የእግዚአብሔር ህዝብ በህይወት ጉዞው ላይ ሊጠነቀቅ ከሚገባቸው ነገሮች አንዱ ቸልተኝነት ነው:: ቸልተኝነት የተነገረውን ሰምቶ ከማድረግ ለከናወን የሚገባውን ከማከናወን መዘግየት ወይም እንደ ቀላል ቆጥሮ አሳንሶ ማየት ...ወዘተ ነው::
የክርስትና ህይወትና ኑሮ የድል የመሻገር ወደ ፊት የመራመድ ህይወት ነው:: ሰለዘህ በአንደዚህ አይነት ህይወት ቸልተኘነት ሰፍራ ሊኖረው አይገባም:: በመሆኑም እለት አለት ቸል ያልኩት ምን አለ? እያልን ራሳችንን እየጠየቅንና እየመረመርን የምንኖረው ኑሮ ነው::
- ከቸልተኝነት ስንላቀቅ ማምለክ እንደሚገባን እናመልካለን:: መፀለይ እንደሚገባን እንፀልያለን:: ማገልገል እንደሚገባንም እናገለግላለን:: ምንም በድካም ብንሆን የሚያበረታ ጌታ ፀጋን ሊሰጠን ከቸልተኝነት ወጥተን በትጋት እንድንሆን ሊረዳን የታመነ ነው::