የዛሬ ጥያቄዎች
1. እግዚአብሔር የሚፈልገው በሥፍራችን እንድንሆን ነው የሚለው ይብራራልን።
2. እግዚአብሔር በሰጠን አገልግሎት ሳይሆን እኛ በምንፈልገው አገልግሎት ብናገለግል እግዚአብሔር አያውቀንም ማለት ነው?
3. እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሰራው በሰጠን ህይወት ነው ተብሎ ተምረናል። ወደ ዚህ ህይወት እንዴት ነው የምንመጣው?
4. እንዴት ነው ይቅርታ የምንጠይቀው? ይቅርታ የጠየቅነው ሰው ይቅርታ ስንጠይቀው ይቅር ብያለው ማለት አለበት?
5. የእግዚአብሔር መገኘት ከህይወታችን ልናጣው (ሊጠፋብን) ይችላል?
6. መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ከየት ነው መጀመር ያለብን? እንዴትስ ነው ማንበብ ያለብን?
7. መንፈሳዊ ህይወት መለቀቅ አለበት የሚለው ይብራራልን።
8. መንፈሳዊ ሰው ነፍሱን ማዳመጥ ሲጀምር እግዚአብሔር ሩቅ ይሆንበታል፣ የተተወ የተጣለ ይመስለዋል የሚለው ይብራራልን።