of Truth and Life:How many episodes does Voice of Truth and Life have?The podcast currently has 1,418 episodes available.